“ዕድሜ ለአንቺ ፍቅሬ”
( #አምኃ)
በፈጣሪ ትዕዛዝ--በማይሻር ቃሉ፤
“በእግዚአብሔር አምሳል”--ተፈጥረናል አሉ፡፡
ቀናቴን ጨርሼ--የማኅፀን ጣጣ፤
እኔም እንደ ፍጥረት--ወደ ምድር ስመጣ፡፡
ከእናቴ ማኅፀን--ስወጣ ጀምሮ፤
ቀናቴ ጨለሙ--ጀመርኩኝ እሮሮ፡፡
መቼም ሰዎች ሁነን--ስንኖር በዓለም ላይ፤
ጣጣ አይጠፋምና--ፈተና የሚያሳይ፡፡
በሕይወቴ ሁሉ--ነግሶ ብቸኝነት፤
ፈተናውን ሁሉ--ለማለፍ በትዕግስት፡፡
ብዙ ዘመን ኖርኩኝ--ብዙ ተስፋ አድርጌ፤
የሕይወቴን አጋር--ሔዋኔን ፈልጌ፡፡
ዘመናትን ሁሉ--በመናፈቅ ኖሬ፤
ደስታዬን ፍለጋ--ታክቼ ዳክሬ፤
…………..ዕድሜ ለአንቺ ፍቅሬ!
ጨለማው ተገፏል--ወድቋል ብቸኝነት፤
በአንቺ ተገለፀ--ሰው የመሆኔ እውነት፡፡
ዕድሜ ለአንቺ ፍቅሬ….!
ደስታዬን አገኘሁ--ሕይወቴ ተሟላ፤
በአንቺ በውዴ ነው--አይደለም በሌላ፡፡
ዕድሜ ለአንቺ ፍቅሬ!
የፍቅር አውድማ--የመውደድ አድባሬ
………..ይኸው ሞላ ዛሬ…
ዕድሜ ለአንቺ ፍ…ቅ…ሬ!!!
( #አምኃ)
በፈጣሪ ትዕዛዝ--በማይሻር ቃሉ፤
“በእግዚአብሔር አምሳል”--ተፈጥረናል አሉ፡፡
ቀናቴን ጨርሼ--የማኅፀን ጣጣ፤
እኔም እንደ ፍጥረት--ወደ ምድር ስመጣ፡፡
ከእናቴ ማኅፀን--ስወጣ ጀምሮ፤
ቀናቴ ጨለሙ--ጀመርኩኝ እሮሮ፡፡
መቼም ሰዎች ሁነን--ስንኖር በዓለም ላይ፤
ጣጣ አይጠፋምና--ፈተና የሚያሳይ፡፡
በሕይወቴ ሁሉ--ነግሶ ብቸኝነት፤
ፈተናውን ሁሉ--ለማለፍ በትዕግስት፡፡
ብዙ ዘመን ኖርኩኝ--ብዙ ተስፋ አድርጌ፤
የሕይወቴን አጋር--ሔዋኔን ፈልጌ፡፡
ዘመናትን ሁሉ--በመናፈቅ ኖሬ፤
ደስታዬን ፍለጋ--ታክቼ ዳክሬ፤
…………..ዕድሜ ለአንቺ ፍቅሬ!
ጨለማው ተገፏል--ወድቋል ብቸኝነት፤
በአንቺ ተገለፀ--ሰው የመሆኔ እውነት፡፡
ዕድሜ ለአንቺ ፍቅሬ….!
ደስታዬን አገኘሁ--ሕይወቴ ተሟላ፤
በአንቺ በውዴ ነው--አይደለም በሌላ፡፡
ዕድሜ ለአንቺ ፍቅሬ!
የፍቅር አውድማ--የመውደድ አድባሬ
………..ይኸው ሞላ ዛሬ…
ዕድሜ ለአንቺ ፍ…ቅ…ሬ!!!