⚖Ethiopian law by Daniel Fikadu Law office⚖


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Право


ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ
ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559
Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia.
Email- nurotekore@gmail. Com
⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Право
Статистика
Фильтр публикаций


Hof on remarriage.pdf
906.6Кб
The House of Federation Decision, on June 25, 2016, in its decision No. 804/16, overturned the decision of the Federal Supreme Court Appeals Chamber in Case file No. 23021..... ruled that if a couple reconciles after divorce, they must remarry Again!!!


Репост из: Ethiopian Law
fsc-cassation-2014-15-short-sumarrys.pdf
3.5Мб
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በ2014/15 ዓ.ም. የተሰጡ አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች በአጭሩ ተመርጠው የተዘጋጁ / ሙሉ መፅሃፍ/     
                            
በዳንኤል ፍቃዱ (ጠበቃና የህግ አማካሪ)


Репост из: Ethiopian Legal insight
የሕግ ስራዎትን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድግልዎ እንዲሁም ዘመናዊ አሰራር ይዞ ቀልጣፋ አገልግሎት የሚያገኙበትን አፕሊኬሽንና ሶፍትዌር ከኢትዮጵያን ሌጋልቴክ ቀረበልዎ !

በኢትዮጵያ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ የቀረበው ሌጋልቴክ በሞባይል መተግበሪያ አማራጭ ቀርቧል
ይህ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ዲጅታል የሕግ ላይብራሪና ኬዝ ማኔጅመንት ሲስተም ለሁሉም የሕግ ባለሙያዎች ፣ ለሕግ ተማሪዎች ፣ ለነጋዴዎችና ለቢዝነስ ተቋማት ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።

ተመጣጣኝ በሆነ የአገልግሎት ክፍያ ይህን ፈርቀዳጅ አገልግሎት መጠቀም ይችላሉ !

የህግ ባለሙያዎች በግራና በቀኝ ተከራካሪ ወገኖች መካከል ያሉ ጉዳዮችን ለመከታተል እንዲሁም የሕግ ተግባራትን ለማስፈር ቀጠሮዎቻቸውን ለማስፈርና ለመከታተል  በኢትዮጵያ ካሌንደር በተዘጋጀው ስማርት አጀንዳ መከታተል ይችላሉ

በኢሜይል አድራሻዎት በቀላሉ በመመዝገብ የዚህን ሶፍትዌር ማራኪ ገፅታዎች ይሞክሩ
ፕሌይ ስቶር በመግባት ሌጋልቴክ/LegalTech ብላችሁ በቀላሉ በመፈለግ ማውረድና መመዝገብ ትችላላችሁ !
አፕሊኬሽኑን ለማውረድ በዚህ ሊንክ ግቡ   👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ethiopianlegaltech.eli
www.ethiopianlegaltech.com በሚለው የዌብሳይት አድራሻ መግባትና መመዝገብም ትችላላችሁ
ፈር ቀዳጅ የሆነውን ይህን ዲጂታል የሕግ ሶፍትዌር እንዴት በተሟላ ሁኔታ መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳዩ የቪዲዮ ማሳያ ቱቶሪያሎች አዘጋጅተን በዩትዩብ ቻናላችን
አስቀምጠናል
ሊንኩ ከታች ይገኛል
https://youtube.com/@ethiopianlegaltech
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Ethiopianlegalinsight


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ለ8ኛ ጊዜ የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ እና ምዝገባ ስራ ሊያከናውን ነው

👉የይዞታ ማረጋገጫ ከታህሳስ 10-ሚያዚያ 15 ይከናወናል ብሏል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ግፋ ወሰን ደሲሳ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ኤጀንሲው ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ከጀመረበት 2007 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2016  በጀት ዓመት ድረስ 7 ጊዜ የይዞታ ማረጋገጥ እወጃ በማካሄድ በ 337 ቀጠናዎች ላይ የማረጋገጥ ስራ ማከናወኑን ተናግረዋል  ፡፡

በዚህ መሰረት በያዝነዉ በጀት  አመት  ለመጨረሻ ጊዜ  ለስምንተኛ ዙር  ቀሪ  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉትን ያልተረጋገጡ  136 ቀጠናዎች   የሚገኙ ቁራሽ መሬቶችን   አረጋግጦ ለመመዝገብ  ዝግጅቱን  በማጠናቀቅ  ዛሬ ታህሳስ 10/4/2017 ዓ.ም እወጃ ማካሄዱን ገልፀዋል ፡፡

የይዞታ ማረጋገጡ ስራ በተመረጡ ስድስት  ክፍለ ከተሞች ማለትም የካ ክፍለ ከተማ( በወረዳ  ወረዳ1፤2፤ 3፤9፤10፤11፤12  በ 25 ቀጠናዎች   በለሚ ኩራ በወረዳ 2፣3፤4፤5፤6፤9፤10፣ 13 እና 14 በ 44 ቀጠናዎች፤ አቃቂ ቃሊቲ  ክፍለ ከተማ  ወረዳ 1፣2፣3፣4፤6፣ 9፣13   በ 19 ቀጠናዎች ንፋስ ስልክ ላፍቶ በወረዳ 6 ፣7፣8፤9፤10፣11፣14 የሚገኙ  በ 22 ቀጠናዎች  ቦሌ በ ወረዳ 11፡12፤13  በ 15 ቀጠናዎች   ኮልፌ ቀራኒዮ  በወረዳ 3፤11   በ 11 ቀጠናዎች አጠቃላይ  በ 136 ቀጠናዎች (በ 467 ሰፈሮች)  ያልተረጋገጡ ይዞታዎችን የማረጋገጡ ስራ  በስልታዊ ዘዴ / በመደዳ /  የማረጋገጥ ስራ የሚከናወን  ሲሆን ስራውም ከ ታህሳስ 10/04/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ወራት ውስጥ እስከ  ሚያዝያ 15 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ሙሉ ወጪውም በመንግስት እንደሚሸፈን ተናግረዋል፡፡
ኤጀንሲው አረጋግጦ ላልመዘገበው ይዞታ ምንም ዓይነት ህጋዊ ዋስትናና ከለላ የማይሰጥ መሆኑን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ባለይዞታዎች ከታህሳስ 20/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስፈላጊውን መረጃ ይዘው የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንድታቀርቡ በድጋሜ አሳስበዋል፡፡

ኤጀንሲው የይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ከጀመረበት 2007 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ 7 ጊዜ የይዞታ ማረጋገጥ እወጃ በማካሄድ በ337 ቀጠናዎች ላይ የማረጋገጥ ሥራ ተካሂዷል፡፡ በዚህም በቁራሽ መሬት 219 ሺ 722፣ በጋራ መኖሪያ ቤት 173 ሺ 136 በመብት 400 ሺ 84 ይዞታዎች ላይ የይዞታ ማረጋገጥ ሥራ በመስራት የአዲስ አበባን ከጠቅላላው የቆዳ ስፋት 54% መሸፈኑ ይታወቃል፡፡


የመንግስት ግዥ ውል ተፈጸመ የሚባለው መቼ ነው? ሰ/መ/ቁጥር 193392

#Daniel Fikadu Law Office

የአስተዳደር የግዥ ውል ተቋቋመ ሊባል የሚችለው የጨረታው አሸናፊ በደብዳቤ አሳውቆ አሸናፊው ጥሪውን ተቀብሎ በመቅረቡ ብቻ ሳይሆን በግዥ ሕግጋገቱ በተመለከተው አግባብ ከተዋዋዮች የሚጠበቀው ተሟልቶ የውሉ ጉዳይ በሚገባ አኳኋን ተጽፎ
በመንግስት መስሪያ ቤቱና በጨረታው አሸናፊ ሲፈረም ብቻ ነው ።
በመንግስት ግዥ ሕግጋት በተመለከተው አግባብ እና በፍ/ብ/ሕግ
ቁጥር 3167 እና 3168 ስር በተደነገገው መሰረት ከጨረታው አሸናፊ ጋር የግዥ ውል ከመፈራረሙበፊት ጨረታውን የመሰረዝ ሙሉ ነጻነት አለው።


የህክምና አገልግሎት ክፍያ ከመጠን በላይ ከተጋነነ ህግ ምን መፍትሄ ይሰጠናል?
ዳንኤል ፍቃዱ ( ጠበቃ ፣ የህግ አማካሪ እና መምህር )

የህክምና ሙያ ለህብረተሰቡ ከሚሰጠው ጥቅም፣ ሙያውን ለማግኘት እና ለማዳበር ካለው ከፍተኛ የሆነ ልፋት፣ እንዲሁም ከምንም በላይ የሆነውን የሰውን ልጅ ህይወት በማትረፍ ላይ የተሰማራ ሙያ እንደመሆኑ፤ለምናገኘው አገልግሎት ምንም ቢከፈል ያንስበት እንደሆነ እንጂ አይበዛበትም፡፡

ሆኖም ግን ማንኛውም አገልግሎት የራሱ የሆነ የመግዣ ዋጋ ( Monitory value ) ያለው መሆኑ እና በዛ ተመን መሰረት አገልግሎቱ መሰጠቱ እንዲሁም እንደ አገልግሎቱ ስፋት እና ጥራት አይነት ክፍያ መፈጸሙ ተገቢ እና በልምድ የዳበረም አሰራር ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ከፍተኛ የሆነ የህክምና ባለሙያ እጥረት ባለባቸው ሀገራት ደግሞ የተጠየቁትን በዝምታ ከፍሎ አገልግሎቱን ለማግኘት መሞከር እየተለመደ ያለ ተግባር ቢሆንም ለሙያቸው ክብር በማይሰጡ እና የገናዘብ ጥቅማቸውን ብቻ በሚያሳድዱ የህክምና ባለሚያዋች እና ተቋማት እየበረከቱ እንደመጡ ሁሉም የሚታዘበው ሃቅ ነው፡፡

ለመሆኑ የኢትዮጵያ ህግ ከመጠን በላ ለሆነ እና ለተጋነነ የህክምና አገልግሎት መጠየቅን በተመለከተ የሚለው ነገር አለ???

ህግ ማንም ሰው ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ጉዳት ላይ እንዳወድቅ ጥበቃ የሚያደርግ መሳሪያ ነው፡፡ የህግ ስርአቱም ይህን መሳሪ በመጠቀም ለህብረተሰቡ ተገቢውን ጥበቃ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ህግ የወረቀት ላይ ነብር ( soft law ) ብቻ ሆኖ ይቀራል፡፡ወደተነሳንበት ጭብጥ ስንመለስም የህክምና አገልግሎትን በተመለከተም ህብረተሰቡ መማረር ከጀመረ ቢሰነባብትም በተለያዩ ምክንቶች ግን ቅሬታው መፍትሄ ሊያገን አልቻለም፡፡ ዋነው ምክንያቱ ደግሞ የግንዛቤ እጥረት ነው ብሎ ፀሀፊው ስለሚያምን ይህን ፅሁፍ ለማዘጋጀት ተሞክሮዋል፡፡እርግጥ የነፃ ኢኮኖሚ ( free market ) ወይም የቅልቅል ኢኮኖሚ ( mixed market system) ተከታ የሆኑ ሀገሮች በሚሰጡ አገልግሎቶች እና በሚሸጡ እቃዋች ላይ በጠቅላላው ወይም በተወሰነ መልኩ የዋጋ ታሪፍ የማውጣት ስርአትን ባይከተሉም፤ዜጎቻቸውን በጣም ከተጋነነ የአገልግሎት እና የእቃ ዋጋ የሚጠብቁበት ስርአት ግን ያበጃሉ ፡፡( የኛ ሀገር ነገር እሳቤውም ተግባሩም ግራ ቢሆንም )

ወደ ህጉ ስንመጣ አዋጅ ቁጥር 1/1952 ወይም በተለምዶ የፍታብሄር ህጉ ቁጥር 2646 ላይ ለህክምና አገልግሎት የሚከፈል ዋጋንበተመለከተ ድንጋጌዋችን አስቀምጧል፡፡ ድንጋጌው ለሃኪም ሊከፈለው የሚገባውን ክፍያ እና ለሆፒታሉ ( መስሪያ ቤቱ ) የሚከፈል ዋጋ በውል ተዋዋይ ወገኖች ( የህክምና አገልግሎት ሰጪው እና ተቀባዩ ) እንዲወስኑ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ሆኖም ዋጋው በውሉ ላይ ሳይገለጽ ከቀረ በልማድ መሰረት ማለትም በአካባቢው ለተመሳሳይ አገልግሎት በሚጠየቀው ክፍያ ልክ እንደሚወሰን ህጉ አማራጭ ይሰጣል፡፡

ወደተነሳንበት መሰረታዊ ሀሳብ ወደሚወስደን ሀሳብን ደግሞ የምናገኘውበአንቀጹ ንኡስ አንቀጽ 3 ስር በሚገኘው ድንጋጌ ነው፡፡ ከላይ በንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 ላይ ከተቀመጡት አማራጮች እንዲከፍል የተባለው ዋጋ ወይም ገንዘብ ከመጠን በላይ ሆኖ ከህክምና ሙያ ክብር ተቃራኒ ሲሆን ዳኞች ዋጋውን ሊያሻሽሉ እንደሚችሉ ህጉ መብት ይሰጣቸዋል፡፡ ስለዚህ ዳኞች( ክስ ሲቀርብላቸው ) ውሉን ወይም ልምዱን በመመልከት ተገልጋዮ ( ታካሚው ) ላይ እንዲከፍል የተጣለበት ገንዘብ የተጋነነ ( ከመጠን በላይ ) ነው ብለው ካሰቡ እና ለህክምና ሙያ ክብር ( የተከበረውን ሙያ ተራ የገንዘብ ማግኛ ወደማድረግ ከተለወጠ ) ዋጋውን ሊያሻሽሉት ይችላሉ፡፡ስለዚህ አንድ ታካሚ ካገኘው አገልግሎት በላይ በጣም የተጋነነ የአገልግሎት ዋጋ ከተጠየቀ በፍርድ ቤት ክስ መስርቶ ከመጠን በላይ የሆነ የህክምና ዐገልግሎት መጠየቁን በማስረጃ በማስረዳት ተገቢውን ብቻ ዋጋ እንዲከፍል በፍርድ ቤቱ ሊወሰንለት ይችላል፡፡የፍርድ ቤት ዳኛ ደግሞ የተሰጠውን የህክምና አገልግሎት ከተጠየቀው ዋጋ ጋር በማገናዘብ በርትዕ ሊሻሻል ይችላል፡፡/ በድጋሚ የተለጠፈ/


Репост из: Ethiopian Legal insight
በኢትዮጵያ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ የቀረበው ሌጋልቴክ በሞባይል መተግበሪያ አማራጭ ቀርቧል
ፕሌይ ስቶር በመግባት ሌጋልቴክ/LegalTech ብላችሁ በቀላሉ በመፈለግ ማውረድና መመዝገብ ትችላላችሁ !
አፕሊኬሽኑን ለማውረድ በዚህ ሊንክ ግቡ 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ethiopianlegaltech.eli
ይህ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ዲጅታል የሕግ ላይብራሪና ኬዝ ማኔጅመንት ሲስተም ለሁሉም የሕግ ባለሙያዎች ፣ ለሕግ ተማሪዎች ፣ ለነጋዴዎችና ለቢዝነስ ተቋማት ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።
www.ethiopianlegaltech.com በሚለው አድራሻ መግባትና መመዝገብ ትችላላችሁ
#share #lawyer #legalsupport #legaladvice
#ethiopianlaw #legalcounsel #legalhelp
#ህግ #የህግምክር #የኢትዮጵያ #Legaltech

ፈር ቀዳጅ የሆነውን ይህን ዲጂታል የሕግ ሶፍትዌር እንዴት በተሟላ ሁኔታ መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳዩ የቪዲዮ ማሳያ ቱቶሪያሎች አዘጋጅተን በዩትዩብ ቻናላችን
አስቀምጠናል
ሊንኩ ከታች ይገኛል
https://youtube.com/@ethiopianlegaltech
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Ethiopianlegalinsight


በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍቺ እና የጉዲፈቻ ውሳኔዎች ምዝገባ ተጀመረ፡፡
******************************************************************
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በፍርድ ቤት የሚወሰኑ የፍቺ እና ጉዲፈቻ ውሳኔዎችን የመመዝገብ አገልግሎት በአንድ ማዕከል ለመስጠት የሚያስችለውን የስራ ስምምነት ከፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋር ቀደም ብሎ ስምምነት መፈጸሙ ይታወቃል፡፡ በስምምነቱ መሰረትም ዛሬ ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም በይፋ አገልግሎቱን በአራዳ እና ቦሌ ምድብ ችሎቶች መስጠት ጀምሯል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ፉዓድ ኪያር፣ የኢመደአ እና የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ስራ አሰኪያጅ አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል እንዲሁም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በአራዳ ምድብ ችሎት ተገኝተው መርሃ ግብሩን ያስጀመሩ ሲሆን የተቋማት ቅንጅት ለከተማው አገልግሎት መሻሻል እጅግ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው የምዝገባ ስርዓቱ ተደራሽ መሆን እንዲችል የተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮች በቅርቡ እንደሚተገበሩ ገልፀዋል። ዋና ስራ አስኪያጁ አያይዘውም አገልግሎት ፈላጊው የሚንገላታበትን አሰራር ማስወገድና አገልጋዩ ወደ ተገልጋዩ በመቅረብ የአገልግሎት ተደራሽነትንና የመረጃ ጥራትን መስጠበቅ ይኖርብናል ያሉ ሲሆን ይህን እውን ለማድረግ ደግሞ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡
የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉዓድ ኪያር በበኩላቸው ፍርድ ቤት ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥበት ተቋም በመሆኑ በተፈራረምነው ስምምነት መሰረት ወደ ስራ መገባቱ የአገልግሎቱን ጥራት የሚጨምር ነው ብለዋል፡፡ ክቡር አቶ ፉዓድ በንግግራቸው የጉዲፍቻ እና የፍቺ ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ በፌዴራል መጀመሪ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚያልቁ በመሆናቸው የምዝገባ ስርዓቱ መጀመር ለተቋማቱ ብቻም ሳይሆን ጥራት ያለው መረጃ በማደራጀት ለሀገርም የሚሰጠው ጠቀሜታ የጎላ ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከፍቺ እና ከጉዲፈቻ ምዝገባ በተጨማሪ የፋይዳ (ዲጂታል መታወቂያ) ምዝገባ በምድብ ችሎቶች የሚካሄድ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ገልጸዋል፡፡


Wallagga University Law journal vol.2.pdf
3.9Мб
Wallagga University Law Journal vol.2, 2024


Репост из: Ethiopian Legal insight
የሕግ ስራዎትን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድግልዎ እንዲሁም ዘመናዊ አሰራር ይዞ ቀልጣፋ አገልግሎት የሚያገኙበትን አፕሊኬሽንና ሶፍትዌር ከኢትዮጵያን ሌጋልቴክ ቀረበልዎ !

በኢትዮጵያ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ የቀረበው ሌጋልቴክ በሞባይል መተግበሪያ አማራጭ ቀርቧል
ይህ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ዲጅታል የሕግ ላይብራሪና ኬዝ ማኔጅመንት ሲስተም ለሁሉም የሕግ ባለሙያዎች ፣ ለሕግ ተማሪዎች ፣ ለነጋዴዎችና ለቢዝነስ ተቋማት ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።
የህግ ባለሙያዎች በግራና በቀኝ ተከራካሪ ወገኖች መካከል ያሉ ጉዳዮችን ለመከታተል እንዲሁም የሕግ ተግባራትን ለማስፈር ቀጠሮዎቻቸውን ለማስፈርና ለመከታተል በኢትዮጵያ ካሌንደር በተዘጋጀው ስማርት አጀንዳ መከታተል ይችላሉ

በኢሜይል አድራሻዎት በቀላሉ በመመዝገብ የዚህን ሶፍትዌር ማራኪ ገፅታዎች ይሞክሩ
ፕሌይ ስቶር በመግባት ሌጋልቴክ/LegalTech ብላችሁ በቀላሉ በመፈለግ ማውረድና መመዝገብ ትችላላችሁ !
አፕሊኬሽኑን ለማውረድ በዚህ ሊንክ ግቡ 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ethiopianlegaltech.eli
www.ethiopianlegaltech.com በሚለው የዌብሳይት አድራሻ መግባትና መመዝገብም ትችላላችሁ
ፈር ቀዳጅ የሆነውን ይህን ዲጂታል የሕግ ሶፍትዌር እንዴት በተሟላ ሁኔታ መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳዩ የቪዲዮ ማሳያ ቱቶሪያሎች አዘጋጅተን በዩትዩብ ቻናላችን
አስቀምጠናል
ሊንኩ ከታች ይገኛል
https://youtube.com/@ethiopianlegaltech
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Ethiopianlegalinsight
#share #lawyer
#ethiopianlaw #legalcounsel #Legaltech


book_2.pdf
20.7Мб
book_1.pdf
5.9Мб
INTERNATIONAL LAW HANDBOOK COLLECTION OF INSTRUMENTS


Репост из: Ethiopia Insider
የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል የተሰኘው ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት በድጋሚ ታገደ

በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተጣለበት እገዳ ባለፈው ሳምንት ተነስቶለት የነበረው የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በድጋሚ ታገደ።

ሀገር በቀሉ የሰብአዊ መብት ድርጅት የታገደው፤ በተሰጠው ማስጠንቀቂያ መሰረት “አሰራሩን ባለማስተካከሉ” እና “ከዚህ ቀደም የፈጸማቸውን ጥፋቶች በመቀጠሉ ነው” ሲል ባለስልጣኑ ወንጅሏል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፤ እነዚህን እና ሌሎችን ውንጀላዎችን ለድርጅቱ በጻፈው ደብዳቤ ላይ መግለጹን ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ፊርማ ያረፈበት ይህ ደብዳቤ የተጻፈው በትላንትናው ዕለት ቢሆንም፤ ለካርድ አመራሮች የደረሰው ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8፤ 2017 መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ገልጸዋል።

ደብዳቤው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በካርድ ላይ ባደረገው “የክትትል እና “የግምገማ ስራዎች”፤ ድርጅቱ ፈጽሟቸዋል ያላቸውን “የህግ ጥሰቶች” በመዘርዝር ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ እንደነበር አስታውሷል። በዚህ መሰረት ድርጅቱ “በተቋቋመበት ዓላማ መሰረት”፤ “ህጋዊ ሂደትን ጠብቆ እንዲሰራ” “በጥብቅ ማሳሰቡንም” ጠቅሷል።

🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2024/14634/

@EthiopiaInsiderNews


FRDE CCI Decision on the issue of OSCCB.pdf
5.7Мб
የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ክልል ያሉ ነዋሪዎችን አስመልክቶ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቅራቢነት የቀረበውን የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄ የህገመንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤው በመዝገብ ቁጥር 7438/15 ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጠው ወሳኔ የህገ መንግስት ትርጉም አያስፈልገውም በሚል በአብላጫ ድምፅ የተሰጠ ውሳኔ::


ድርጅት እና እንደ አገር ውስጥ ባለሀብት መቆጠር የፈለገ፤ በብር የባንክ አክሲዮን ስለሚገዛበት አግባብ ወይም ባንክ ስለሚያቋቁምበት አግባብ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰን ነው” ይላል። ሆኖም ትውልደ ኢትዮጵያዊው ከዚሁ ኢንቨስትመንት የሚያገኘውን ማንኛውንም ክፍያ ወይም ገቢ “በውጭ ምንዛሬ ከኢትዮጵያ ውጭ ማዛወር እንደማይችል” በአዲሱ አንቀጽ ላይ ተደንግጓል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)


አዲሱ የባንክ ስራ አዋጅ ያካተታቸው ተጨማሪ ድንጋጌዎች የትኞቹ ናቸው?
****

ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8፤ 2017 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የባንክ ስራ አዋጅ፤ በረቂቅ ደረጃ ከነበረው ይዘት የተወሰኑ ማሻሻያዎች ተደርገውበታል። በሶስት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ የጸደቀው ይህ አዋጅ፤ በረቅቁ ላይ ተካትተው በነበሩ ትርጓሜዎች እና ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ላይ ማሻሻያ አድርጓል። 
ማሻሻያ ከተደረገባቸው ድንጋጌዎች መካከል የባንክ ቅርንጫፎች እና የውጭ ባንኮችን የተመለከቱት ይገኙበታል። የውጭ ዜጎች በባንክ ስራ የሚሳተፉበትን አካሄድ በሚዘረዝረው የአዋጅ ክፍል ላይ አዲስ አንቀጽ እንዲካተት ተደርጓል። በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋ በባንክ ስራ ስለሚሰማራበት ሁኔታ በረቂቁ ላይ ከተቀመጠው በተጨማሪም አዲስ ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ ላይ ተካትቷል። 
ከማሻሻያዎቹ እና ከአዳዲስ አንቀጾች ውስጥ በ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተጠናቀሩትን፤ ከዚህ በታች አቅርበናቸዋል፦

ትርጓሜዎች
ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት፦ ባለፈው ሰኔ ወር ለፓርላማ የቀረበው የአዋጅ ረቂቅ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን ትርጓሜ ሲያብራራ “ወለድ ያለመቀበልን ጨምሮ ከሸሪዓ መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ የሚሰጥ የባንክ አገልግሎት ነው” በሚል ነበር ያስቀመጠው። ይህ ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ እንደ አዲስ እንዲሻሻል ተደርጓል።
በአዲሱ ድንጋጌ “ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት” ማለት “ወለድ ያለመቀበልን ጨምሮ ከሸሪዓ መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ በወለድ ነጻ ባንኮች እና ከወለድ ነጻ አገልግሎት መስኮት በሚሰጡ ባንኮች የሚሰጥ እንደሆነ” ተቀምጧል። ይህ ማሻሻያ የተደረገው፤ አገልግሎቱ በወለድ ነጻ ባንኮች እና ከወለድ ነጻ አገልግሎት መስኮት በሚሰጡ ባንኮች የሚሰጥ መሆኑን “በማያሻማ መልኩ” መደንገግ አስፈላጊ በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ ለፓርላማ በቀረበ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተብራርቷል።  
ቋሚ ንብረቶች፦ የአዋጅ ረቂቁ የትርጓሜ ክፍል፤ ቋሚ ንብረቶች “የረጅም ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ንብረቶች ሆነው በመመሪያ ይወሰናሉ” በማለት የተሰጠው ትርጓሜም እንደዚሁ ተሻሽሏል። ዛሬ በጸደቀው አዋጅ “ቋሚ ንብረት” ማለት “ግዙፋዊ ሀልዎት ያለው እና ገቢ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጥ ንብረት እና ዝርዝሩ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ የሚወሰን ነው” የሚል ትርጓሜ ተሰጥቶታል። 
ሀብት እና እዳ ማስተላለፍ፦ የአንድ ባንክን የባንክ ስራ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተሰማራ ሌላ ባንክ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ማስተላለፍ የሚመለከተው የ“ሀብት እና እዳ ማስተላለፍ” ትርጓሜ፤ ፋይናንስ ነክ የሆኑ እና ያልሆኑ ሀብቶችን የሚጨምር እንደሆነ በረቂቅ አዋጁ ላይ ተቀምጧል። በጸደቀው አዋጅ ላይ “ዕዳዎች” በተመሳሳይ መልኩ እንደሚተላለፉ ተደንግጓል።

የባንኮችን ቅርንጫፍ በተመለከተ
የባንክ ቅርንጫፍ ወይም ንዑስ ቅርንጫፍ ለመክፈት መሟላት ያለባቸው “ዝቅተኛ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች በብሔራዊ ባንክ መመሪያ” እንደሚወሰኑ በአዋጅ ረቂቁ ላይ ተቀምጦ ነበር። በጸደቀው አዋጅ ከዚህ በተጨማሪ የባንክ ቅርንጫፎችን ለመዝጋት መሟላት ያለባቸው “ዝቅተኛ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች” በብሔራዊ ባንክ መመሪያ እንዲወሰን ተደርጓል።   
የውጭ ባንክ እንደራሴ ቢሮ በተመለከተ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማንኛውም የውጭ ባንክ እንደራሴ ቢሮ ፈቃድ ለማግኘት ሊያሟላቸው የሚገቡ ዝቅተኛ ሁኔታዎች እና መስፈርቶችን በተመለከተ በመመሪያ እንደሚወስን በረቂቅ አዋጁ ስልጣን ተሰጥቶት ነበር። በጸደቀው አዋጅ ላይ ባንኩ ከዚህ ስልጣን በተጨማሪ “ቁጥጥር የማድረግ” ኃላፊነትም ተደርቦለታል።   
በአዋጅ ረቂቁ ላይ “ማንኛውም ባንክ ከብሔራዊ ባንክ አስቀድሞ የጽሁፍ ፈቃድ ሳያገኝ ኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፍ ወይም ንዑስ ቅርንጫፍ መክፈት አይችልም” የሚል ድንጋጌ ሰፍሮ ነበር። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ማንኛውም ባንክ ከብሔራዊ ባንክ አስቀድሞ የጽሁፍ ፈቃድ ሳያገኝ  “የተከፈተ ቅርንጫፍ መዝጋት አይችልም” የሚል ተጨማሪ ድንጋጌ ታክሎበታል።   

የውጭ ባንኮችን በተመለከተ
የአዋጅ ረቂቁ “ማንኛውም ተቀማጭ ገንዘብ የሚቀበል ወይም የማይቀበል የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ ወይም የውጭ ባንክ ተቀጥላ፤ ተቆጣጣሪው ያወጣቸውን ማንኛውም የጤናማነት መለኪያ መስፈርቶች እንደአግባብነቱ ከሀገር ውስጥ ባንኮች እኩል ማክበር አለበት” ይላል። የውጭ ባንክ ቅርንጫፉ ወይም የውጭ ባንክ ተቀጥላው ከዚህ በተጨማሪ “ሌሎች አግባብነት ያላቸው ተቆጣጣሪ አካላት ያወጡትን ህጎች ማክበር” እንደሚጠበቅበት በጸደቀው አዋጅ ላይ ሰፍሯል። 
ይህ ማሻሻያ የተደረገው “የውጭ ባንኮች የብሔራዊ ባንክን ብቻ ሳይሆን የሌሎች አግባብነት ያላቸውን ተቆጣጣሪ አካላት ህጎችን ከሀገር ውስጥ ባንኮች እኩል አክብረው መስራት እንዳለባቸው ለማመላከት” እንደሆነ በማሻሻያው ላይ ሰፍሯል።
የውጭ ዜጎች በባንክ ስራ ስለሚሳተፉበት ሁኔታ
አዲስ ድንጋጌ፦ የውጭ ዜጎች በተለያዩ ዘዴዎች የሚያደርጉት ኢንቨስትመንት በባንክ ስራ አዋጅ የተደነገገውን ገደብ በጠበቀ መልኩ መሆኑን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ፤ በረቂቅ አዋጁ ላይ ያልነበረ አዲስ ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ እንዲካተት ተደርጓል። ይህ ድንጋጌ “በውጭ ዜጎች እና ኢትዮጵያዊያን ወይም እንደ አገር ውስጥ ባለሀብት በሚቆጠር የውጭ ሀገር ዜግነት ባለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ በጋራ ባለቤትነት የተያዘ ድርጅት፤ አንድ ባንክ ላይ አክስዮን ሲይዝ፤ ባንኩ ላይ የተደረገው የውጭ ኢንቨስትመንት መጠን የሚሰላው፤ አክስዮን በገዛው ደርጅት ላይ የውጭ ዜጎች ያላቸውን የባለቤትነት ድርሻ መጠን መሰረት በማድረግ ይሆናል” ይላል። 
የተሰረዘ ድንጋጌ፦ “ተቀማጭ የማይቀበል የውጭ ባንክ ቅርንጫፍን” በተመለከተ በረቂቅ አዋጁ ላይ ተካትቶ የነበረው ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ እንዲሰረዝ ተደርጓል። የተሰረዘው ድንጋጌ “ማንኛውም ተቀማጭ የማይቀበል የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ መሰማራት የሚፈቀድለት፤ በማበደር፣ የብድር ክፍያዎችን በመቀበል እና ብድር የመስጠት ሂደቱን ለማቀላጠፍ የተከፈቱ የተበዳሪዎች የተቀማጭ ሂሳቦችን በማስተዳደር ላይ ብቻ ነው” የሚል ነበር። 
የውጭ ባንኩ “ብድሮችን እና ሌሎች ፋይናንሶችን ከውጭ ሀገር ምንጮች ሊያገኝ እና በብሔራዊ ባንክ መመሪያ እና አግባብነት ባላቸው ሌሎች ሕጎች መሰረት መጀመሪያ ላይ በተመዘገበው አግባብ መልሶ ሊከፍል” እንደሚችልም በዚህ ድንጋጌ ላይ ተካትቶ ነበር። ይህ ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ ላይ ሳይካተት የቀረው“ ማንኛውም የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ስራ በሚሰራበት ወቅት የሚፈቀዱለትን እንቅስቃሴዎች በግልጽ የሚያስቀምጥ መመሪያ ብሔራዊ ባንክ እንደሚያወጣ የተደነገገ” በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ ለፓርላማ አባላት የተሰራጨው ማብራሪያ ያስረዳል። 

በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋ በባንክ ስራ ስለሚሰማራበት ሁኔታ
በፓርላማ የጸደቀው አዋጅ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋ በባንክ ስራ የሚሰማራበትን ሁኔታ የተመለከተ አዲስ አንቀጽ፤ በረቂቁ ከተቀመጡ ድንጋጌዎች በተጨማሪነት እንዲያካትት ተደርጓል። አዲሱ አንቀጽ የተካተተው “በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች በባንክ ሥራ ላይ ስለሚኖራቸው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ስርዓት በግልጽ በሕግ መደንገግ በማስፈለጉ” ምክንያት እንደሆነ በማብራሪያው ላይ ተቀምጧል።ይህ አንቀጽ “አግባብነት ባለው ሕግ የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ሰው ወይም በእነዚህ ሰዎች ሙሉ በሙሉ የተያዘ እና የተቋቋመ






የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምጽ ጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ4ተኛ ዓመት የስራ ዘመን በ11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅን ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል፡፡

በምክር ቤቱ፤ ቋሚ ኮሚቴው የብሄራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ሪፖርት ካቀረበ በኋላ የውሳኔ ሀሳቡን መርምር ረቂቁን አጽድቋል፡፡

በዚህም ረቂቁ አዋጅ ቁጥር 1359 /2017 በመሆን በሙሉ ድምጽ ጸደቋል፡፡

ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም


Репост из: Ethiopian Legal insight
ተከሳሽ ከሞተ በምን ያህል ጊዜ ነው ማመልከቻ የሚቀርበው
በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 49(2) ላይ እንደተመለከተው ከሳሽ ከሞተ ክሱን ለመቀጠል መብት አለን የሚሉ ወገኖች ዋናው ከሳሽ በሞተ በአንድ ዓመት ውስጥ ክሱ ለመቀጠል እንዲፈቀድላቸው ሳያመለክቱ የቀሩ እንደሆነ የተጀመረው ክርክር ውድቅ እንደሚሆን የተመለከተ ሲሆን ነገር ግን በቁጥር 50 ላይ ተከሳሽ ሲሞት መብት አለን የሚሉ ወገኖች ክሱን ለማስቀጠል በስንት ጊዜ ማመልከት እንዳለባቸው አልተመለከተም ሆኖም የድንጋጌው እንግሊዝኛ ከአማርኛው በተለየ አራት ንዑስ አንቀፃት ያሉት ሲሆን በንዑስ አንቀፅ 3 ላይ በአማርኛው ድንጋጌ የሌለ ‹‹where within one year from the death of the defendant no application is made under sub-art.(1),the suit shall abate as against the deceased.›› ተከሳሽ በሞተ በአንድ ዓመት ውስጥ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 50(1) መሰረት አቤቱታ ካልቀረበ ክሱ ውድቅ ይደረጋል ሲል ደንግጓል፡፡በአማርኛ ቅጂ ላይ ያለው አገላለፅ በእንግሊዘኛው ላይ ያለውን ሀሳብ በትክክል አመላስተላለፉን በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡የትርጉም ልዩነት ሲኖር የአማርኛውን ትርጉም መውሰድ ተመራጭ ቢሆንም ነገር ግን የአማርኛው ድንጋጌ በእንግሊዝኛው ድንጋጌ የማይገኝ ጭራስ ንዑስ አንቀፅ የሌለው መሆኑ ሲታይ ጉዳዩ አከራከሪ ሆኖ ሲቀርብ በእንግሊዝኛው ንዑስ አንቀፅ በመጠቀም ለጉዳዩ እልባት መስጠት ይገባል፡፡

በኢትዮጵያ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ የቀረበው ሌጋልቴክ በሞባይል መተግበሪያ አማራጭ ቀርቧል
ፕሌይ ስቶር በመግባት LegalTech ብላችሁ ማውረድና መመዝገብ ትችላላችሁ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ethiopianlegaltech.eli


የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታራሚዎች በሙሉ ወደ ገላን አባሳሙኤል ሊዘዋወሩ ነው።
***
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 1174/2012 የተሰጠውን ተልዕኮ ውጤታማ በሆነ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችለውን ሰፋፊ ስራዎች እየሰራ ይገኛል፡፡ ለአብነትም የህግ ታራሚዎችን የጥበቃና ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግ ፣ የመሰረታዊ ፍላጎት አቅርቦት ለማሻሻል፣ የታረሙ፣ የታነፁና ህግ አክባሪ ዜጎች ሆነው ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ ለማድረግ በአዲስ አበባ እና በክልል በሚገኙ ማዕከሎቹ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ማረሚያ ቤቶችን በመገንባት ታራሚዎችን ለአደጋ ሊያጋልጡ ከሚችሉ መጠለያዎች የማዘዋወር ስራ ሲሰራ ቆይቷል፤አሁንም እየሰራ ይገኛል፡፡
በመሆኑም በአዲስ አበባ የህግ ታራሚዎች ቀደም ብለው ይኖሩበት ከነበረው አሮጌው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል አዲስ ወደ ተገነባው ገላን አካባቢ ወደ ሚገኘው እና በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም የማዘዋወር ስራ ይሰራል፡፡
ስለዚህ ኮሚሽናችን በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ይሰጥ የነበረውን የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ ስራ አገልግሎት ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተቋርጦ የሚቆይ በመሆኑ የሀገር ውስጥም ሆናችሁ የውጭ ሚዲያዎች መረጃውን ለታራሚ ቤተሰቦችም ሆነ ለህዝብ እንድታደርሱልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ነገር ግን ከዛሬ ጀምሮ የሚቋረጠው አገልግሎት ከታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መደበኛ ስራው የሚመለስ በመሆኑ አገልግሎቱ በአዲሱ የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ገላን አካባቢ በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው ማዕከል ማግኘት የሚቻል መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

Показано 20 последних публикаций.