.
መ ቅ ደ ላ ዊ ት 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣
♥️ ክፍል 19
◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Ambaye Getahun
ምን ያልገባሽ ነገር አለ ? ከጣፍኩልሽ ውስጥ? " ዝምታውን ለመስበር እና የውይይት መጀመሪያ እንዲሆን አስቦ ባሩክ የጠየቀው ጥያቄ ነበር። " ሀሳብህ በጣም ከባድ ነው እኔ ያን ማድረግ አልችልም እዚህ እኔን የሚያውቁኝ ብዙ ናቸው ። ቤተሰቦቸንም የሚያውቋቸው ተማሪዎች አሉ። አንተ ያልከውን ባደርግ እና ብል ያለ ጥርጥር ቤተሰቦቼ ጋር እቀያየማለሁ በስስት የሚያየኝን እና የሚወደኝን አባቴን እስከመጨረሻው አጣዋለሁ። እናም በጭራሽ አልችልም። ወይ ለዚህ ሀሳብህ ሌላ ሴት መፈለግ ሳይኖርብህ አይቀርም ።" አለች " የሀሳቡ አመንጪ እኮ እኔ አይደለሁም ይሄን የስነልቦና ህክምና የጀመራችሁት አንቺ እና ናታኔም ናችሁ። እኔን በተወሰነ መልኩ እንድረዳችሁ ጠይቆኝ ነው። እናም በዚህ ምክንያት የዚህ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጇ አንቺ ስለሆንሽ ነው ይሄን ሀሳብ የሰጠሁሽ እንጂ አንቺ እምቢ ብለሽ ለሌላ ልሰጠው የምችለው የፊልም ስክሪፕት አይደለም። " አለ ባሩክ " አይ እኔ እኮ እምቢ ያልኩት ሀሳብህ ከባድ ስለሆነ ነው ። " አለች " ምን መሰለሽ መቅደላዊት ለከባድ ገጠመኞች ለከባድ ችግሮች ከባድ ውሳኔ ያስፈልጋል። ለዚህም አሁን ከባዱን ነገር ታደርጊያለሽ።እመኚኝ ስኬታማ ትሆኛለሽ። አውቃለሁ ብዙ ነገር ሊደርስብሽ ይችላል ግን ለዛም መፍትሔ እናስቀምጣለን።" አለ ባሩክ እጆቿን እየጨበጠ " እንደ እውነቱ ከሆነ ጥሩ ልብ አለሽ ከቅንነት ጋ ከውብ ቁንጅና ጋ ይሄን ባለኝ መረጃ እና በደቂቃዎች ለመረዳት ችያለሁ ።ሰወች ደግሞ ትክክለኛ ነገር አስበው ከሄዱ ከሚጓዙበት የእውነት መንገድ ማንም ሊመልሳቸው ሊያሰናክላቸው አይችልም ይህ የተፈጥሮ እውነት ነው።መጨረሻው መጨረሻ መሆን እንዳለበት ይሆናል። ናሆም ላይ ለእንዲህ አይነት የስነልቦና ችግር በመጋለጡ እኔ በጣም ነው ያዘንኩት ማንም ሰው እንዲህ አይነት ችግር እንዲደርስበት የሚፈልግ የለም እስከማቀው ድረስ አትጠራጠሪ እሱ ላይ የደረሰበት ችግር እኔ ላይ አለያም አንቺ ላይ ቢደርስ የምናደርገው እሱ ከሚያደርገው ቢበልጥ እንጅ አያንስም ። እሱስ ባይሆን ከላይም ቢሆን እናቱን ያወራታል እሷ ጋ ይኖራል ከዚህ በላይ እኮ ምህረት የለም። ግን ደግሞ እናቱ ነች ስለዚህ ለጥላቻው ገደብ ልናበጅበት ይገባል ይቅር ማለትን ልናስተምረው ይገባል። አለዚያ ከባድ ነው"አለ ባሩክ። " ካልክ እሽ ግን ውስጤን ልክ አይደለም እየተሰማኝ ያለው።" አለች መቅደላዊት " አሁን ለስነፅሁፍ ምሽቱ ተዘጋጅ እኔም ወግ ነገር ስለማወጋ መለማመድ አለብኝ በይ ተነሽ ልሸኝሽ አለ እና ቀድሞ ብድግ አለ ።
ናሆም አቢሲኒያ ስታዲየም በክቡር አቶ ይድነቃቸው መቀመጫ በኩል ጫፍ ላይ ከአንዲት ግራር ዛፍ ስር ሆኖ በየደቂቃው ይጥፋል ፣ይቀደዳል ፣ ይጥላል። ቀዶ በጣላቸው ወረቀቶቹ ተከቦ ራሱን ይዞ ቁጭ ብሏል። ከእንደገና ራሱን ለቀቅ አድርጎ ዙሪያውን ሲመለከት ከአንዲት ቁራጭ ወረቀት ላይ ያፈጣል። ወረቀቱ ላይ የተጀመሩ ቃላቶች አሉ።
"የዘራውን ሲያጭድ ይኖራል አለሜ፣
እማ ነች ቅኝቴ እናቴ ናት ህልሜ"
ስንኟን ደጋግሞ አነበባት ማን ይሆን ማን ትሆን ይሄን ስንኝ የሰደረችው የሰደረው? ስንኟ የተፃፈችባትን ወረቀት ኪሱ ውስጥ አስገባት። ይሄን የፃፈው ሰው በምን አይነት ጥልቅ የእናት ፍቅር ውስጥ ይሆን? ምን አለ እኔም እናቴ እንዲህ እንዳደርግ ብትፈቅድልኝ ለምን አባየን ለምን እኔን ትታኝ ሄደች? ምን አድርጊያት ነው ገና በልጅነቴ የጨከነችብኝ? " ብሎ ራሱን ይጠይቃል። ትዝ አለው አንድ ቀን ትምህርት ቤት የተቋጠረላቸውን ምሳ ተሰብስበው ሲበሉ ሁሉም ጓደኞቹ እናታቸው እንደሰራችላቸው እየተናገሩ ናሆም ግን አባቴ ነው የሰራልኝ ሲላቸው በጣም ተገረሙ ።ነገር ግን ናሆም ከትምህርት ቤት ሲመለስ አባቱን ጠየቀ እናቴ ለምንድነው ትታን የሄደችው? ብሎ ሲጠይቀው ልጄ እኔን ትታ ለመሄድ ምክንያት ሊኖራት ይችላል አንተን ትታ ለመሄዷ ግን ምክንያት ያላት አይመስለኝም ቢሆንም ምክንያት ካላት ደግሞ አንተ ትልቅ ልጅ ስትሆን እናትህ ጋ ሄደህ እማ ምን አድርጌሽ ነው? ትተሽኝ የሄድሽው?"ብለህ ትጠይቃታለህ " አሁን ግን ጥያቄወችህን በሙሉ ተዋቸው እኔ ለአንተ ሁሉ ነገሬን እሰጣለሁ የእኔ ትልቁ ህልም የአንተ ትልቅ መሆን ነው። ስለዚህ በትምህርትህ በርትተህ ወደፊት እኔን እንድታኮራኝ ነው የምፈልገው ።እሽ የኔ ልጅ ደግሞ እኮራብሀለሁ " አለና እያገላበጠ ሳመው። ናሆም ከትዝታ ማዕበል ወጥቶ ጉንጩን ተደገፈ ።ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ " አባቱ እንደነገረው እናቱ ለምን ጥላው እንደሄደች አልጠየቃትም ። ግን ደግሞ መጠየቅ የምችለው አሁን አይደለም ብሎ ያስባል። ይህን እያሰበ እያለ ሀሳብ መጣለት እና ወረቀቱን አውጥቶ መፃፍ ጀመረ። ለስአታት ቀና ሳይል ከፃፈ በኋላ ። ጨርሶ በደስታ ፈገግ አለ ደግሞ ደጋግሞ አነበበው። " "ሸጋ ግጥም" አለ በለሆሳስ.....
꧁༺༒༻꧂
✎ 🌺ክፍል ሃያ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @loverrtime
የፍቅር ጊዜ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄