የፍቅር ጊዜ❤


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


💗አሁን ጊዜው የፍቅር🌺 ነው ከእኛ ጋር አብራችሁ በፍቅር እየተደሰታችሁ እየተዝናናችሁ አብራችሁን ቆዩ🙏
እናንተ ለፍቅር 💕 ያላችሁ አመለካከት ምንድነው?
የፍቅር ጊዜ💟 ለእኔ ፍቅር ፀጋ ነው 💏

For any comment & for cross inbox me📬
@Gelilaye_mal 🌺
.
.
.
.
.
.
.
.

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций






​​​​​​​​​​​​​​​​​​.
መ ቅ ደ ላ ዊ ት 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣

♥️ ክፍል 19

◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Ambaye Getahun


ምን ያልገባሽ ነገር አለ ? ከጣፍኩልሽ ውስጥ? " ዝምታውን ለመስበር እና የውይይት መጀመሪያ እንዲሆን አስቦ ባሩክ የጠየቀው ጥያቄ ነበር። " ሀሳብህ በጣም ከባድ ነው እኔ ያን ማድረግ አልችልም እዚህ እኔን የሚያውቁኝ ብዙ ናቸው ። ቤተሰቦቸንም የሚያውቋቸው ተማሪዎች አሉ። አንተ ያልከውን ባደርግ እና ብል ያለ ጥርጥር ቤተሰቦቼ ጋር እቀያየማለሁ በስስት የሚያየኝን እና የሚወደኝን አባቴን እስከመጨረሻው አጣዋለሁ። እናም በጭራሽ አልችልም። ወይ ለዚህ ሀሳብህ ሌላ ሴት መፈለግ ሳይኖርብህ አይቀርም ።" አለች " የሀሳቡ አመንጪ እኮ እኔ አይደለሁም ይሄን የስነልቦና ህክምና የጀመራችሁት አንቺ እና ናታኔም ናችሁ። እኔን በተወሰነ መልኩ እንድረዳችሁ ጠይቆኝ ነው። እናም በዚህ ምክንያት የዚህ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጇ አንቺ ስለሆንሽ ነው ይሄን ሀሳብ የሰጠሁሽ እንጂ አንቺ እምቢ ብለሽ ለሌላ ልሰጠው የምችለው የፊልም ስክሪፕት አይደለም። " አለ ባሩክ " አይ እኔ እኮ እምቢ ያልኩት ሀሳብህ ከባድ ስለሆነ ነው ። " አለች " ምን መሰለሽ መቅደላዊት ለከባድ ገጠመኞች ለከባድ ችግሮች ከባድ ውሳኔ ያስፈልጋል። ለዚህም አሁን ከባዱን ነገር ታደርጊያለሽ።እመኚኝ ስኬታማ ትሆኛለሽ። አውቃለሁ ብዙ ነገር ሊደርስብሽ ይችላል ግን ለዛም መፍትሔ እናስቀምጣለን።" አለ ባሩክ እጆቿን እየጨበጠ " እንደ እውነቱ ከሆነ ጥሩ ልብ አለሽ ከቅንነት ጋ ከውብ ቁንጅና ጋ ይሄን ባለኝ መረጃ እና በደቂቃዎች ለመረዳት ችያለሁ ።ሰወች ደግሞ ትክክለኛ ነገር አስበው ከሄዱ ከሚጓዙበት የእውነት መንገድ ማንም ሊመልሳቸው ሊያሰናክላቸው አይችልም ይህ የተፈጥሮ እውነት ነው።መጨረሻው መጨረሻ መሆን እንዳለበት ይሆናል። ናሆም ላይ ለእንዲህ አይነት የስነልቦና ችግር በመጋለጡ እኔ በጣም ነው ያዘንኩት ማንም ሰው እንዲህ አይነት ችግር እንዲደርስበት የሚፈልግ የለም እስከማቀው ድረስ አትጠራጠሪ እሱ ላይ የደረሰበት ችግር እኔ ላይ አለያም አንቺ ላይ ቢደርስ የምናደርገው እሱ ከሚያደርገው ቢበልጥ እንጅ አያንስም ። እሱስ ባይሆን ከላይም ቢሆን እናቱን ያወራታል እሷ ጋ ይኖራል ከዚህ በላይ እኮ ምህረት የለም። ግን ደግሞ እናቱ ነች ስለዚህ ለጥላቻው ገደብ ልናበጅበት ይገባል ይቅር ማለትን ልናስተምረው ይገባል። አለዚያ ከባድ ነው"አለ ባሩክ። " ካልክ እሽ ግን ውስጤን ልክ አይደለም እየተሰማኝ ያለው።" አለች መቅደላዊት " አሁን ለስነፅሁፍ ምሽቱ ተዘጋጅ እኔም ወግ ነገር ስለማወጋ መለማመድ አለብኝ በይ ተነሽ ልሸኝሽ አለ እና ቀድሞ ብድግ አለ ።

ናሆም አቢሲኒያ ስታዲየም በክቡር አቶ ይድነቃቸው መቀመጫ በኩል ጫፍ ላይ ከአንዲት ግራር ዛፍ ስር ሆኖ በየደቂቃው ይጥፋል ፣ይቀደዳል ፣ ይጥላል። ቀዶ በጣላቸው ወረቀቶቹ ተከቦ ራሱን ይዞ ቁጭ ብሏል። ከእንደገና ራሱን ለቀቅ አድርጎ ዙሪያውን ሲመለከት ከአንዲት ቁራጭ ወረቀት ላይ ያፈጣል። ወረቀቱ ላይ የተጀመሩ ቃላቶች አሉ።
"የዘራውን ሲያጭድ ይኖራል አለሜ፣
እማ ነች ቅኝቴ እናቴ ናት ህልሜ"
ስንኟን ደጋግሞ አነበባት ማን ይሆን ማን ትሆን ይሄን ስንኝ የሰደረችው የሰደረው? ስንኟ የተፃፈችባትን ወረቀት ኪሱ ውስጥ አስገባት። ይሄን የፃፈው ሰው በምን አይነት ጥልቅ የእናት ፍቅር ውስጥ ይሆን? ምን አለ እኔም እናቴ እንዲህ እንዳደርግ ብትፈቅድልኝ ለምን አባየን ለምን እኔን ትታኝ ሄደች? ምን አድርጊያት ነው ገና በልጅነቴ የጨከነችብኝ? " ብሎ ራሱን ይጠይቃል። ትዝ አለው አንድ ቀን ትምህርት ቤት የተቋጠረላቸውን ምሳ ተሰብስበው ሲበሉ ሁሉም ጓደኞቹ እናታቸው እንደሰራችላቸው እየተናገሩ ናሆም ግን አባቴ ነው የሰራልኝ ሲላቸው በጣም ተገረሙ ።ነገር ግን ናሆም ከትምህርት ቤት ሲመለስ አባቱን ጠየቀ እናቴ ለምንድነው ትታን የሄደችው? ብሎ ሲጠይቀው ልጄ እኔን ትታ ለመሄድ ምክንያት ሊኖራት ይችላል አንተን ትታ ለመሄዷ ግን ምክንያት ያላት አይመስለኝም ቢሆንም ምክንያት ካላት ደግሞ አንተ ትልቅ ልጅ ስትሆን እናትህ ጋ ሄደህ እማ ምን አድርጌሽ ነው? ትተሽኝ የሄድሽው?"ብለህ ትጠይቃታለህ " አሁን ግን ጥያቄወችህን በሙሉ ተዋቸው እኔ ለአንተ ሁሉ ነገሬን እሰጣለሁ የእኔ ትልቁ ህልም የአንተ ትልቅ መሆን ነው። ስለዚህ በትምህርትህ በርትተህ ወደፊት እኔን እንድታኮራኝ ነው የምፈልገው ።እሽ የኔ ልጅ ደግሞ እኮራብሀለሁ " አለና እያገላበጠ ሳመው። ናሆም ከትዝታ ማዕበል ወጥቶ ጉንጩን ተደገፈ ።ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ " አባቱ እንደነገረው እናቱ ለምን ጥላው እንደሄደች አልጠየቃትም ። ግን ደግሞ መጠየቅ የምችለው አሁን አይደለም ብሎ ያስባል። ይህን እያሰበ እያለ ሀሳብ መጣለት እና ወረቀቱን አውጥቶ መፃፍ ጀመረ። ለስአታት ቀና ሳይል ከፃፈ በኋላ ። ጨርሶ በደስታ ፈገግ አለ ደግሞ ደጋግሞ አነበበው። " "ሸጋ ግጥም" አለ በለሆሳስ! ..........


꧁༺༒༻꧂


✎ 🌺ክፍል ሃያ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @loverrtime
የፍቅር ጊዜ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄

ቀጣዩ ክፍል ቶሎ እንዲደርሳቹ ቀጣይ ሚለውን ይጫኑ ❤❤


እባካችሁ email ያላችሁ የፍቅር ጊዜ ቤተሰቦች ይህንን👇👇 ሊንክ በመጫን የዩቱብ ቻናሌን Subscribe አድርጉ በቅንነት 🙏🏻🙏🏻💚💚💛💛❤❤

https://youtube.com/channel/UCtJE3G2Alqf42FtI0XVYkZQ?Sub_confirmation=1


127ሺ ተከታይ ያለዉ ቻናል አሪፍ view ያለዉ ቻናል በተመጣጣኝ ዋጋ መግዛት ምትፈልጉ!... ገዝተዉ ወደ ፈለጉት የቢዝነስ አገልጎሎት መቀየር ምትፈልጉ
INBOX Us @ZSJONI

ማሳሰብያ ❗️❗️
እዉነተኛ ገዢ ብቻ ያናግረኝ:


Репост из: Неизвестно
♥️የፍቅርኛዎን ውይም የእርሶን ስም የመጀመሪያ ፈደል በመንካት ከዛ የምሆነውን አሰገራሚ ነገር ያያሉ♥️!!

A ♥️ B ♥️ C 🌹
D ♥️ E ♥️ F 🌹
G ♥️ H ♥️ I 🌹
J ♥️ K ♥️ L 🌹
M ♥️ N ♥️ O 🌹
P ♥️ Q ♥️ R 🌹
T ♥️ U ♥️ V 🌹
W ♥️ X ♥️ Y 🌹
🌹Z🌹


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Репост из: Неизвестно
Watch "ሰው ተገልብጦ መኪና ሞተ አስቂኝ ፕራንክ / Someone overturned and the car died funny prank / sew tegelbto mekina" on YouTube
https://youtu.be/RpCl0nrKAEE






​​​​​​​​​​​​​​​​​​.
መ ቅ ደ ላ ዊ ት 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣

♥️ ክፍል 19

◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Ambaye Getahun


ምን ያልገባሽ ነገር አለ ? ከጣፍኩልሽ ውስጥ? " ዝምታውን ለመስበር እና የውይይት መጀመሪያ እንዲሆን አስቦ ባሩክ የጠየቀው ጥያቄ ነበር። " ሀሳብህ በጣም ከባድ ነው እኔ ያን ማድረግ አልችልም እዚህ እኔን የሚያውቁኝ ብዙ ናቸው ። ቤተሰቦቸንም የሚያውቋቸው ተማሪዎች አሉ። አንተ ያልከውን ባደርግ እና ብል ያለ ጥርጥር ቤተሰቦቼ ጋር እቀያየማለሁ በስስት የሚያየኝን እና የሚወደኝን አባቴን እስከመጨረሻው አጣዋለሁ። እናም በጭራሽ አልችልም። ወይ ለዚህ ሀሳብህ ሌላ ሴት መፈለግ ሳይኖርብህ አይቀርም ።" አለች " የሀሳቡ አመንጪ እኮ እኔ አይደለሁም ይሄን የስነልቦና ህክምና የጀመራችሁት አንቺ እና ናታኔም ናችሁ። እኔን በተወሰነ መልኩ እንድረዳችሁ ጠይቆኝ ነው። እናም በዚህ ምክንያት የዚህ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጇ አንቺ ስለሆንሽ ነው ይሄን ሀሳብ የሰጠሁሽ እንጂ አንቺ እምቢ ብለሽ ለሌላ ልሰጠው የምችለው የፊልም ስክሪፕት አይደለም። " አለ ባሩክ " አይ እኔ እኮ እምቢ ያልኩት ሀሳብህ ከባድ ስለሆነ ነው ። " አለች " ምን መሰለሽ መቅደላዊት ለከባድ ገጠመኞች ለከባድ ችግሮች ከባድ ውሳኔ ያስፈልጋል። ለዚህም አሁን ከባዱን ነገር ታደርጊያለሽ።እመኚኝ ስኬታማ ትሆኛለሽ። አውቃለሁ ብዙ ነገር ሊደርስብሽ ይችላል ግን ለዛም መፍትሔ እናስቀምጣለን።" አለ ባሩክ እጆቿን እየጨበጠ " እንደ እውነቱ ከሆነ ጥሩ ልብ አለሽ ከቅንነት ጋ ከውብ ቁንጅና ጋ ይሄን ባለኝ መረጃ እና በደቂቃዎች ለመረዳት ችያለሁ ።ሰወች ደግሞ ትክክለኛ ነገር አስበው ከሄዱ ከሚጓዙበት የእውነት መንገድ ማንም ሊመልሳቸው ሊያሰናክላቸው አይችልም ይህ የተፈጥሮ እውነት ነው።መጨረሻው መጨረሻ መሆን እንዳለበት ይሆናል። ናሆም ላይ ለእንዲህ አይነት የስነልቦና ችግር በመጋለጡ እኔ በጣም ነው ያዘንኩት ማንም ሰው እንዲህ አይነት ችግር እንዲደርስበት የሚፈልግ የለም እስከማቀው ድረስ አትጠራጠሪ እሱ ላይ የደረሰበት ችግር እኔ ላይ አለያም አንቺ ላይ ቢደርስ የምናደርገው እሱ ከሚያደርገው ቢበልጥ እንጅ አያንስም ። እሱስ ባይሆን ከላይም ቢሆን እናቱን ያወራታል እሷ ጋ ይኖራል ከዚህ በላይ እኮ ምህረት የለም። ግን ደግሞ እናቱ ነች ስለዚህ ለጥላቻው ገደብ ልናበጅበት ይገባል ይቅር ማለትን ልናስተምረው ይገባል። አለዚያ ከባድ ነው"አለ ባሩክ። " ካልክ እሽ ግን ውስጤን ልክ አይደለም እየተሰማኝ ያለው።" አለች መቅደላዊት " አሁን ለስነፅሁፍ ምሽቱ ተዘጋጅ እኔም ወግ ነገር ስለማወጋ መለማመድ አለብኝ በይ ተነሽ ልሸኝሽ አለ እና ቀድሞ ብድግ አለ ።

ናሆም አቢሲኒያ ስታዲየም በክቡር አቶ ይድነቃቸው መቀመጫ በኩል ጫፍ ላይ ከአንዲት ግራር ዛፍ ስር ሆኖ በየደቂቃው ይጥፋል ፣ይቀደዳል ፣ ይጥላል። ቀዶ በጣላቸው ወረቀቶቹ ተከቦ ራሱን ይዞ ቁጭ ብሏል። ከእንደገና ራሱን ለቀቅ አድርጎ ዙሪያውን ሲመለከት ከአንዲት ቁራጭ ወረቀት ላይ ያፈጣል። ወረቀቱ ላይ የተጀመሩ ቃላቶች አሉ።
"የዘራውን ሲያጭድ ይኖራል አለሜ፣
እማ ነች ቅኝቴ እናቴ ናት ህልሜ"
ስንኟን ደጋግሞ አነበባት ማን ይሆን ማን ትሆን ይሄን ስንኝ የሰደረችው የሰደረው? ስንኟ የተፃፈችባትን ወረቀት ኪሱ ውስጥ አስገባት። ይሄን የፃፈው ሰው በምን አይነት ጥልቅ የእናት ፍቅር ውስጥ ይሆን? ምን አለ እኔም እናቴ እንዲህ እንዳደርግ ብትፈቅድልኝ ለምን አባየን ለምን እኔን ትታኝ ሄደች? ምን አድርጊያት ነው ገና በልጅነቴ የጨከነችብኝ? " ብሎ ራሱን ይጠይቃል። ትዝ አለው አንድ ቀን ትምህርት ቤት የተቋጠረላቸውን ምሳ ተሰብስበው ሲበሉ ሁሉም ጓደኞቹ እናታቸው እንደሰራችላቸው እየተናገሩ ናሆም ግን አባቴ ነው የሰራልኝ ሲላቸው በጣም ተገረሙ ።ነገር ግን ናሆም ከትምህርት ቤት ሲመለስ አባቱን ጠየቀ እናቴ ለምንድነው ትታን የሄደችው? ብሎ ሲጠይቀው ልጄ እኔን ትታ ለመሄድ ምክንያት ሊኖራት ይችላል አንተን ትታ ለመሄዷ ግን ምክንያት ያላት አይመስለኝም ቢሆንም ምክንያት ካላት ደግሞ አንተ ትልቅ ልጅ ስትሆን እናትህ ጋ ሄደህ እማ ምን አድርጌሽ ነው? ትተሽኝ የሄድሽው?"ብለህ ትጠይቃታለህ " አሁን ግን ጥያቄወችህን በሙሉ ተዋቸው እኔ ለአንተ ሁሉ ነገሬን እሰጣለሁ የእኔ ትልቁ ህልም የአንተ ትልቅ መሆን ነው። ስለዚህ በትምህርትህ በርትተህ ወደፊት እኔን እንድታኮራኝ ነው የምፈልገው ።እሽ የኔ ልጅ ደግሞ እኮራብሀለሁ " አለና እያገላበጠ ሳመው። ናሆም ከትዝታ ማዕበል ወጥቶ ጉንጩን ተደገፈ ።ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ " አባቱ እንደነገረው እናቱ ለምን ጥላው እንደሄደች አልጠየቃትም ። ግን ደግሞ መጠየቅ የምችለው አሁን አይደለም ብሎ ያስባል። ይህን እያሰበ እያለ ሀሳብ መጣለት እና ወረቀቱን አውጥቶ መፃፍ ጀመረ። ለስአታት ቀና ሳይል ከፃፈ በኋላ ። ጨርሶ በደስታ ፈገግ አለ ደግሞ ደጋግሞ አነበበው። " "ሸጋ ግጥም" አለ በለሆሳስ.....


꧁༺༒༻꧂


🌺ክፍል ሃያ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @loverrtime
የፍቅር ጊዜ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄


ሌሎች ቪዲዎችንም ለማግኘት ይህን የtiktok ሊንክ 👇👇 https://vm.tiktok.com/ZMethxQbp/ በመጫን follow ,like & share በማድረግ ከኛ ጋር ይዝናኑ😂


​​​​​​​​​​​​​​​​.
መ ቅ ደ ላ ዊ ት 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣

♥️ ክፍል 18

◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Ambaye Getahun



ማን ነው ስራህን ያቀለለልህ? ምን አይነት ስራ ነበር የነበረህ? " ናሆም ጥያቄወቹን አከታተለበት ። " አሳይመንት ነበረኝ እሱን ሰርቶልኝ ነው " አለ ናታኔም በድንጋጤ " ታዲያ ምነው ደነገጥክ? " " በድንገት ስለገባህብኝ ነዋ " " እንደዛ ከሆነ ጥሩ ግን..... ምን አሳይመንት ነበር? እንዴት ስታወራ አልሰማህም?" አለ ናሆም " አየ ወንድሜ ለዚህ እኮ ነው እኔ እና አንተ ተጠፋፍተናል የምልህ ።ግን የስነፅሁፍ ዝግጅት አለብኝ ምናምን ብለኸኝ ነበር እኮ እንዴት ታዲያ ተመለስክ?" " ባክህ ያቺ መቅደላዊትን ከሩቅ አይቻት የሁሉም ነገር ፍላጎቴ ጠፋ " " ቆይ ግን ይቺ ልጅ ምን አድርጋህ ነው እንዲህ ጠምደህ የያዝካት?" ምን እኔ ጠምጀ እይዛታለሁ እሷ ነች እንጅ " እኮ እሷ ምን አድርጋህ ነው?" " ከንፈሩን ነከሰ ባውቅማ ኖሮ ጥሩ ነበር የማደርገውን አውቅ ነበር። ነገር ግን ልጅቱ አስመሳይ ነች በጭራሽ የሆነ ነገር እየሰራች ነው እስካሁን አላወኩም ግን ግዴለም እደርስበታለሁ።" አለ ናሆም "

መቅደላዊት ፖስታውን እያየች ይሄ ደግሞ ምን ለማድረግ አስቦ ነው? " ራሱን እንዴት ነው የሚያየው? ሲያስጠላ " አለች እየተመናጨቀች ፖስታውን በዝግታ አንስታ ከከፈተች በኋላ በጥሞና አምብባ ከጨረሰች በኋላ ፊቷ ሁሉ ተለዋወጠ። ስልኳን አንስታ ደወለች " አቤት መቅደላዊት " ከወዲኛው የስልክ ድምፅ የተሰማው የናታኔም ድምፅ ነበር። " ቆይ ጓደኛህ ምን አይነት ጅል ነው ያመዋል ልበል? ሰውን ሳያውቅ " አለች መቅደላዊት " ቆይ መቅዲ ተረጋጊና ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ " አለ ናታኔም ።መቅደላዊት አንድም ሳታስቀር ሁሉም በስልክ ነገረችው እና በመጨረሻ" አሁን ላገኘው እፈልጋለሁ ስልኩን ስጠኝ " አለች " እሽ 0910..........ባሩክ እስጢፋኖስ ከፈለግሽ ዲዮጋንም ማለት ትችያለሽ ።ነፃ ሁኝ ግን መቅዲ አደራሽን ባሩክ ላይ ብስጭት መቆጣት መጮህ አይሰራም ።በእርጋታ የአንቺን ሀሳብ ትነግሪዋለሽ ።ለምን የእሱን ሀሳብ በአንቺ ሀሳብ ላይ እንደመዘንሽ ይገባዋል።ወይም ለምን እንደዛ እንዳለሽ ያብራራልሻል። ይህ ካልሆነ ግን በእውነት ትቶሽ ይሄዳል ።" አለ ናታኔም በልመናም በማስጠንቀቂያም አዘል ንግግር በተወሰነም መልኩ ስለ ባሩክ ግብአት " እና መሄድ ይችላል ለእኔ ብሎ አይቀመጥ " አለች መቅደላዊት " መቅዲ ምን ሆነሻል? ናታኔም በስልክ አምባረቀ " በዚህ ጉዳይ ላይ እኮ አንቺ ነሽ ትልቁን ስራ እየሰራሽ ያለሽው ለምንድነው የምትቀልጅው?" ናታኔም እየተቆጣ ተናገራት። " እሽ ናቲ በቃ አትቆጣ እንዳልከኝ አደርጋለሁ " አለች " ጥሩ አመሰግናለሁ ስትጨርሽ ደውይልኝ " እሽ እደውልልሀለሁ ።

ባሩክ " አክሱም የተማሪወች መናፈሻ " መጨረሻ ፎቅ ላይ ሆኖ " መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ" የተሰኘውን የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ን መፅሀፍ ማንበቡን ገታ አድርጎ ያዘዛትን ወተት አንስቶ ፉት ሲል ስልኩ ጠራ። ያነሳትን ወተት አንድ ጊዜ ስቦ ወደ ነበረችበት ጠረምጴዛ መለሳትና ስልኩን ከኪሱ አወጣ ። አዲስ ቁጥር ነው ላለማንሳት ካመነታ በኋላ አንስቶ "ሀሎ" አለ ። " ሰላም ነው ባሩክ? አወከኝ?" " አላወኩሽም ወይዘሪት " አለ። " መቅደላዊት ነኝ " አለች " እሽ መቅደላዊት በጣም ነው የሚገርመው አሁን ስለ አንቺ እያሰብኩ ነበር።" " እንዴ ስለምንድን ነው ስለ እኔ እምታስበው?" የዋህነትሽን ፣ ቁጡነትሽን ፣..... ሌላም ሌላም እሱን አለማሰብ አይቻልም በዛ ላይ ........" ብሎ ዝም አለ ።" እህ በዛ ላይ .........ጨርሰው እንጅ " አለች ግን ለምንድነው ሴቶች ተጀምሮ ላልተጨረሰ ሀሳብ የምትሞቱት? ውይ ሁሉንም ማወቅ የሚፈልጉ ፍጥረቶች ቢኖሩ ሴቶች ናቸው ሊፈነዱ እኮ ነው የሚደርሱት። ምን እንደሚሻላቸው አሁን ይሄን ሳልጨርስላት ብቀር ሌቱንም ቀኑንም ስለዚህ ጀምር ሀሳብ ነው ቁማ የምታድረው ጉድ እኮ ነው። " አለ በውስጡ " እየጠበኩህ እኮ ነው "አለች ።መቅደላዊት እንዳልተፋታችው ሲረዳ " በዛ ላይ ቆንጆ ነሽ ለማለት ፈልጌ ነው።" አላት በተቻለው መጠን ግንኙነታቸውን ጤናማ አድርጎ ለመሞከር አስቧል። " ኧረ ባክህ ቆንጆ ነኝ እንዴ? አላወኩም ነበር።" አለች መቅደላዊት ምፀታዊ ንግግር ነበር። ባሩክ ገብቶታል ግን እንዳልገባው ለመምሰል " አባቴ ይሙት እውነቴን ነው " አለ ባሩክ እየሳቀ ። መቅደላዊት በሱ በኩል ያላትን የተቃረነ አመለካከት የማስተካከል አይደለም ዋና እቅዱ ናሆም ነው መቅደላዊት ጋር ያለው ጓደኝነት ጤናማ እና አሪፍ ከሆነ ናሆምን ካለበት የስነልቦና ችግር ማውጣት ይቻላል ብሎ ስላመነ ነው።እንዲህ ውድ ጊዜውን የሚያባክነው። ባሩክ ህይወቱ ማንበብ ብቻ ነው።መቅደላዊት ትንሽ ፈገግ ካለች በኋላ " ፈልጌህ ነበር " አለች " ለምንድነው ነው ልታገኚኝ የፈለግሽው?" አለ ባሩክ በደብዳቤው የተነሳ እንደሆነ ገምቷል።" እሱን ስንገናኝ እነግርሃለሁ " " ጥሩ መምጣት ከቻልሽ አክሱም ነኝ ጣራው ላይ " እሽ በቃ መጣሁ " ብላ ስልኩን ዘጋችው።

መቅደላዊት አክሱም መናፈሻ ጣራው ላይ ስትወጣ ሽቅብ የሚነፍሰው ነፋስ አንዳች ነገር የፈለገ ይመስል ቀሚሷን ለመግለብ ይጥራል ። ቅንዝራም የሆነ ነፋስ እሷ ዝቅ ስታደርግ እሱ ደግሞ ከእንደገና ይገልበዋል በስተመጨረሻ እጇን ከቀሚሷ ላይ ሳታነሳ በሁሉም አቅጣጫ ስታማትር ባሩክ በመናፈሻው ደቡብ አቅጣጫ ጥግ ላይ ሆኖ በጥሞና ሲያነብ ተመለከተችው። ለተወሰነ ደቂቃ ቆማ ብትመለከተው እሱ ግን ከሚያነበው መፅሀፍ ውጭ ሌላ የትኛውንም አቅጣጫ ለማየት የፈለገ አይመስልም ። " ባይፈላሰፍ ቆንጆ ወንድ ነበር " አለችና ባሩክ ወደተቀመጠበት ቦታ ሄደች ባሩክ ወደ እሱ የቀረበ የእግር ኮቴ እንደሰማ ቀና ሲል መቅደላዊት ደርሳለች። ሰለም ብያለሁ እንዴት ነሽ ? እጁን ለሰላምታ ዘረጋ ጨበጠችው ጨበጣት እና ፈጠን ብሎ የምትቀመጥበትን ወንበር ስቦ አስቀመጣት። መቅደላዊት በአድራጎቱ የተገረመች ትመስላለች ። የአክሱም ሀውልት ምስል ያለበትን ቲሸርት የለበሰ አስተናጋጅ መጣ እና የተለመደውን ጥያቄ ጠየቀ የመቅደላዊትን የስፕራይት ትዕዛዝ ተቀብሎ አስተናጋጁ ሄደ። " ፈጥነሽ ገው የመጣሽው " አለ " የእውነት? እኔ ደግሞ የቆየሁ መስሎኝ ነበር " አይ በጭራሽ ጥሩ ስአት ላይ ነው ቢያንስ ከዘገየሽ ራሱ የዘገየሽው ካለሽበት እስከዚህ ድረስ ለመድረስ የፈጀብሽ መንገድ ነው " አለና ምቾት እንዲሰማት አደረገ። አስተናጋጁ አንድ የውሀ ብርጭቆ ከአንድ ሎሚ ጋር የታዘዘውን ስፕራይት አስቀመጠ እና ወደ ሌላኛው አካባቢ ተሰወረ........


꧁༺༒༻꧂


✎ 🌺ክፍል አስራ ዘጠኝ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @loverrtime
የፍቅር ጊዜ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄


​​​​​​​​​​​​​​.
መ ቅ ደ ላ ዊ ት 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣

♥️ ክፍል 17

◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Ambaye Getahun



ናሆም ዶርም ሲገባ ናታኔም አልሰማውም ። ምክንያቱም ናታኔም በረንዳ ላይ ጀርባውን ለዶርሙ በር ሰጥቶ እያነበበ ነበር። ናሆም የሚቀይረውን ልብስ ቀይሮ ሊወጣ ሲል ናታኔም ደግሞ ቀና ሲል አይን ለአይን ይገጣጠማሉ ። ናታኔም ብድግ ብሎ "እንዴ ናሆም ደህና ነህ አሁንማ ተጠፋፋን እኮ ወንድሜ " አለ " በጣም ደህና ነኝ ወንድሜ ልክ ነህ በጣም ነው የተጠፋፋነው ግን ደግሞ ያው አንተም ስታነብ ነው የምትውለው እኔም ማንበብ ስለጀመርኩ ነው ።በል አሁን ቶሎ መውጣት አለብኝ " " ናሆም ወደየት ነው እንዲህ የምትቻኮለው? ቀስ በል እንጅ" አለ ናታኔም ወደ ናሆም እየተጠጋ " እየውልህ ወንድሜ ቶሎ መሄድ አለብኝ ቀጣይ ሳምንት የሚዘጋጅ የስነፅሁፍ ምሽት አለ ስለዚህ መዘጋጀት አለብኝ ለዛ ነው ወንድሜ " " ታቀርባለህ ?" አለ ናታኔም " አወ አቀርባለሁ " አለና ናሆም ትቶት ወጣ።

መቅደላዊት በንዴትም በእልህም ወዲያና ወዲህ ትንጎራደዳለች። አይኖቿ ፀሀይ ለመሞቅ ወጥተው የተቀመጡ ይመስላሉ" ናሆም እንኳንም መረቤ ላይ ተጠመድክ ይሄን ነበር የምፈልገው ።አሁን የጨዋታው አሸናፊ ማን እንደሚሆን እናያለን ። አታስብ ቃል እገባልሀለሁ ትክክለኛዋን መቅደላዊት ታያለህ። አወ " አለች ራሷን አያወዛወዘች ስለዚህ ቀጣይ ማድረግ ያለብኝ ነገር ቢኖር ይሄ ነው " አለችና ጠረምጴዛው ላይ የተወሰነ ፅሁፍ የማይመስል ደግሞም ስዕልም የማይመስል ነገር ሞነጫጨረች እና በአንድ እጇ ወገቧን ይዛ አውራ ጣቷን ከንፈሯ ላይ አስጠጋችው።

ባሩክ ሰባ ደረጃ አለፍ ብሎ ከበቀለች አንዲት ትንሽየ ዛፍ ስር ተቀምጦ ወጭ ወራጁን ይመለከታል ። kissing square በመባል የሚታወቅ ቦታ ነው። አንዳንድ ካፕሎች እየመጡ እዚህ ቦታ የሆድ የሆዳቸውን ሲጫወቱ ያመሹና
"ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ፣
አቤት የአንቺ ፍቅር ሲበረታ "
ብሎ ድምፃዊ ቴወድሮስ ካሳሁን እንደዘፈነው ።እነዚህ ካፕሎችም ደንገዝገዝ ሲል ጨለማው ለአይን ሲነሳ ከንፈር ለከንፈር ይያያዛሉ። ከዚያ ለያዥ ለገናዥ ያስቸግራሉ።በዙ ቆነጃጅት የከንፈር ድንግልናቸው የሚወሰደው እዚህ አካባቢ ነው። አንዳንድ ቦዘኔ እና በሰው ደስታ የሚደሰቱ ስራየ ብለው እዚህ አካባቢ በመምጣት የማታ ትዕይንትን ያለ ገቢር ክፋይ ይመለከታሉ ።ያለ ክፍያ ሲኒማን እንደማየት ይቆጥሩታል። ሰባ ደረጃ ደግሞ ስንቱን ደምበር እየሆነ ያስመልሰዋል ።ከሁሉም ብሎኮች ያሉት ወንዶች በመንገዳቸው ባይገናኝም እንኳ ሰባ ደረጃን ሳይሳለሙ አይሄዱም ።አንዳንዶች በዚህ ደረጃ ላይ ሲወጡ ሲወርዱ ከየካቲት ወይም ከስድስት ኪሎ ወደ ፒያሳ የሚወርዱበት ትክክለኛው ሰባ ደረጃ ይመስላቸዋል። በርግጥ ይሄን አካባቢ ለሚያዘወትር ሰው እና ለሚመሰጥበት ሰው ተነቦ የማያልቅ መፅሐፍ መፃፍ ይችላል።ባሩክ ከወዲያኛው መስመር መቅደላዊት ስትመጣ ሲያይ ከተቀመጠበት ይነሳ እና ወደ እሷ ይሄዳል። መቅደላዊት ስለ ባሩክ ሰምታለች ለሴት ባለው ከልክ ያልፈ ድፍረት እና ንቀት ትናደዳለች።ወደ እሷ አቅጣጫ እየመጣ እንደሆነ ስታይ ጉዞዋን ገታ አድርጋ ባለችበት ቆመች ባሩክ እየተጠጋት መጣ ። " ሰላም እንዴት ነሽ መቅደላዊት ባልሳሳት አንቺ ነሽ?" አልተሳሳትክም ፈላስፋው ባሩክ እስጢፋኖስ " አለች መቅደላዊት በጥላቻ አይን እየተመለከተችው " ወይ ይቺ አለም ምን አይነት ሰወች ነን የምንኖርባት ግን? ብሎ ከራሱ ጋ አወራ እና "መቅደላዊት የአንቺ እንዲህ መሆን የኔ ጉዳዬ አይደለም እንኳን አንቺ በህይወቴ ላይ ቅንጣት ታህል ቦታ የሌለሽ ሴት ይቅርና በህይወቴ ውስጥ ሰፊ ቦታ ያላቸው ሰወች እንኳ ምንም ቢሉ ግድ አይሰጠኝም ።እዚህ የመጣሁት የአንቺን የተዘፈዘፈ ፊት ለማየት አይደለም ለዚህም ብየ የምጠቀምበትን ጊዜየን አላጠፋም ።አውቃለሁ የዚህ ጊቢ ሴቶች በእኔ በኩል ጤናማ አመለካከት የላችሁም።እሱ ለእኔ ምይም ነው ሰው እንዲወደኝ አለያም እንዳይጠላኝ ሀሰት የምሸርብ ሰው አይደለሁም።እስከሚገባኝ እና እስከማውቀው አንቺ በእኔ ላይ የምትናደጅበት አመክንዮ አለ ብየ አላስብም ።ምን አልባት በሌሎቹ ጓደኞችሽ ካልሆነ። አሁን እሱን ልተወውና የመጣሁበትን ብየሽ ልሂድ ምን አልባት በሀሳብ ላንግባባ እንችላለን በሚል እሳቤ የምታደርጊውንና የምታደርጊውን ምክንያት ፣ ውጤት በተገቢው ሁኔታ እዚህ ደብዳቤ ላይ አስፍሬልሻለሁ። እኔ እና አንቺ የተለያየን አመለካከት እንዳለን አውቃለሁ ግን በናሆም ጉዳይ አንድ ነን ።እርዳታየን የጠየቀኝ ናታኔም ነው። ፖስታውን ስታነቢ ማንም እንዳያይሽ ተጠንቀቂ በተረፈ ቀጣይ እሁድ ናሆም የሚሳተፍበት የስነፅሁፍ ምሽተሰ አለ ከፈለግሽም ሀሙስ የሂስ ምሽት አለ መምጣት ትችያለሽ " አለ እና ባሩክ ትቷት ሄደ ። መቅደላዊት ለተወሰነ ርቀት እስኪሄድ በአይኗ ከሸኘችው በኋላ ስልኳን አውጥታ ወደ ናታኔም ደወለች " አቤት መቅዲ " አለ ናታኔም " አልገባኝም ናታኔም ምን እያሰብክ እንደሆነ ለምንድነው በዚህ ጉዳይ ላይ ባሩክን ያስገባኸው? በእኔ ስለማትተማመን ነው? ወይስ ሌላ ያሰብከው ነገር አለ? " አለች " ለዛ አይደለም አንቺ እንዳሰብሽው አይደለም። ታቂያለሽ አንቺ በዚህ ጉዳይ ላይ ተዋናይ እንጅ ፀሀፊም ዳይሬክተርም ተዋናይም እንዳትሆኚ ብየ ነው። ጊዜሽን እንዳይወስድብሽ ከትምህርትሽ እንዳትዘናጊ በዛ ላይ ባሩክ አሪፍ የማንበብ ልምድ እና የማስተዋል አቅም ስላለው ናሆምን በቀላሉ ለማጥመድ ይቀለናል ። ከዚህ በኋላ ባሩክ የሚሰጥሽን ስክሪፕት ናሆም ላይ መተወን ብቻ ነው የሚጠበቅብሽ ። ገባሽ አይደል መቅዲ? " አለ አወ ገብቶኛል ጥሩ ያሰብክ ይመስለኛል ። ባሩክ ግን ደስ ስለማይለኝ ነው " አለች " አውቃለሁ መቅደላዊት ስለ ባሩክ ጥሩ ያልሆነ አመለካከት እንዳላችሁ አውቃለሁ ግን ባሩክን አውቀዋለሁ የሰፈሬ ልጅ ነው የዚህን አላማም እንደነገርኩት ሳያቅማማ ስለተቀበለኝ ነው።" አለ " እሽ በቃ የሆነ ፖስታ ነገር ሰጥቶኛል ከአነበብኩት በኋላ እናወራለን ደግሞ እረስቼው ናሆም እሁድ የስነፅሁፍ ምሽት ላይ ግጥም ያቀርባል።" " ማን ነገረሽ? " " ይሄ ባሩክ ተብየህ ነዋ መረጃው እውነት ይሁን አይሁን የማውበው ነገር የለኝም " አለች " ባሩክ ባሩክ ካሰብኩህ በላይ ስራየን እያቃለልክልኝ ነው " አለ ናታኔም ጮሆ። " ማንነው ስራህን የሚያቃልልልህ? አለ በሩን ከፍቶ እየገባ። ናታኔም ደንግጦ ቆመ........


꧁༺༒༻꧂


🌺ክፍል አስራ ስምንት ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @loverrtime
የፍቅር ጊዜ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄


° 🤱 መልካም የእናቶች ቀን 🤱




https://vm.tiktok.com/ZMe49DE1w/

እስቲ እሄን የtiktok ሊንክ በመጫን👈 follow , like & share ♥️በማድረግ ተዝናኑልኝ ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች🌺🌺
Mengistu Abshiro (@mengisteab) on TikTok
Mengistu Abshiro (@mengisteab) has created a short video on TikTok with music original sound. | 🤣🤣🤣🤣


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም ፥ የደስታ ፥ የፍቅር ፥ የመተሳሰብ እንዲሆንልን እንመኛለን።

ዋው ብራንድ ፋሽን የሁላችን


✝ መልካም የትንሳኤ በዓል ✝



Показано 20 последних публикаций.

43 992

подписчиков
Статистика канала