Репост из: 🌹ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም🌹
🍃ሴት ልጅ ሐጅና ዑምራህ ላይ፥🍃
1/ወንዶች ባሉበት አካባቢ ላይ ተልቢያህ (ለብይክ አላሁመ ለበይክ...) እና ተክቢራህ ስትል ድምጿን ጮኽ አታደርግም (ማድረግ የለባትም)።
2/የጠዋፍ የመጀመሪያ 3ዙሮች ላይ እንደ ወንዶች ፈጥና አትራመድም። ሰፋና መርዋ ላይም ወንዶች የሚሮጡበት ስፍራ ላይ አትሮጥም።
3/ የሰፋና መርዋ ከፍታ ላይ አትወጣም (የሁለቱም የታችኛው ጫፍ ላይ ብቻ እየደረሰች ትዞራለች)።
4/ጠዋፈል-ወዳዕ (የመሰናበቻ ጠዋፍ) ሳታደርግ ሐይዷ ቢመጣ ጠዋፉን ትታ መሄድ ይፈቀድላታል፤ ካልቸኮለችና ካልተቸገረች ጠብቃ ብታደርግ ግን የተሻለ ነው።
5/ከኒቃብና ጓንት በስተቀር ሸሪዓህ የማይከለክለውን የፈለገችውን ልብስ መልበስ ትችላለች። ወንድ ያለበት ቦታ ላይ ስትሆን ፊትና እጇን ከኒቃብና ጓንት ውጪ ባለ ጨርቅ መሸፈን አለባት፤ ግዴታዋም ነው! እነ ዓኢሻና ሌሎችም ሰሓባ ሴቶች ይህን ነበር የሚያደርጉት።
6/ሙዝደሊፋህ አድራ ንጋት ላይ ከሰዎች ጋር ወደ ሚና መጓዝ የሚከብዳት ከሆነ ሙዝደሊፋህ ላይ እስከ እኩለ-ለሊት ድረስ ከቆየች በኋላ ወደ ሚና መጓዝና በደረሰችበት ሰዓት (ከፈጅርም በፊት ቢሆን) ጠጠር ወርውራ ወደ ማረፊያዋ መሄድ ትችላለች።
7/በእርግዝና፣ በህመም እና መሰል ምክንያቶች ጠጠሮችን እራሷ እየሄደች መወርወር ከከበዳት ሌላ ሰው ወክላ ማስወርወር ትችላለች።
8/ ለንጽህናው ጥንቃቄ ከማድረግ ጋር በሰፋና መርዋ መሀል ሐይድ ላይ እንኳ ብትሆን መመላለስ (ሰዕይ ማድረግ) ትችላለች።
9/ሐይድ ላይ ሆና ከከዕባህ ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ በመሰረቱ አትችልም፤
👉🏻ነገር ግን የሐጅ መሰረት ለሆነው ጠዋፈል-ኢፋዷ በምንም መልኩ እስክትጠራ መጠበቅ ወይም ወደ ሀገሯ ሄዳ ስትጠራ ተመልሳ መጥታ ማድረግ የማትችል ከሆነ ሙሉ ንጽህናዋን ከመጠበቅ ጋር ጠዋፍ ማድረግ እንደምትችል ኢብኑ ተይሚያን ጨምሮ የተወሰኑ ሊቃውንት ገልጸዋል። ወደ ሀገሯ ተመልሳ ስትጠራ ለጠዋፍ መመለስን ከወሰነችም ባለ ትዳር ከሆነች በዚህ መሀል የግብረ-ስጋ ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድላትም!
ነገር ግን ሳይቸገሩ መመለስ ለሚችሉ ሴቶች የሚሻለው ሲጠሩ ተመልሶ ማድረጉ ነው።
✍ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
@ዛዱል መዓድ7/12/1439 ዓ.ሂ
🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐https://telegram.me/ahmedadem