ሰላም የmaf digital ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ዛሬ ወደተለያዩ ዌብሳይቶች ስትገቡ የተለያዪ በቁጥር የተገለፁ ከላይ በፎቶ እንዳስቀመጥኩላችሁ errors ምልክትን ይመጣሉ ማለትም ለምሳሌ 507 error ሊላችሁ ይችላል ይሔም ማለት ያንን ዌብሳይት ለመጠቀም በቂ storage የላችሁም ለማለት ነው በዛሬው ፅሁፋችን የ error አይነቶችና ትርጉማቸውን እናያለን ✅
በዞዎቻችሁ እነዚህ error ሲመጡ ደጋግማችሁ ትሞክራላችሁ ነገር ግን በerror መሰረት ያንን እስካላስተካከላችሁ ድረስ ምንም የምታገኙት ነገር አይኖርም ለሌላ ጊዜም save አድርጓቸው ⚠️. 400 (Bad request)
- ይሔ error የሚመጣባችሁ ብዙ ጊዜ የተሳሳተ ነገር ካስገባችሁ ለምሳሌ link, letter ሊሆን ይችላል ስለዚህ 400 error ካላችሁ ያስገባችሁትን ነገር በደንብ ቼክ አድርጉ
⚠️ 401 (Authorization required)
- ይሔ ችግር ከገጠማችሁ ያልተፈቀደላችሁ ቦታ እየባችሁ ነው ማለት ነው የሆነ private የሆነ ነገር ላይ login ስታደርጉ ወይም expired ባደረገ link ስትገቡ ይመጣባችኋል
⚠️
402 (Payment required) ➡️ይሔ ግልፅ ነው ክፍያ የሚጠይቁ ቦታዎች ላይ ሳትከፍሉ ለመግባት ስትሞክሩ ይመጣባችኋል
⚠️
403 (Forbidden) ➡️ ለጠየቃችሁትን resources ፍቃድ ካላገኛችሁ ይሔ ይመጣል
⚠️404 (Not found)
➡️ይሔ የጠየቃችሁት resources server ላይ ካልተካተተ ወይም ከሌለ ይመጣል ስለዚህ ይሔ ከመጣ የጠየቃችሁት ነገር የለም ደግማችሁ በመጠየቅ ጊዚያችሁን አትጨርሱ
⚠️
405 (Method not allowed)➡️The server recognizes the request method (like GET, POST, PUT, DELETE) but the method is not allowed for the requested resource. This occurs when the client uses an HTTP method that the server does not permit for that particular URL or resources
ስለዚህ በምትሞክሩበት ሰአት መጀመሪያ ያንን ለማድረግ ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም የሚለውን ማጣራት አለባችሁ ለምሳሌ የትምህርት መፅሐፍ ተፈልጎ የፍቅር መፅሐፍ ብትልኩ 405 ትባላላችሁ
⚠️
406 (Not acceptable)➡️የጠየቃችሁት resource አለ ግን በእናንተ እና በserveru መካከል አለመስማማት ሲኖር ይሔ ይፈጠራል ለምሳሌ የጠየቃችሁት እናንተ በXML format ቢሆንና serveru የሚያገኘው በJSON format
⚠️
407 (Proxy authentication required)
➡️ ይሔኛው ከ401 ጋር ተመሳሳይ ሲሆን proxy server መካተቱ ነው የሚለየው
⚠️
408 (Request Timeout)
➡️ይሔኛው ብዙ ጊዜ የሚከሰተው serveru ከደንበኞች የሚቀበለው ጥያቄ ሙሉለሙሉ ካልተቀበለ ከዘገየ ሲሆን የኢንተርኔት ደካማ መሆን ለእንደዚህ አይነት የerror ምልክቶች ይዳርገናል
⚠️
409 (Conflict)➡️ይሔኛው ብዙ ጊዜ የሆነ ፋይል ለማስገባት ፈልጋችሁ ወይም ስም ለመስጠት ፈልጋችሁ መጀመሪያውኑ serveru ላይ የነበረ ነገር ከሆነ ይሔ ይመጣባችኋል ለማስተካከል የተለየ ስም መጠቀም ወይም ሌላ ፋይል መላክ ይኖርባችኋል
⚠️
410 (Gone)➡️የጠየቃችሁት ፋይል ሙሉለሙሉ ከserveru ላይ እንዲጠፋ ተደርጎ ከሆነ ይሔ ይመጣል ይሔኛው ከ404 የሚለየው የጠየቃችሁት ፋይል በፋይሉ ደካማነት ምክንያት ተወግዷል ነው 404 ግን የለም የሚለውን ነው የሚያመለክተው
የሆነ website ላይ search አድርጋችሁ 410 error ከመጣ ፋይሉ ጠፍቷል የለም ማለት ነው ደግማችሁ አጠይቁ
⚠️
411 (Length required)➡️ይሔኛው serveru content-length header እየጠበቀ ነገር ግን ደንበኛው ወይም ተጠቃሚው ሳያስገባ ሲቀር የሚመጣ error ነው
⚠️
413 (Request entity too large)➡️ይሔ የሚመጣባችሁ የላካችሁች ፋይል serveru መጠቀም ከሚችለው በላይ ሲሆን ነው ስለዚህ ፋይሉ የተቀነሰ ማስገባት ይኖርባችኋል
⚠️
414 (Request URI too large)
➡️error 414 የሚመጣባችሁ በጣም ረጅም የሆነ URL ስትልኩ ነው
⚠️
415 (Unsupported media type)➡️ይሔኛው ለምሳሌ እናንተ የJSON file ብትልኩና serveru የሚቀበለው የXML file ከሆነ ይመጣል ስለዚህ serveru ከሚጠይቃችሁ ተመሳሳይ የሆነ file format አስገቡ
⚠️423 (Locked)
ይሔ በሌላ ተጠቃሚ የተቆለፈን ፋይል ወይም ዶክመንት ኢዲት ለማድረግ ከሞከራችሁ ይመጣል ስለዚህ እስኪከፈት መጠበቅ እንዳትረሱ
⚠️
500 (Internal server errorይሔኛው ከሌሎቹ የሚለየው 505 error የሚል ከመጣባችሁ አንድ ልክ ያልሆነ ነገር አለ የሚለውን ሲያመለክት በግልፅ የቱ እንደሆነ ሳይታወቅ ሲቀር ይመጣል ስለዚህ ይሔ ችግር ከመጣባችሁ ደግማችሁ በጥንቃቄ መግባት ትችላላችሁ
⚠️
501 (Not Implemented)➡️ ይሔኛው ፍቃዱ ሳይኖራችሁ serveru ላይ post put delete ለማድረግ ስትሞክሩ ይመጣል ይሔ ስህተት ከሰርቨር የሚመጣ ነው
⚠️
502 (Bad gateway)
➡️ይሔ error የሚመጣው ሁለት websiteችን ለመጠቀም ፈልጋችሁ በሁለቱ መካከል የግንኙነት ችግር ሲኖር ነው
⚠️
503 (Service unavailable)
➡️ይሔ error የሚመጣው ለመግባት እየሞከራችሁበት ያለው server በዛ ሰአት ላይ እየሰራ ካለሆነ ዘይም maintenance ላይ ከሆነ ነው ስለዚህ ቲንሽ ቆይታችሁ መመለስ ጥሩ ነው
⚠️
507 (Insufficient storage)
➡️ይሔ መጠቀም ለፈለጋችሁት ሰርቨር በቂ ቦታ ከሌላችሁ ወይም insufficient storage ከሆነ ይመጣል
✅
በጥቂቱም ቢሆን እንደሚጠቅማችሁ save 👌📱
በMaf digital ቴሌግራም ቻናል የተዘጋጀ