Репост из: ✟ ጋሜል- ዘ ኦርቶዶክስ ✟
🏵 እንኳን ለዕለተ ብርሃን አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
------------------------------------------------------------
🌟 † ዕለተ ብርሃን † 🌟
➦ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስንና የቅዱስ ያሬድን አስተምሕሮ መሠረት አድርጋ ይህንን ዕለት (ታኅሳስ 14ን) "ዕለተ-ብርሃን" : ሳምንቱን (ከታኅሳስ 14-20 ያለውን) ደግሞ "ሰሙነ-ብርሃን" ስትል ታስባለች።
➦ "ብርሃን" በቁሙ የእግዚአብሔር ስሙ: አንድም የባሕርይ ገንዘቡ ነው። "እግዚአብሔር ብርሃን ነውና። ጨለማም በእርሱ ዘንድ የለችምና።" ዮሐ. 1:4 ~በዚህ ዕለት "ብርሃን" በሚል መነሻ ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ታስተምሠራለች:-
1.እግዚአብሔር ብርሃን መሆኑን። ዮሐ. 1:5
2. አምላካችን በመጀመሪያው የፍጥረት ቀን (በዕለተ እሑድ) ዲያብሎስ ቅዱሳን መላእክትን ሲረብሽ "ለይኩን ብርሃን" ብሎ ብርሃንን መፍጠሩን። ዘፍ. 1:2, አክሲማሮስ
3.ነቢያት አበው በጨለማው ዓለም ሆነው መከራ ሲበዛባቸው "ፈኑ ብርሃነከ - ብርሃንህን ላክልን" እያሉ መጮሃቸውን። መዝ. 42:3
4.ጩኸታቸውን የሰማ ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ (እውነተኛው ብርሃን) ወደዚህ ዓለም መምጣቱን። ሉቃ. 1:26
5."እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ" ሲል የባሕርይ ብርሃንነቱን እንደ ነገረን። ዮሐ. 9:5
6.ብርሃነ መለኮቱን በገሃድ መግለጡን። ማቴ. 17:1
7.ብርሃን የሆነችውን ሕግ: ወንጌልን እንደ ሠራልን። 1ዮሐ. 2:9
8.ድንግል እመቤታችን ብርሃን : የብርሃንም እናቱ መሆኗን። ሉቃ. 1:26, ራዕ. 12:1
9.ቅዱሳኑ ብርሃን መባላቸውን። ማቴ. 5:14
10.እኛ በሰው ፊት ሁሉ እንድናበራ መታዘዛችን። ማቴ. 5:16 ሁሉ ይታሰባል።
🌺 እርሱ ፈጣሪያችን ክርስቶስ ጨለማውን በምሕረቱ አርቆልናልና ዳግመኛ ወደ ጨለማ እንዳንሄድ እየለመንን እናመስግነው።
"ክርስቶስ ብርሃን ዘአሰሰልከ ጽልመተ።
ላዕለ ኪሩቤል ነቢረከ ዘትሬኢ ቀላያተ።
ስቡሕኒ ወልዑል አንተ::" (መልክአ ኢየሱስ)
🌟✝️ ዕለተ ብርሃን ✝️🌟
💚 @maedot_ze_orthodox
💛 @maedot_ze_orthodox
❤️ @maedot_ze_orthodox