የትምህርት ዘርፍ ምርጫ | Department Selection.
ውድ የ ቀለሜ ቤተሰቦቻችን እንደምን አላችሁ! የትምህርት ዘርፍ ምርጫ እጅግ ማሰብ የሚጠይቅ እና ቁርጠኛ የሆነ ውሳኔ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፤ ስለዚህ በጥንቃቄ እና በትጋት እንድታስቡበት እመክራለሁ።
በመጀመሪያ፣ የራሳችሁን ፍላጎት፣ ችሎታ እና አቅም በጥልቀት አስቡበት........። ምን አይነት ነገር ነው በእውነት የሚስባችሁ? ምን አይነት ስራ ነው ለመስራት የምትፈልጉት? በየትኛው ዘርፍ ውስጥ ነው ራሳችሁን ከሆኑ ዓመታት በኋላ ማግኘት የምትፈልጉት?
የራሳችሁን ፍላጎት ከመረጣችሁ በኋላ፣ በዚያ የትምህርት መስክ ልታገኟቸው የምትችሏቸውን የወደፊቱን እድሎች እንዲሁም ሊያጋጥሟችሁ የሚችሉትን ፈተናዎች ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው።
የመረጣችሁት መስክ በአሁኑ ጊዜ እና በወደፊት ጊዜ ምን ያህል ተፈላጊ እንደሆነም አስቡበት። እንዲሁም Business ተኮር ከሆነ አሁን ላይ ያለውን የስራ ገበያውን ሁኔታ እና እድገትን መመርመር ይጠቅማል።
ከላይ የተነሱትን ጉዳዩች አጢናችሁ ፍላጎታችሁን ከመረጣችሁ በኋላ ከቤተሰብ እና ከቅርብ ጓደኞች ጋር መግባት በምትፈልጉት የትምህርት ዘርፍ ዙሪያ መነጋገር እና ምክራቸውን መጠየቅ አሪፍ ነው...አሪፍ ነው....... ነገር ግን በመጨረሻ ውሳኔው የእናንተ መሆን እንዳለበት አትዘንጉ።
ፍላጎታችሁ እቅዳችሁ ዓላማችሁ የእናንተ ህልም ነው፣ የእናንተን ህልም ሊያዳምጧችሁ ይችላል ነገር ግን ማንም በምንም መልኩ አይረዳችሁም። ህልማችሁ ተራ ሊመስል ይችላል ምክንያቱም ህልም ነው፣ በመጨረሻ ግን የእናንተ ህልም ፍሬ አፍርቶ የሚታይ የሚጨበጥ ነገር ማንጠባረቅ ሲጀምር ያኔ ዓላማችሁ ህልማችሁ የእውነትም የከበረ እንደነበር ሁሉም ይረዳችኋል።
ስለዚህ የምትመርጡት ዘርፍ ምንም ይሁን ምን እናንተ ካመናችሁበት እና በትጋት፣ በቁርጠኝነት እና በጽናት የምትሰሩበት ከሆነ ስኬታማ መሆናችሁን እርግጠኛ ሁኑ።
ውሳኔ በራሳችሁ ወስኑ፣ መቸም አትቆጩበትም!
#friend_advice , #from_my_experience
👍 @keleme_2013