Репост из: 😘✌محمد☜☆☞ حب رسل✌😘
አላህ ( ሱ.ወ) ጅብሪል (ዐ.ሰ) ምን በፈጠረ ግዜ አሳምሮ ነበር የፈጠረው:: 600 ክንፎችን የቸረው ሲሆን የአንዱ ክንፍ ርዝመት ከፀሐይ መውጫ እስክ ፀሐይ መግቢያ ይደርሳል።ጅብሪልም ይህን በተመለከተ ግዜ እንዲህ አለ ፡እንደኔ አሣምረክ የፈጠርከው አለን ? ብሎ አላህን(ሡ.ወ)ን ጠየቀው አላህም (ሡ.ወ) የለም አለው ።ጅብሪልም በጣም በመደሠት 2 ረካዐ ሀረመ ለያንዳንዱ ረካዐ 20 ሺ ዐመት ፈጀበት ።እንደጨረሠም አላህ(ሡ.ወ) ም የሚገባኝን መገዛት ተገዝተኸኛል እንዳንተ የሚገዛኝም የለም ነገር ግን በመጨረሻው ዘመን አካባቢ ነብይ ይመጣል እኔ ዘንድ ውድ የሆነ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የሚባል ፡የሡ ዑመቶች ደካሞች ወንጀለኞች ናቸው፡፡2 ረካዐ ይሠግዳሉ በመሠላቸትም ጭምር በአጭር ደቂቃ ከብዙ ሀሣብ ጭንቅ ጭምር ጋር ይሰግዳሉ።ነገር ግን በልቅናዬ በክብሬ ይሁንብኝ የነሡ ሠላት እኔ ዘንድ ተወዳጅ ነች ።ካንተ ሠላት የነሡ ሠላት እኔ ዘንድ ተወዳጅ የሆነችው እነሡ በኔ ትዕዛዝ ነው የሚሰግዱት አንተ ግን በሠጠሁህ ኒዕማ ተደሥተህ በፍላጎትህ ነው ።ጅብሪልም ለዚህ ኢባዳቸው ምን አዘጋጀህላቸው ሢልው ጀነቱል መዕዋ አለው ጅብሪልም ለማየት ፍቃድ ጠየቀ አላህ (ሡ.ወ)ም ፈቀደለት በሙሉ ክንፎቹ መብረር ጀመረ።1ክንፉ ሢዘረጋ 3 ሺ ዐመት ይቆርጣል እጥፍ ሢሆን እንደዛው።በንደዚ ሁኔታ 300 ዐመት በረረ ያም ሆኖ ደከመው አረፍ ብሎ ስጁድ አድርጎ አላህ ሆይ ግማሿን ደረስኩ ወይስ ሩቧን ወይስ ሲሶዋን ?? ብሎ ጠየቀ አላህ(ሠ.ወ) ም 3000 ዐመት ብትበር የሠጠሁክን ያክል ሀይል የሠጠሁክን ያክል ክንፍ እጥፍ ብሠጥህ አሁን የበረርከውን ያክል ብትበር የሙሐመድን(ሠ.ዐ.ወ) ዑመት የሠጠሁትን ስጦታ አንድ አስረኛውን አትደርስም !!!! አላሁ አክበር አላህ(ሡ.ወ) ምን ያክል ስጦታ አዘጋጀልን ለ 2 ረካዐ ሡብሀነ አላህ።ትክክለኛ ሠጋጆች አላህ ያድርገን። አሚን።
የሰሀቦችን ታሪክ ለማወቅ ከፈለጉ
@hayatusahaba
የሰሀቦችን ታሪክ ለማወቅ ከፈለጉ
@hayatusahaba