ይቅርታ.png
አዳምና ሄዋን በገነት ሆነው አትብሉ የተባሉትን በሉ። ህግንም ተላለፉ። ይኸው ዛሬም ምንም ሳናጣ የተከለከልነውን በማድረግ ሃጢያት እንሰራለን፤ እንበድላለን፤ እናስቀይማለን። ሃጢያት የሰው ልጅ ባህሪ ነው።
ነገር ግን እግዚአብሔርም የሰውን ልጅ ስለወደደ በይቅርታ ከሃጢያታችን የምነነፃበት ሁለተኛ እድል ሰጠን።
ይቅርታ ሁለት አይነት ትርጉም አለው። አንድ የእግዚአብሔርን ህግ በሃጢያት ስንስት፡ ተፀፅተን ይቅርታ የምንጠይቅበት፣ በዚህም ካለፈ እድፋችን የምንነፃበት ነው።
ሁለተኛው እኛ የበደሉንን ይቅርታ የምናደርግበት ነው።
ሁለተኛው ለመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ እንደሆን አስበንበታል።
ለሌሎች ይቅርታ ስናደርግ የእግዚአብሔርን ይቅርታ አድራጊነት የምንመሰክርበት ነው።
ይቅርታ እንዲደረግልን፡ ይቅር ማለት አለብን!
ተቀይማችሁ፡ በቂም የምትኖሩ፡ ሽንፈት፡ የሚመስላችሁ ካላችሁ ፡ ከፈጣሪ ህግ ይሉኝታ የባሰባችሁ የሚባክን ግዜ የለምና ዛሬውኑ ከልብ ይቅር በሉ።
ይቅርታ ያደረጋችሁበት፡ ወይም ይቅርታ ለማድረግ የከበዳችሁ አጋጣሚ አለ? እስቲ አካፍሉን።
@LoveFkrLove