ተይኝ...!
.
አምኃሥላሴ.
እኔም ወስላታ ነኝ...
እንጀራ እየበላሁ ፍርፋሪ 'ሚያምረኝ...
.
ከአተላ እስከ ዝቃጭ ሳላስተርፍ ቀማሽ፤
ከኋላና ከፊት...
እየተመላለስኩ በራበው ሆዴ አፋሽ፤
እባብ በገላዬ ሰይጣኑን በአካሌ ተቀብየ አንጋሽ...
.
ምን ላድርግ ወዳጄ...
ሰብዓዊ ፀባዬ ሲመርጥ እየዋለ፤
ከትናንት የሚሻል ቀን ቢመጣ እያለ፤
.
.
አይ ምስኪኗ ሚስቴ..
.
"ትሻላለች ብየ ትብስን አመጣሁ" ኾነና ነገሩ፤
በአንቺ በውዴ ላይ...
የመጣች ወንበዴ ሥጋዬን በላችው ታወቀች ባ'ገሩ፤
.
"ለሁሉም ጊዜ አለው!" እንዲል መጽሐፉ፤
ጊዜ ያመጣቸው በጊዜ እያለፉ፤
ስንት ዘመን ሔዶ ስንት ዘመን መጣ፤
ምስኪኑ ያንቺ ባል በሥጋ ስቀጣ፤
.
ተይኝ...! አንቺ ክፉ...
"ግፍ ይተርፋል ለራስ" ሕሊናሽ ይመስክር፤
በራሔሎች እንባ
በሰማዕታት ደም
ፍትሕ ከላይ ሲኾን
ይውጥሻል'ኮ የቆምሽበት ምድር!!!
2.
ስወድሽሽሽ…
©አምኃሥላሴ
..
ንጋት ሲጀማምር~የአህያ ሆድ መስሎ..፣
በውብ ቀለሞቹ~በጥበብ ተስሎ..፤
.
በአውራ ዶሮ ጩኸት~በአዕዋፍ ዜማ ንጋቱ ሲበሰር፣
የማይቆም ኹናቴ~የዘለዓለም ተግባር፤
እጅግ ይደንቀኛል~~የተፈጥሮ ነገር!
.
ጽልመቱ ተገፎ~
ብርሃን ምድር አርፎ
በቀን ይለወጣል፣
ትናንት እንዳለፈ ዛሬም ሊያልፍ ይመጣል፤
.
ቀንም ኾነ...
የፀሐይ ብርሃን
ከወና ሕዋ ላይ እንደመጣ ርቆ፣
በምድር ገጽ ላይ ጨረሩን ፈንጥቆ፤
በብርሃን መዋዕል ቀንም እንዳጌጠ
ጀንበር ስትገባ
ጨለማ መጣና እሱም ተለወጠ...
✍
በፀሐይ ብርሃን ፈክቶ የዋለ ቀን
በጸዳል አብርቶ
ምሽትን ተክቶ
ለጽልመት ሲለቀን...፤
በእልፍ አዕላፍ ከዋከብት ታጅባ ጨረቃ፣
ጽልመት ትገፋለች መሔጃዋ እስኪደርስ ፍቅሯ እስከሚያበቃ!
✍
ዐየሽልኝ ውዴ
የተፈጥሮን ነገር፣
መጥቶ የሚሔድ ነው የኹነታት ፍቅር!
.
እኔ ግን ስወድሽሽሽ...
መውደዴ ብርታቱ
ናፍቆቴ ብዛቱ
የፍቅሬ ጽናቱ!
ፀሐይን አይደለም~~ ሌት የሚያንቀላፋ፤
ጨረቃንም አይደል~~ ንጋት የሚጠፋ!!!
.
አምኃሥላሴ.
እኔም ወስላታ ነኝ...
እንጀራ እየበላሁ ፍርፋሪ 'ሚያምረኝ...
.
ከአተላ እስከ ዝቃጭ ሳላስተርፍ ቀማሽ፤
ከኋላና ከፊት...
እየተመላለስኩ በራበው ሆዴ አፋሽ፤
እባብ በገላዬ ሰይጣኑን በአካሌ ተቀብየ አንጋሽ...
.
ምን ላድርግ ወዳጄ...
ሰብዓዊ ፀባዬ ሲመርጥ እየዋለ፤
ከትናንት የሚሻል ቀን ቢመጣ እያለ፤
.
.
አይ ምስኪኗ ሚስቴ..
.
"ትሻላለች ብየ ትብስን አመጣሁ" ኾነና ነገሩ፤
በአንቺ በውዴ ላይ...
የመጣች ወንበዴ ሥጋዬን በላችው ታወቀች ባ'ገሩ፤
.
"ለሁሉም ጊዜ አለው!" እንዲል መጽሐፉ፤
ጊዜ ያመጣቸው በጊዜ እያለፉ፤
ስንት ዘመን ሔዶ ስንት ዘመን መጣ፤
ምስኪኑ ያንቺ ባል በሥጋ ስቀጣ፤
.
ተይኝ...! አንቺ ክፉ...
"ግፍ ይተርፋል ለራስ" ሕሊናሽ ይመስክር፤
በራሔሎች እንባ
በሰማዕታት ደም
ፍትሕ ከላይ ሲኾን
ይውጥሻል'ኮ የቆምሽበት ምድር!!!
2.
ስወድሽሽሽ…
©አምኃሥላሴ
..
ንጋት ሲጀማምር~የአህያ ሆድ መስሎ..፣
በውብ ቀለሞቹ~በጥበብ ተስሎ..፤
.
በአውራ ዶሮ ጩኸት~በአዕዋፍ ዜማ ንጋቱ ሲበሰር፣
የማይቆም ኹናቴ~የዘለዓለም ተግባር፤
እጅግ ይደንቀኛል~~የተፈጥሮ ነገር!
.
ጽልመቱ ተገፎ~
ብርሃን ምድር አርፎ
በቀን ይለወጣል፣
ትናንት እንዳለፈ ዛሬም ሊያልፍ ይመጣል፤
.
ቀንም ኾነ...
የፀሐይ ብርሃን
ከወና ሕዋ ላይ እንደመጣ ርቆ፣
በምድር ገጽ ላይ ጨረሩን ፈንጥቆ፤
በብርሃን መዋዕል ቀንም እንዳጌጠ
ጀንበር ስትገባ
ጨለማ መጣና እሱም ተለወጠ...
✍
በፀሐይ ብርሃን ፈክቶ የዋለ ቀን
በጸዳል አብርቶ
ምሽትን ተክቶ
ለጽልመት ሲለቀን...፤
በእልፍ አዕላፍ ከዋከብት ታጅባ ጨረቃ፣
ጽልመት ትገፋለች መሔጃዋ እስኪደርስ ፍቅሯ እስከሚያበቃ!
✍
ዐየሽልኝ ውዴ
የተፈጥሮን ነገር፣
መጥቶ የሚሔድ ነው የኹነታት ፍቅር!
.
እኔ ግን ስወድሽሽሽ...
መውደዴ ብርታቱ
ናፍቆቴ ብዛቱ
የፍቅሬ ጽናቱ!
ፀሐይን አይደለም~~ ሌት የሚያንቀላፋ፤
ጨረቃንም አይደል~~ ንጋት የሚጠፋ!!!