Репост из: ከመፅሐፍ ገፅ ®
አንተ ያስተኛህውን...
፨፨፨
ፍልስፍና እንግዲህ የኛ የሁላችንም ተግባር ነው..እስካሰብን ድረስ መጠየቃችን እስከጠየቅን ድረስ መልስን መሻታችን...መልሱንም መልሰን መጠየቃችን የሕይወት አዙሪት ነው ።
ሶርያ ውስጥ...
" መምህሩ ክላስ ገብቶ እያስተማረ ነው..ድንገት ጥግ ላይ አንድ ተማሪ ቁጭ ብሎ አንቀላፍቶ ይመለከታል...ከዛም ይህንን ይናገራል..
" ጥግ ላይ ያለህው አጠገብህ የተኛውን አስነሳው "
ይለዋል...
ልጁም ይሄንን መለሰለት...
" አንተ ያስተኛህውን ሥለምን እኔ አስነሳው ዘንድ ትጠይቀኛለህ? "
፧
ብዙ ግዜ እኛ አገር ላይ የምንስተው አስተሳሰብ አለ ። ለተማሪ ማንቀላፋት ተማሪውን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ...!! ተማሪን እሚያነቃቃ እና እየገባው እንዲማር እሚያደርግ መምህር ከሌለ ተማሪ ቢያንቀላፋ ምን ይገርማል ። ተማሪ ያልገባውን እንዲጠይቅ የሚያደርግ መምህር በሌለበት ተማሪ ልክ እንደገባው ሆኖ ዝም ማለቱ ምን ያስደንቃል?
፧
ተማሪ አይጠይቅም ማለት ገብቶታል ማለት ብቻ ላይሆን ይችላል ። ወይ እየተማረ ያለው እየገባው አይደለም ወይም መማር አልፈለገም ማለትም ሊሆን ይችላል ። ምህንያቱም ለመጠየቅም በራሱ የተወሰነ መረጃ ወይም መረዳት ያስፈልጋልና ። ትክክለኛ መምህር ማለት ደግሞ የራሱን አስተሳሰብ እኛ ላይ እየጫነ የአስተሳሰቡ ወዛደር የሚያደርገን ሳይሆን እኛም ማሰብ እንደምንችል የሚያሳየን ነው ። ለዛም ነው ሶቅራጥስ...
" ማንንም ስለምንም አስተምሬ አላውቅም የኔ አላማ ማሰብ እንደሚችሉ ማሳየት ብቻ ነው "
ይል የነበረው ።
፧
የኛ የትምህርት አቀራረብ እና አሰጣጥ ላይ ችግር ካለ ተማሪ ለምን አያንቀላፋም...? አንዳንዴኮ የደከመን ሰውነት እንኳን አነቃቅቶ ለትምህርት ዝግጁ እሚያደርግ መምህር አለ...አንዳንዱ ደግሞ የነቃውንም እንዲያንቀላፋ ያደርጋል ። መምህር ራሱን ከመጠየቅ ነው መጀመር ያለበት...የትምህርት አይነት አይደለም የአስተማሪ ልዩነት ነው ተማሪን ለንቃትም ሆነ ለእንቅልፍ የሚዳርገው ።
ራስን መጠየቅ ይቅደም...!!
ምንጭ ፦
📰 philosophical world
ግኝት :- ከፍልስፍና ዓለም
ይቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://t.me/ewuketmad