ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አምስት
ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ለመጀመሪያ ጊዜ የቀኝ እጇ የመሀል ጣት ተነቃነቀ…እቤቱ ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ በደስታ ፈገገ ..ከአስር ደቂቃ በኃላ አይኖቾ ተከፈቱ፣አራቱም የቤቱ አባላት የተኛችበትን ፍራሽ በሁሉም አቅጣጫ ከበው በፈገግታ ያዩት ጀመር….ግራ ገባት፡፡መልሳ አይኖቾን ጨፈነች…፡፡መንቃቷ እራሱ የእውነት ሳይሆን በህልም አለም ውስጥ የተፈጠረ መንቃት ነው የመሰላት ፡፡ለዛ ነው ዳግመኛ እይኖቾን የጨፈነችው..፡፡መልሳ ስትገልጥ ያየችው ተመሳሳይ ነገር ነው….አራት ወዛቸው የተመጠጠ የለበሱት ልብስ የነታተበ ..በአባቷ ግቢ ውስጥ አትክልቶችን ከሚንከባከቡ ሰራተኞች በላይ ኑሮ የጠበሳቸው ጠና ያሉ ሰውዬ…ቆዳቸው የተሸበሸበ እናት… የ ሀያ አመት ልጅ እግር የምታምር ግን ደግሞ ያልተመቻት ልጃገረዶች..ባለጡንቻ ፈርጣማ እና ባለኮስታራ ፊት ሀያ አምስት ወይም ስድስት የሚሆነው ወጣት ..ጭስ የጠጣና ያረጀ የማዳበሩያ ኮርኒስ ያለው ጠባብ ክፍል…መሬት ላይ የተነጠፈ ፍራሽና ያረጀ በህይወቷ እንኳን ለብሳው አይታው የማታውቀው አይነት ብርድ ልብስ ለብሳ ነበር እራሷን ያገኘችው፡፡ግን እንደዛም ሆኖ የተለየ እና የማታውቀው ቦታ ያለች መስሎ አልተሰማትም….የሆነ ከዘመናት በፊት ታውቀው የነበረ እና ስትናፍቀው የቆየችው ቦታ ተመልሳ እንደመጣች አይነት ስሜት ነው እየተሰማት ያለው
‹‹…የት ነኝ?››
‹‹ልጄ…አሁን ሰላም ነሽ …ትንሽ አደጋ ደርሶብሽ ነው?››
‹‹የምን አደጋ?››
‹‹አሁን ሰላም ነሽ..በውድቅት ለሊት ሞተር ስትነጂ ነበር…ተገልብጠሸ ነው፡፡››
‹‹ሞተር››
‹‹አዎ..ሞተር..ከማን ስትሸሺ ነበር….?እስከአሁን ለፖሊስ አላሳወቅንም…..ይሄውልሽ እኔና ቤተሰቦቼ በህይወት ፈተና ጋር ግብግብ ገጥመን በትግል የምንኖር ሰዎች ነን…ከሆነ ወንጀል ጋር የተያያዘ ታሪክ ካለሽ እባክሽ.እኛንም ጣጣ ውስጥ እንዳንገባ ከአሁኑ ንገሪን››ሲል ፊራኦል ተናገረ፡፡
‹‹ምነካህ ልጄ? ልጅቷ ገና አሁን መንቃቷ ነው…ተው እንጂ ነውር ነው›እናትዬው ገሰፁት..አባትዬውም ለባለቤታቸው ድጋፍ በመስጠት‹‹ልጄ አዎ..አሁን ዋናው ያንቺ መትረፍ ነው ፡፡ሌላውን ቀላል ነው…የሰው ልጅ በህይወት ካለ የማያልፈው መከራ የማያሸነፍው የህይወት ትግል የለም..አሁን አንቺ ምንም አታስቢ..እኔነኝ የተባለ ውጌሻ ጠርቼያለሁ፡፡ ወለምታ ወይም ስብራት ነገር ካለሽ ያዩልሻል…ከዛ ካገገምሽ በኃላ ለቤተሰቦችሽ እንደውልላቸውና መጥተው ይወስዱሻል››
በፀሎት ለሊት በውድቅት ለሊት ከቤቷ አምልጣ እንዴት እንደወጣችና ምን እንዳደረገችና አሁን ያለችበት ቤትም የእነማን እንደሆነ ትዝ እያላት ሲመጣ ….የመረጋገትና የደስታ ስሜት ተሰማት‹‹አመሰግናለሁ…ምንም ወንጀል አልሰራሁም….ፖሊስም እየፈለገኝ አይደለም…አሁን ደክሞኛል ልተኛ..››አለችና መልሳ አይኖቾን ጨፈነች፡፡
‹‹ሰማችሁ አይደል..ምንም ወንጀል አልሰራሁም ብላለች..አሁን ዞር በሉላት …ትንፋሻችሁ እራሱ በሽታ ነው የሚሆናባት››አባትዬው ተቆጡ፡፡
‹‹አባዬ ደግሞ ፣አንተ ሁል ጊዜ ሰው እንዳመንክ ነው.. ሚገርመው ደግሞ ሰዎች ቃላቸውን እያጠፉ አንተን ማሳዘናቸውን አያቆሙም… አንተም ደግሞ ደግመህ አደጋግመህ እነሱን ማመንህን አታቆምም››ፊራኦል ተነጫነጨ፡፡
‹‹ልጄ ገለባ ቢዘሩት አይበቅልም ተጠራጣሪ ሰው አይፀድቅም ይባላል..ያገኘሁትን ሰው ሁሉ በመጠራጠር ህይወቴን ሳሰቃይ ከመኖር እያመንኩ ብከዳ ይሻለኛል…ቢያንስ በማመኔ ምክንያት የሚደርስብኝ ችግር ምክንያቱ እኔ አይደለሁም..››
ፊራኦል በወላጆቹ ውሳኔ ባለመስማማት ‹‹በሉ እሺ እኔ ወደ ስራ ሄጃለሁ፡፡››በማለት ቤተሰቡን ተሰናብቶ ግቢውን ለቆ ሲወጣ በራፍ ላይ ውጌሻዋ ወደውስጥ ስትገባ ተላለፉ፡፡
‹‹ቤቶች አቶ ለሜቻ››ሁሉም ግር ብለው ወጥተው ውጌሻዋን ተቀበሉና ወደውስጥ አስገቧት፡፡
‹‹የትኛው ልጅህ ነች… ለሜቻ?››
‹‹የወንድሜ ልጅ ነች ከድሬደዋ ልትጠይቀኝ መጥታ ነው››
‹‹እና ምን ገጥሟት ነው?››
‹‹ባኮት ከሆነ የሰፈር ልጅ ጋር ሞተር ተፈናጣ ስትሄድ ሞተሩ ተገለበጠባቸውና ትንሽ ተጎዳች..ምን አልባት ስብራት ወይም ወለምታ ይኖራት እንደሆነ ብለን ስለተጠራጠርን ነው ያስቸገርኖት፡፡››
በፀሎት የሚነጋገሩትን ሁሉ አይኖቾን ጨፍና እየሰማች ነው…
‹‹ታዲያ ተኝታለች?››
‹‹አሁን ነቅታ ነበር…እንዴት ነው እንቀስቅሳት?››ወ.ሮ እልፍነሽ ጠየቁ፡፡
‹‹አይ ቆይ ተዋት ..ህመሙ እራሱ ይቀሰቅሳታል፡፡››አሉና ስሯ ፍራሽ ላይ ተቀመጡ…
‹‹ እስቲ እሱን የከሰል ፍም አቅርቡልኝ››ትዕዛዝ ሰጡ፡፡
ማንደጃው ቀረበላቸው…‹‹ እስኪ አንዳችሁ ኑና የለበሰችውን ልብሷን አውልቁላት…..››ለሊሴ ፈጠን ብላ መጣችና ከላይ የለበሳቸውን ጃኬት… ቦዲ ተራ በተራ አወለቀችላት… በጡት ማስያዣ ብቻ አስቀረቻት ፡፡አንገቷ ላይ ያለው የእጅ መዳፍ የሚያህል አብረቅራቂ እንቁ ፈርጥ ያለበት ጌጥ የሁሉንም አይን በቅፅበት ተቆጣጠረ
….ጆሮዋ ላይም ያንጠለጠለችው የጆሮ ጌጥ ከአንገት ሀብሏ ጋር እንዲናበብ ተደርጎ የተሰራ ለልደት በዓሏ ከአባቷ የተበረከተላት ልዩ አይነት ጌጥ ስለሆን በተለይ የሌሊሳን ትኩረት በደንብ ነው የተቆጣጠረው…ሁሉም ግን አርቴ እንጂ ትክክለኛ ነው ብለው አላሰቡም ነበር፡፡
ውጌሻዋ ቦርሳቸው ውስጥ እጃቸውን ሰደዱና በብልቃጥ ከለጋ ቅቤ ጋር ተለውሶ የተዘጋጀ መዳህኒታቸውን አወጡና ፊት ለፊታቸው አስቀምጠው በሌባ ጣታቸው ዛቅ እያደረጉና በመሀል አጣታቸው ላይ አድርገው በመላ መዳፋቸው ላይ ለቀለቁና ስራቸው በቀረበላቸው የከስል ፍም ላይ ጠጋ አድርገው ሙቀት እንዲያገኝ ካደረጉ በኃላ ከአንገቷ ጀምሮ ትከሻዋን እያሹ መፈተሽ ጀመሩ‹‹ ..ምንም አልሆነችም እስኪ ሱሪዋን አውልቁልኝ››ሌላ ትዕዛዝ ሰጡ..በዚህ ጊዜ አቶ ለሜቻ ከተቀመጡበት ተነሱና ወደውጭ ወጡ..ሴቶቹ እንደምንም
ታጋግዘው የለበሰችውን ጅንስ ሱሪ ከላዮ ላይ አወለቁና በፓንት ብቻ ለውጌሻዋ አስረከቧት
…ውጌሻዋ ተመሳሳዩን እሽት ከጭኖቾ ጀመረው ወደታች መውረድ ጀመሩ…ቀኝ እግሯ ቁርጭምጭሚቷ ጋር ደርሰው ጨበጥ..ጨበጥ ሲያደርጓት ግን ከተኛችበት እንደመብረቅ አጓርታ ተነስታ ቁጭ አለች…ሁሉም በድንጋጤ የሚያደርጉት ጠፋቸው..‹‹አዎ እዚህ ጋር ችግር አለ‹‹አሁን በደንብ አድርጋችሁ ግራና ቀኝ ትከሻዋን ያዟት፡፡››የውጌሻዋን ትዕዛዝ ስትሰማ አይኖቾ በፍራቻ ተጉረጠረጠ፡፡በእድሜዋ መርፌ ለመወጋት እሩሱ በስንት እዝጊዎታና ማባበያ ነው...ታዲያ አሁን እንዲህ ላይቨ በስቃይ ስትፈተን እንባዋ ረገፈ
፡፡እናትና ልጅ ግራና ቀኛ ትከሻዋን አጥብቀው እንዳትነቃነቅ ያዙዋት..ሴትዬዋ እየጨመቁና እያሽከረከሩ ያሾት ጀመር…በህይወቷ ተስምቷት የማያውቀው አይነት ህመም…..ተሰማት..የሆነ መጋዝ ጥርስ ያለው አዞ በሁለት መንጋጋዎች መሀከል እግሮቾን አስገብቶ እያኘካት ነው የመሰላት..እንባዋ ብቻ ሳይሆን ንፍጦም በአፍንጫ ላይ እየተዝረከረከ እንደሆነ ይታወቃታል…ለዛ ግን የምትጨነቅበት ሁኔታ ላይ አይደለችም…..ውጌሻዋ ከ10 ደቂቃ በኃላ የተሰበረውን አጥንት ወደቦታው ከመለሱ በኃላ እንዳይነቃነቅ በቀርከሃ በደንብ አድርገው ከሰሩት በኃላ በፋሻ ጠቅልለው አጠናቀቁ…ከዛ እቃቸውን ሰብስባው ተነሱ…ለሊሴ የራሷን ቢጃማ አለበሰችትና መልሰው አስተኞት፡፡
‹‹እልፍነሽ››
‹‹አቤት እማማ››
‹‹ለሜቻ ድሬደዋ ሀብታም ወንድም አለው እንዴ?