ማናአስ ሲገብ ፍርሀታቸው ከላያቸው ላይ ረግፎ ...የድል ብስራት ፈንጠዝያ ልባቸውን ሲያሞቀውና ...በሀሴት ነፍሳቸው ስትደንስ እየታያቸው ነበር፡፡ በእኩለ ለሊት ለስድስት ቀን ተኩል ከተጓዙበት ጀልባ ወርደው የከሳ አካላቸውንና የወፈረ ተስፍቸውን ይዘው የወረዱት፡፡ቀጥታ ወደከተማዋ መካከል ተጓዙ።ከተማዋም ልክ እንደእነሱ ደምቃና በቀለማት አሸብርቃ ነበር።ልክ እነሱን በፈንጠዝያ ለመቀበል እንዲህ ጠብ እርግፍ ብላ ተዘጋጅታ ያማረች ሙሽራ ነው የምትመስለው ።
እንደምንም የሚያረፍበት ቤርጎ ፈልገው ያዙና ተከራይተው ወደውስጥ ገቡ፡፡ እቃቸውን አራግፈው አስቀመጡ፡፡እሷ ፈጥና ስልኳን እና ቻርጀሯን አወጣችና ሰከችው፡፡ነፃ መውጣቷን ለወንድሞ ደውላ እስክትግረው እና ድምፁንም አስክትሰማ ቸኩላለች፡፡ስልኩን ከሰካች በኃላ ወደአልጋው ሄዳ ቁጭ አለች..ከርሎስም ከጎኗ ተቀመጠ፡፡
‹‹ምንድነው አንተ ከተማዋ እንዲህ ያሸበረቀችው?"ስትል በመንገዷ ያየችውን ነገር ካርሎስን ጠየቀችው።
"ገና በዓልን ለማክበር ነው እንዲህ ሽር ብትን የምትለው...በየአመቱ በዚህ ጊዜ የተለመደ ነው።››
"ውይ ገና ደረሰ ማለት ነው?"
"ታከብሪ ነበር እንዴ?"
"ገናን እንኳን በተለየ ሁኔታ አላከብርም..ግን በሀገሬ ኢትዬጰያ ከ10 ቀን በኃላ የሚከበረውን የጥምቀት በአል ነው በተለየ ሁኔታ የማከብረው።ታውቃለህ አሁን እግዚያብሄር ፈቅዶ እዚህ ከደረስኩ ተጨማሪ ቀናቶችን ማባከን አልፈልግም ....ቀጥታ ወደሀገሬ ሄጄ ከእንዳልኩህ መጪውን የጥምቀት በዓል በሀገሬ ምድር ላይ ከወንድሜ ጋር ማክበር አለብኝ።››
‹‹እና በሳምንት ውስጥ ትሄጂያለሽ ማለት ነው?"ሲል በቅሬታ ጠየቃት።
"አይ ነገ ወደብራዚሊያ ብበር...ከተሳካልኝና ትኬት ማገኝ ከሆነ ከነገወዲያ ወደሀገሬ እበራለሁ..."
"ቆይ ክብረ በዓሉ ሀይማኖታዊ ነው?ማለቴ እንዲህ በትኩረት ልታከብሪው የጓጓሽበት ምክንያት አልባኝም።"
""ሀይማኖተዊነቱ እንዳለ ሆኖ አንድም እኔና ወንድሜ የተወለድንበት የልደት ቀናችን ነው...ሁለተኛው ደግሞ እናትና አባታችንን በሞት የተነጠቅንበት ቀን ነው። በዚህም ምክንያት ግማሽ ደስታ ግማሽ ሀዘን...ከፊል ሳቅ ከፊል ለቅሶ የምናለቅስበት ቀን ነው።በእንደዛ አይነት ቀን ወንድሜን ብቻውን እንዲሆን ማድረግ አልችልም።ለቅሶውንም አብሬው ማልቀስ ሳቁንም ከእሱ ጋር መሳቅ ነው የምፈልገው።››
ካርሎስ ለረጅም ደቂቃ በትካዜ ዝም አለና"አሁን ደስታዬ ሁሉ ጥሎኝ በነነ"አላት፡፡
ደንግጣ በመሀከላቸው ያለውን ክፍተት አስወግዳ ወደእሱ ተጠጋችና "ምነው? ምን ተከሰተ?"ስትል ጠየቀችው።
"እኔ እንጃ አንዳንድ ነፃነት አዙሮ አዙሮ እጦትና ቦዶነት ላይ ነው ሚጥለን… አሁን ነው ያወቅኩት።እንደዚህ ጥልቅ ብቸኝነትና የሚሸረካክት የእጦት ስሜት እንደሚሰማኝ ባውቅ ኖሮ ምን አልባት እዛው የአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ እየዟዟርን ዘላለማችንን እንድንኖር አደርግ ነበር"
አንተ ምን አይነት ክፉ ነህ..ትከሻውን በፍቅር ነቀነቀችውና ወደራሷ ጎትታ ጉንጩን ሳመችው፡፡ ወደኃላዋ ስትመለሰ መልሶ ጎተተና ከንፈሯ ላይ ተለጠፈባት፡፡ ...በቀላሉ ሊላቀቁ አልቻሉም፡፡ ተያይዘው አልጋው ላይ ወደኃላቸው ተዘረሩ ፡፡ከዛ ለመጀመሪያ ጊዜ በምቾት በሚያነጥረው አልጋና በሚለሠልሰው ፍራሽ ላይ ለስላሳ ፍቅር ሰሩ...በሁለቱም ምናብ በተሻለ ምቹ ቦታ ፍቅር መስራት የተሻለ እርካታ ያስገኛል የሚል ስሌት ነበራቸው።ግን እንደዛ አይደለም ...እንደውም ከስቃይ የተለወሰ ተራክቦ ልዩ እና ቸኮሌት አይነት ጣዕም አለው።

ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️