ግጥም 🇪🇹


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ ግጥም እና የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።🙏🙏🙏
👏👏👏👏👏👏
ግጥሞቻችሁን ለመላክ እንዲሁም
ለአስተያየት ይችን ይጠቀሙ @kidus15👍
ግሩፓችንን ይቀላቀሉ @kidapoimgroups

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ
✍️✍️✍️

እኛ ያንተ ጥበብ
እጅ ስራዎችህ የዋህ ቅን ደጋጎች
###
የሚመጣው ሁሉ
እንዳሻው ሚመራን የእረኛችን በጎች
###
ሀገር እያለችን
ሀገር ለናፈቀን ምንኖር በስጋት
####
የስደትን ገፈት
የረሀብን ፅዋ መራራ ምንጋት
###
ባለቀን ሹመኛው
ሲገፋን ሲጋፋ ለንግስናው መንበር
###
በጊዜ መነፅር
መስኮት እያሳዩን የምናውቀውን በር
###
ለተቀማጭ ሁሉ
የኛ ሩቅ ሰማይ እየቀረባቸው
###
ተረት እንቆቅልህ
ተስፋ ብቻ ቢሆን ወትሮም ቀለባቸው
###
ሙሴን በመናፈቅ
ሸክላ ሰሪ ሁነን እየበላን በገል
###
ከፈርኦን ሀሳብ
ሮጠን ለማምለጥ ደርሶ ምንታገል
###
እሺ ከማለት ውጭ
አማራጭ ያጣን ህዝብ ሁሌ እያስቀሱን
###
የተወጋ ይሁን ወይም ያልተወጋ
ግራ ለተጋባን ምን እንዳቀመሱን
###
ከመንገድ አጋማሽ
መመለስ ርቆን መሄድ ስለፈራን
###
እንደ ሰብአ ሰገል
የዳዊትን ኮከብ ላከው እንዲመራን


ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ
✍️✍️✍️✍️

ግጥም ጥሞሽ
""""""""""
የሆነ ጊዜ ላይ
የዘነበው ዝናብ
በላዬ ላይ ሲወርድ
እግሬ አውጪኝ አልኩና
ወደ ቤቴ መጣው
###
የረጠበ ልብሴን
ውልቅልቅ አድርጌ
ድንገት ውጥት ስል
ገመድ ላይ ላሰጣው
###
ገመድ አልነበረም,,,,,,
የት ገባ እያልኩኝ
አለመጠለሌ
ዳርጎኝ እንድፀፀት
###
ጆሮዬ ሹክ ሲል
ደጋግሞ ተሰማኝ
የሚያቃስት ድምፀት
###
በድርጊቴ ሁሉ
እየተበሳጨው
ስራገመው ቀኔን
###
አንዲት ጎረቤቴ
መታነቋን ተወች
ብታየኝ እርቃኔን
####
ታዲያ በዚህ መሀል
ገርሞን ተሳስቀን
ተግባብተን የዛን ቀን
ዙሩን አከረርን
###
ከመግባባት በላይ
ከመዋደድ አልፎ
በጣም ተፋቀርን
###
ያ,ሁሉ ቢሆንም
እኔ ግን ጨነቀኝ
ሰጋሁኝ ይልቅስ
###
ከኔ ስትጣላ
ኮሽ ባለ ቁጥር
ቆይ ብትታነቅስ
###
ብዬ ስለሰጋው
###
የከፈትኩላትን
የልቤን መግቢያ በር
ቶሎ ብዬ ዘጋው


ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ
@@@

እግዜር ቁራና ሰው
✍️✍️✍️✍️

በሰለለ ዋይታ በሚያላዝን ድምፀት
በዛ ቁጣ ዘመን ድርቁ ባየለበት
####
ጠኔ ያጠነናት
አቅም የጣች ህፃን ከትቢያ ላይ ወድቃ
ድረሱልኝ በሚል ከሞት ጋር ተናንቃ
###
ቀድሞ እያስተጋባ ልክ እንደ ማሚቱ
የኮሽታው ደወል ያነቃው ድምፀቱ
###
አልሾምከኝ በላቤ አላጭድ አልዘራ
ፀንተህ የምትቀልብ እልፍ እውር አሞራ
በጨቅላዋ ህልፈት የኔን ህይወት ዝራ!
###
እያለ ሚለምን,,,
የራበው ጥምብ አንሳ ከዳተኛ ቁራ
###
ሌላው የሰው ፍጡር
ትዕይንቱን ለመቅረፅ ደቅኖ ካሜራ
###
አየው አንድ ምስል
ውስጥን ሚያብሰለስል
####
ጥምብ አንሳው ለሆዱ
ህፃኗም ለነፍሷ ፎቶ አንሺው ለዝና
ርሀቧን ጉርስ አርጎ በንዋይ ሊሸጠው
###
እኔ ምልህ እግዜር
ባምሳልህ አንፀህ ሰውን ከፈጠርከው
###
በውሃ ሙላት ዘመን የከዳውን ቁራ
ከታመነህ ሰው ዘንድ በምን አምነህ ላከው?

😪😪😪😪😪

ልንጋ ያለች ምድር (ያሬዳዊ ግጥም) ከሚለው መድብል ላይ የተወሰደ






ያሬዳዊ ግጥም ) ያሬድ ከበደ
&&&&
ያአምላክ ፍቅር
@@@@

ቃል ስጋ ሆነና ስጋን ቃል ለበሰው
ሰው አምላክ ተባለ አምላክም እንደ ሰው
###
አልፋና ኦሜጋ ጥበብ መጀመሪያው
ፍፁም ቃል ነበረ መለኮት ማደሪያው
####
በትምህርተ መስቀል





መውረዱን

በድንግል ማህፀን
በረት መወለዱን
###
ትዕግስትን ተችሮት
ፍቅር ሊያስተምረን
ፅናቱን ሲታደል
####
አንዱ ባለ ቅኔ
ተቀኘ ሶስት ፊደል
###
ከተቀኘው ጥበብ
ለመፍታት ቋጠሮ
####
ፈጣሪ ከፍጡር
ያዘና ቀጠሮ
###
ትምቢቱን ሊፈፅም
ሰዓት ቀን ቆረጠ
####
ቀራንዮ ምድር
ቦታውን መረጠ
###
ከዲያቢሎስ ግዞት
ነፃ እንድንወጣ
###
ፍቅርን ሰንቆ
በምሳሌ መጣ
###
አሁን ለምሳሌ
በማያልፈው ቃሌ
####
መንገድና ህይወት
እውነት እኔ ነኝ ሲል
በቅዱስ ወንጌል ላይ
####
አምላክ በፈቃዱ
መከራን ሊቀበል
ተገኝቷል አርብ ላይ
####
ያቺ አርብ የሚሏት
ለመከራ ጭንቁ
ለኛ ግን ድህነት
ምሳሌ ቢያደርጋት
####
ለጥሙ መቁረጫ
መራራውን ቢጋት
####
በጅራፍ ተገርፎ
ሲውል በመስቀሉ
###
ዓለም ሁሉ ዳነ





ቃሉ


ያሬድ ከበደ (ያሬዳዊ ግጥም)
""""'"""""""""
እኔ'ና ጨረቃ
""""""""""""""
ከዕለታት ባንድ ዕለት
ብሩህ ማለዳዬ ሳትፈካ በቅጡ
"""""""""'""""""'
ፀሐይ ከነ ልጇ
መፈክር አንግበው ባንድነት ሳይወጡ
""""""""""""""""""
እምብርቷ ላይ ቆሜ
የምድርን አፅናፍ ስመትር ስለካው
"""""""""""""""""""
ሰማይን ሸንቁራ
የምትወጣው ጨረር ድንገት ልቤን ማርካው
""""""""""""""""""""
ከምርኮዋም በላይ
ውበት ነፀብራቋ ፍቅሯ ቢያሳውረኝ
""""""""""""""
ለመንገዴ መሪ
ምርኩዟን ተዉሼ ማዶ እንዲያሻግረኝ
""""""""'""""""""""""
በሩቅ ብስራት ስንቄ
ጭላንጭሉ ተስፋ ገፎ እስኪታያቸዉ
"""""'""""""'""""""
በሷ መሰቃየት
ልክ እንደ ሱስ ልማድ አመል ሆኖባቸዉ
""""""""""""""""""
ከሰዋራ ልቧ
ተቆልፈዉ ሳሉ ያይኖቼ ቆብ መቃን
"""""‘""""""""""""
ጨለማን ጠብቀዉ
ይከፈቱ ነበር ለማየት ጨረቃን




ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ
###
እማምላክ
✍️✍️✍️✍️

ማን ይታደለዋል
ምድሩን ሳይጨርስ እንኳን አርያምን
,,,,,,,,
የትኛውስ ጠቢብ
አምብቦ ተረዳ ተአምረ ማርያምን
""""
ብራና እንደ ሰማይ ተዘርግቶ ቢታይ
ላማላጅነትሽ ኪዳን ምህረትሽ
""""
በምንስ ሊከተብ ከቶ እንዴት በምን ቃል
""""""""""""""
የደግነትሽ ጫፍ
በቅጡ ሳይፃፍ

ውቅያኖስ ተሟጦ
ባህር ሙሉ ቀለም በደቂቃ ያልቃል




ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ

እንዳትቀየሚኝ
###

ብቅሉ ሲበቅል
ጌሾ ሲቀረጠፍ
###
ጀምበሯን አጥልቀሽ
በጨረቃዋ ጠፍ
###
የዛሬን አያርገው
ቢያልፍም ትናንትና
###
እንደዋዛ ቢቀር
የኛ ጉርብትና
###
እንዳትቀየሚኝ,,,,,,

ብትቀየሚኝም
ከድፍድፍ ጥንስስሽ
ክጠላሽ መራቄን
#####
እንኳን አንቺን ቀርቶ
ምንም ቢቀጥን ጠጅ
አይብልጥም አረቄን




ከኖረ ሰው እኩል
ምነው መጣ ሞት
አንተን ሲወስድህ
ይህ እኮ ነው አግርሞት
ቀመሱልህ ንፍሮ
በሉልህ ጣፍጧቸው
ነብስ ይማር ይላሉ
የሞትኩት እኔ ምን ተዳቸው
አቤሌ ተንገበገብኩልህ
እናትህ ተቃጠልኩ
እንዲህ እንደዘበት የመሄድህን ነገር
እኔ በምን አሰብኩ
መች ሰለቸኝ ልጄ እድሜ ልኬን ብሆን
ከእናት አልፎ ባሪያ
ምነው ባስታመምኩህ ከማጣህ በሞቴ
ከአይኖቼ ዙሪያ
ልጄ ሆይ በጡቶቼ አድባር
እንደው ልለምንህ
ቀና በል ተነሳ አለኝ የምነግርህ
እንደው እግዜሩ ሆይ
ማነው ያማከረህ
የኔን ብላቴና በየትኛው አይንህ
ኧረ ማን አሳየህ
መቼ ጠገበ እንደባልጀራ
እሮጦ ሳይጨርስ
እንዲህ ለመሆን
መፈጠር ቢቀርስ

አቤሌ ስማኝ እንጂ ልጄ በል ተነስ ተነስ ተነስ.........

✍️የአብ........


ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ

መንቶ

*
ሼሁም ቆቡን ደፋ የእምነት አባት ቄሱም
መስቀሉን አንግቦ ሻሹን ሲጠመጥም
*
ሙስሊም ክርስትያኑ ፆማቸው ሲገጥም
**
ከመስጅዱ ቅጥር ከበተስኪያን አፀድ
አሀዱ ቅዳሴ ማልዶ ሲባል አዛን
****
የፍቅርን ማዕድ ተቋድሰን ባንድነት
አላህም እግዜር ነው የሚል ቃል ሲገዛን
**
የተሰቀለውን ህማሙን ለማሰብ
አርብ የሚሏት ግብዣ ስታቀጣጥረን
****
እንደየ እምነታችን ስንለማመነው 
በፆም በስግደቱ ባንድነት አፍጥረን
*
ዱአ ፀሎታችን ካምላክ ዘንድ ቀርባ
ለልባችን መሻት ፍቅር አስተምራን
**
     በዥንጉርጉር ዓለም
####
አንድ እውነት አግባብቶን
እኩል  ይሰበካል ወንጌልና ቁራን


ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ
★★★
ጿሚውን ለይልን

★★★

እኛ አገልጋይህ
ያንተ ደቀ መዝሙር የምንኖር በቃል
★★★
ይኸው ለቅበላ
ገዝተን እንዳንበላ ስጋ ማልዶ ያልቃል
★★★
አየህልኝ አይደል
እንደ ተቃውሞ ሰልፍ የነዳጅ ወረፋ
★★★
ከሚፆመው ይልቅ
የማይፆመው በልጦ ሰልፍ ላይ ሲጋፋ
★★★
እኛ ያንተ ጥበብ
የወንጌልህን ምንጭ ሌተቀን ምንጋት
★★★
ከበተስኪያን አፀድ
አምነን ምንመራ በሙሴ ህግጋት
★★★
ካውደ ምህረት ቆመን
ታቦት ተሸክመን
*
ህዝብና ርስትህን
ባርክልን እያልን እምባ የምናፈስ
★★★
ሰው በምግብ ብቻ
እንደማይኖር አውቀን ብንሞላም መንፈስ
★★★
መቼም ሰው ነንና
ከኛ ማይጠበቅ ቢሆንም ስራችን
★★★
በስጋ ተማርኮ
ስለተሸነፈ ፈራሹ ገላችን
★★★
ያየም የተመኘ
እኩሌታ ፍርዱ እዳያስቀስፈን
★★★
ዐቢይን ከማይፆም
ጿሚውን ለይና ከፊት አሰልፈን


(ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ

የሴቶች ቀን

ቢከፋም ቢለማም
**
ሀገር እያለችን ሀገር ለናፈቀን
ስጋት ላደረብን መኖር ለጨነቀን
*
የባንዳራው ቀለም የእናት መቀነት ነው
ተብላ ከተጠራች ሀገር በሴት አምሳል
**
የሴቶች ቀን ተብሎ
ባመት አንዴ ብቻ ለምን ይወደሳል?


ያሬድ ከበደ
(ያሬዳዊ ግጥም)

✍️✍️ ✍️✍️

ሰው ይምሰለው እንጂ
ፈጣሪ ሳይደግስ ከቶ መች ይጣላል
****
ለምታጣጥር ነፍስ
እስትንፋስን ዘርቶ ህይወት ይቀጥላል
**
ሁሌም ትክክል ነው
ይፈርዳል ይምራል መሳትን አያውቅም
**
ይሁን ካለው ቀድሞ
ንጋት ሳያበስር ጀምበር አያጠልቅም

✍️✍️✍️✍️✍️
መልካም ቀን


Репост из: Неизвестно


ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ

ያልተነገረለት

★★★
ባክሱም ራስ ጥበብ
እንደ ሮሃ አለት ቀርፆን በራሱ ልክ
★★★
ድምበር አሻጋሪው
ነፃ አውጪው ሙሴያችን እምዬ ምኒልክ
★★★
ለእናት ሀገር ፍቅር
ከላይ በተቸረው ብርቱ ጥንካሬ
★★★
ያንገቱን ማህተብ
ልቡ ላይ አትሞ የእምነት ቃል ፉካሬ
★★★
ጥንት አባቶቻችን
የከፈሉት ዋጋ የተቀዳጁት ድል
ወስዶኝ ወደ ትናንት
★★★
በድል የተፃፈ
ቱባ ታሪክ ነበር ያለፉት ዘመናት
★★★
ድል አድራጊው ጀግና
በደል እንዳይቆየን ብርቱ ፀፀት ተርፋን
★★★
ነጭ የበላይነት
ያልነገሰበትን አወረሰን ዙፋን
★★★
ከንግስናው በላይ
ከዙፋኑ ግርጌ አንድነት የዘራው
★★★
ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ
ወገን እንዳይጠፋ ሞቶ ለባንዲራው
★★★
በደምና ባጥንት
መሰረት የጣለ የአፍሪካ ቀንዲል
★★★
ለጥቁር ህዝብ ታግሎ
ከባርነት ግዞት ካንገቱ ቀና እንዲል
★★★
ዛሬም ነገም አልፎ
ልክ እንደ ትላንቱ ታሪክ እንዲወሳ
★★★
ቅኔው ሲፈታለት
ብድር መላሽ አርጎት ዉለታ እንዳይረሳ
★★★
ህያው ፅኑ እምነትህ
ያላመነ ልቡን በፀሎት አግዛው
★★★
ማርያምን ነው ምልህ
የዛሬውን ትውልድ ዳግም አንተ ግዛው

Показано 20 последних публикаций.

4 296

подписчиков
Статистика канала