ተረት ተረት
አንበሳ ቀበሮን ጠራና "በጣም ርቦኛል የምበላው ነገር አምጣልኝ፣አለበለዚያ አንተን እበለሀለሁ" ይለዋል። ቀበሮ አህያ ጋር ሄደና " ወንድሜ አህያ፣ እንኳን ደስ አለህ! አያ አንበሳ በእንስሳት ሁሉ ላይ ሊያነግስህ ይፈልጋል ቶሎ እንሂድ" አለው። አህያ ከአመዱ ላይ ዘሎ ተነሳና ተያይዘው መንገድ ጀመሩ። እንደደረሱ አንበሳ ተስገብግቦ የአህያውን ጆሮ ገነጠለው። ንግስና አስቦ የሄደው አህያ በገጠመው አደጋ ደንግጦ የሞት ሞቱን ተፈተለከ። ከዛ የሮጠ ቤቱ ደርሶ እንደተቀመጠ ቀበሮ እያለከለከ ደረሰና "ምን ነካህ አንተ ጅል?! " ይለዋል።
"እንዴ ጆሮየን ገነጠለውኮ፤ ሊበላኝ ነበ፤ በሰላም ላንግስህ ብሎ ጠርቶ ...."
"አይ አህያ ደደብ ነህ ሲሉ ሀሜት ይመስለኝ ነበር...አያ አንበሳ ለንግስና ዘውድ ሲጭንልህ ይሄ ከርፋፋ ጆሮህ ዘውዱን ስለማያስገባው በቅድሚያ ጆሮህን ለማስተካከል ነበርኮ ጆሮህን የቆረጠው፤ ጆሮ ያለው ንጉስ አይተህ ታውቃለህ? አንበሳ ምን አጥቶ ነው የአንተን ጆሮ የሚበላው?
አህያ ባለአዋቂነቱ እያፈረ ቀበሮን ተከትሎ ወደንግስና ቦታው አዘገሙ።