"ኢትዮጵያዊነት በርቱዓዊነት" ተመረጠ! በርቱዓዊነት መርሕ፥ ፉክክሩ ሲያበቃ ትብብሩ ይጀምራል!
በ6ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምርጫ ክልል 28፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት።፣ በግል ዕጩነት ድምጽ ማግኘቴን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።
በ"ሐ" የምርጫ ምልክት እና "ኢትዮጵያዊነት በርቱዓዊነት" በሚል መርሕ፣ የምርጫ ቅስቀሳ አስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም ለወራት ባደረግነው እንቅስቃሴ በልዩ ልዩ ድጋፎች የተራዳችኹኝን፣ በምርጫ ኮሚቴነትና በታዛቢነት ያገለገላችሁትን፣ የገጠማችኹን ችግሮች ኹሉ ታግሣችኹ ድምፃችኹን የሰጣችኹኝን መራጮቼን በሙሉ ከልብ አመሰግናለኹ።
ይህ ምርጫ ምርጫ እንዲሆን ዋጋ የከፈላችሁ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ታሪክ በደማቅ ቀለም ይጽፋችኋል። የተሸነፋችሁም አንዱንና ዋናውን የኢትዮጵያ ጎደሎ ሞልታችኋል። ኢትዮጵያ በፖለቲካ ፉክክር የተሸናፊ እንጂ የአሸናፊ እጥረት አልነበረባትም። እናንተ ይሄንን በመሙላት አሸንፋችኋል። የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ሚዲያዎች፣ ታዛቢዎችና የጸጥታ አካላት ሁሉ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ የከፈላችሁት መሥዋዕትነት የሀገራችን የክንድ ንቅሳት ሆኖ የሚኖር ነው።
ከሁሉም በላይ ለ12 ሰዓት እንደ ሰዓታት ቋሚ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ ቆሞ የመረጠው ሕዝብ፣ ጠላትን ሐሞቱ ያለቀ፣ ወገንን ልቡ የሞቀ የሚያደርግ ነበር።
አኹን የፉክክር ወቅት አብቅቷል። ቀጣዩ ጊዜ ለመረጣችኹኝም ላልመረጣችኹኝም ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በርቱዓዊነት የመተባበር ኢትዮጵያዊ መንፈስ ብቁ የሕዝብ ወኪል እና እንደራሴ ለመኾን የበኩሌን ጥረት የማደርግበት ነውና ጸሎታችኹ እና ድጋፋችኹ እንዳይለየኝ አደራ እላለኹ።