ሺርክና ተውሒድ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡
1. ሺርክ
"ሺርክ" شِرْك የሚለው ቃል "አሽረከ" أَشْرَكَ ማለትም "አጋራ" ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን "ማጋራት" ማለት ነው፤ ሺርክ በአምላካችን አላህ ሃቅ ላይ የሚሰራ ታላቅ በደል ነው፦
31:13 ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን፦ ልጄ ሆይ! በአላህ #አታጋራ تُشْرِكْ ፤ #ማጋራት الشِّرْكَ ታላቅ በደል ነውና ያለውን አስታውስ።
አላህ እኔነት ያለው አምላክ ሲሆን በእርሱ ላይ ምንም ተጋሪ እንዳናጋራ አዞናል፦
31:15 ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር "#በእኔ" "#እንድታጋራ" تُشْرِكَ ቢታገሉህም አትታዘዛቸው፤
22:26 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ #በእኔ ምንንም #አታጋራ لَا تُشْرِكْ ፤ ቤቴንም፣ ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ ባልነው ጊዜ አስታውስ።
ሺርክ ሁለት ነገርን ያቅፋል አንደኛ "ሙሽሪክ" ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ሸሪክ" ነው፦
ጭብጥ አንድ
"ሙሽሪክ"
የሚጋራው ሰው "ሙሽሪክ" مُشْرِك ማለትም "አጋሪ" ይባላል፤ አላህ በእርሱ የማጋራትን ወንጀል አይምርም፤ በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፤ መኖሪያውም እሳት ናት፤ ለአጋሪዎቹም ወዮላቸው፦
41:6 በላቸው፦ እኔ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ፤ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ወደርሱም ቀጥ በሉ፤ ምሕረትንም ለምኑት ማለት፣ ወደ እኔ ይወርድልኛል። #ለአጋሪዎቹም لِلْمُشْرِكِينَ ወዮላቸው።
4:116 አላህ በእርሱ #የማጋራትን يُشْرَكَ ወንጀል አይምርም ከዚህም ወዲያ ያለውን፣ ለሚሻ ሰው ይምራል። በአላህም #የሚያጋራ يُشْرِكْ ሰው ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ።
5:72 እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፤ አልመሲሕም አለ፦ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፤ እነሆ! በአላህ #የሚያጋራ يُشْرِكْ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፤ መኖሪያውም እሳት ናት፤ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም።
ጭብጥ ሁለት
"ሸሪክ"
እንዲሁ በኣላህ ላይ የሚያጋሩት ማንነትና ምንነት "ሸሪክ" شَرِيك ማለትም "ተጋሪ" ይባላሉ፤ አላህ በእርግጥም በጌትነቱ፣ በአምላክነቱ፣ በስሙና በባህርይው ተጋሪ የለውም፦
34:27 እነዚያን #ተጋሪዎች" شُرَكَاءَ አድርጋችሁ በእርሱ ያስጠጋችኋቸውን አሳዩኝ፣ ተዉ፣ "አታጋሩ"፤ በውነቱ እርሱ አሸናፊው፣ ብልሃተኛው፣ አላህ ነው፤ በላቸው።
6:163 «ለእርሱ #ተጋሪ" شَرِيكَ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል፡፡
2. ተውሒድ
የሽርክ ተቃራኒ ደግሞ "ተውሒድ" ነው፤ “ተውሒድ” توحيد የሚለው ቃል “ዋሐደ” وحد “አንድ አደረገ” ወይም “ነጠለ” ከሚል ስርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አንድ ማድረግ” ወይም “መነጠል” አሊያም “አንድነት” የሚል ፍቺ አለው፣ “ተውሒድ” توحيد “አንድነት”oneness” የሚለው ቃል የዋሒድ وَٰحِد ግሳዊ-ስም “Verbal Noun” “መስደር” مصدر ነው፣ አምላካችን አላህ "አል-ዋሒድ" እንደሆነ በተከበረ ቃሉ ይናገራል፦
41:6 በላቸው፦ እኔ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ፤ አምላካችሁ “አንድ” وَاحِدٌ አምላክ ብቻ ነው፤
6:19 «እርሱ “አንድ” وَاحِدٌ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡
የተውሒድ አስኳሉ ደግሞ "ተህሊል" تهليل,ነው፣ ተህሊል ማለትም “ላ-ኢላሃ ኢልለሏህ”لا اله الاّ الله "ከአንዱ አላህ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ማለት ነው፣ ይህ ተህሊል ከአላህ ሌላ ያሉትን ማንነት ሆነ ምንነት ውድቅ የምናደርግበት እና አላህን አንድ አምላክ ብቻ አድርገን ለማምለክ የምንነጥልበት "ጠንካራን ዘለበት" ነው፦
31:22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም ሰው፣ ""ጠንካራ ዘለበት"" بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፤ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው።
2:256 በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ""ጠንካራ ዘለበት"" بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡
ይህንን ጠንካራ ዘለበት አምላካችን አላህ በተከበረው ከሊማ በሶስት መልኩ ይዘረዝረዋል፦
ነጥብ አንድ
"ከእኔ በቀር አምላክ የለም"
አላህ ስለ እራሱ አንድ ነጠላ ማንነት ሲናገር፦ "ላ ኢላሃ ኢልላ አና" لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا "ከእኔ በቀር አምላክ የለም" በማለት ነው፤ ከአንድ በላይ አምላክነትን የሚጋሩ የሆኑ ማንነቶች ቢኖሩ ኖሮ የሚናገረው፦ "ላ ኢላሃ ኢልላ ነህኑ" لَا إِلَٰهَ إِلَّا نَحْنُ "ከእኛ በቀር አምላክ የለም" የሚል ነበር፤ ነገር ግን አላህ ሁሌም በመጀመሪያ መደብ ስለ አምላክነት የሚናገረው፦"ከእኔ በቀር አምላክ የለም" ብሎ ነው፦
16:2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል፤ ከሐዲዎችን በቅጣት አስጠንቅቁ፤ እነሆ "ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም" لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا እናም ፍሩኝም ማለትን አሳታውቁ በማለት ያወርዳል።
20:14 እኔ አላህ እኔ ነኝ፣ "ያለ እኔ አምላክ የለም" لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا እና አምልከኝ፤ ሶላትንም በርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ።
21:25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ "ከኔ ሌላ አምላክ የለም" لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا እና አምልኩኝ፣ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።
ነጥብ ሁለት
"ከአንተ በቀር አምላክ የለም"
ነብያት አላህ ሲያናግሩት፦ "ላ ኢላሃ ኢልላ አንተ" لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنْتَ "ከአንተ በቀር አምላክ የለም" በማለት ነው፤ ከአንድ በላይ አምላክነትን የሚጋሩ የሆኑ ማንነቶች ቢኖሩ ኖሮ የሚናገሩት፦ ""ላ ኢላሃ ኢልላ አንቱም" لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنْتُمْ "ከእናንተ በቀር አምላክ የለም" የሚል ነበር፤ ነገር ግን ነብያት ሁሌም በሁለተኛ መደብ ሲያናግሩት፦"ከአንተ በቀር አምላክ የለም" ብለው ነው፦
21:87 የዐሣውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ አስታውስ፤ እርሱም ላይ ፍጽሞ የማንፈርድበት መሆናችንን ጠረጠረ፤ ዐሳም ዋጠው፤ በጨለማዎችም ውስጥ ሆኖ ፦ "ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም" لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنْتَ ፤ ጥራት ይገባህ፤ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ።
ነጥብ ሶስት
"ከእርሱ በቀር አምላክ የለም"
ነብያት ስለ አላህ ሲናገሩ፦ "ላ ኢላሃ ኢልላ ሁወ" لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ "ከእርሱ በቀር አምላክ የለም" በማለት ነው፤ ከአንድ በላይ አምላክነትን የሚጋሩ የሆኑ ማንነቶች ቢኖሩ ኖሮ የሚናገሩት፦ ""ላ ኢላሃ ኢልላ ሁም" لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُمْ "ከእነርሱ በቀር አምላክ የለም" የሚል ነበር፤ ነገር ግን ነብያት ሁሌም በሶስተኛ መደብ ሲያናገሩለት፦"ከእርሱ በቀር አምላክ የለም" ብለው ነው፦
7:158 በላቸው፦እላንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደሁላችሁም የአላህ መልክተኛ ነኝ፤ እርሱም ያ የሰማይና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነ ነው፤ "እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም" لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُو