💐💐ክፍል ⓼💐💐
🌿🌿"ጤዛዉ ፍቅሬ"🌿🌿
✍✍(በኑዕማን ኢድሪስ)✍✍❥............🍃💐💐🍃..............❥
...... ፎዚያ የሀምዛን ሚስት (መኪያን) ሀምዛ ትንሽ እንዳመመዉና ሆስፒታል እንደተኛ ቀለል አድርጋ ነገረቻት፡፡ የሀምዛ ሚስት ግን 'የህመም ትንሽ የለዉም፡፡" ብላ የምትይዘዉ የምትጥለዉ ተደናግሯት በፍጥነት ወደ ሆስፒታል አመራች፡፡
.
..... ሀቢብ ጉዳዩን ሁሉ ለሀምዛ ነግሮታል፡፡ ሀምዛ ግን ለነግሩ ክብደትና ቦታ ሳይሰጠዉ ቀለል አድርጎ የራሱን ሀሳብ ይነግረዋል፡፡
.
"የብዙዎቻችን ችግር ምን እንደሆነ ታዉቃለህ?..." ብሎ የሀቢብን አይኖች በአትኩሮት እየተመለከተ ጠየቀዉ፡፡ ሀቢብም ጥያቄዉን ከመመለሱ ይልቅ ሀምዛን በፅሞና ማዳመጡን መርጧል፡፡
..."ሀቢቢ እኔ የቅርብ ጓደኛህ ነኝ፡፡ አንተ ስለኔ እንደምታዉቀዉ ሁሉ እኔም ስላንተ ብዙ ነገር አዉቃለሁ፡፡ ... የሰርጋችሁ ቀን በማግስቱ ስለ አዳራችሁ ስጠይቅህ ሙሉ እንደሆነችና እስከ ክብረ ንጽህናዋ እንዳገኘሃት ነግረኸኝ ነበር፡፡..."
..."አዎ ምን መሰለህ ..." ብሎ የዚያ ቀን ለምን እንደዋሸዉ ሊያስረዳዉ ሲል ሀምዛ የሀቢብን ወሬ አቋረጠዉና፡፡
..."ይገባኛል ጓደኛዬ የዚያን ቀን ለኔም ሆነ ለቤተሰቦችህ የዋሸህዉ የሷን ክብር ለመጠበቅና እሷን ዝቅ አድርገን እንዳናስባት በማሰብህ ነዉ፡፡... (ሀቢብ የዋሸበትን ምክንያት ሀምዛ ስለተረዳለት አንገቱን ወደ ላይና ወደ ታች ከፍ ዝቅ እያደረገ ነቀነቀ፡፡)... አየህ ሀቢብ ትወዳታለህኮ! - ምክንያቱም ለሷ ክብር የምትጨነቅ አሳቢዋ ነህ፡፡..." እያለ ጥሩነቱን ከነገረዉ በኃላ ... " ግን ሀቢብ የተወሰኑ ወራቶችን ችለህና በፍቅር አብረህ ኑረህ ስታበቃ እንዴት አሁን ያ ነገር ትዝ አለህ? ለምን በዚህ ምክንያት ነገር ትቀሰቅሳለህ?፡፡ ያ ያለፈ ጉዳይ አይደለ እንዴ" ብሎ ጠየቀዉ፡፡ ሀቢብ በረጅሙ ትንፋሹን "እህህህህህ...." ብሎ ካወጣ በኃላ፡፡
.
..."ልክ ነህ ሀምዛ...! በወቅቱ ለነገሩ ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር፡፡ ምክንያቱም በጣም ስለማፈቅራት፡፡ እያደር ግን ዉስጤን ይከነክነኝ ጀምር፡፡ ከመጀመሪዉ በጣም እተማመንባት ስለነበር ክብረ ንፅህናዋን ሳይሆን እሷነቷን ነበር የፈለግኳት፡፡ አሁን ግን እሷነቷን ብቻ ሳይሆን እሷነቷን ሙሉ ሁና እስከ ክብረ ንፅህናዋ ማግኘት ፈለግኩ፡፡ በዚህ ምክንያት ለሷ ያለኝ ቦታ ወረደ፣ በፊት የማፈቅራትን ያክል ላፈቅራት አልቻልኩም፡፡ ምክንያቱም ሁሌ ሳስባት ርካሽ መስላ ትታየኛለች፡፡...." ወሬዉን ቀጥሏል በስተመጨረሻም ሀምዛ የሀቢብን የጥላቻ መነሻ ከሰማ በኃላ...
"ሀቢብ አንተ ሙሉ ነበርክ እንዴ? ...ማለቴ አንተ ፎዚያን ስታገባት ክብረ ንፅህና ነበረህ?" ብሎ ጠየቀዉ፡፡
ሀቢብ ጓደኛዉን ለማስረዳት ሲዳዳ ሀምዛ የጥያቄዉን መልስ ራሱ መለሰለት፡፡
..."ሁለታችንም እንተዋወቃለንኮ፡፡ አንተ ለስንት ሴቶች መበላሸት ምክንያት ሆነሃል? ... ስንት እህቶችን እስከ ክብራቸዉ ትዳር እንዳይመሰርቱ አድርገሃል? እና አንተ ስለ ክብረ ንፅህና መጠየቅ ነበረብህን?... ይሄዉልህ ሀቢቢ ክብር የሚገባዉ ክብር ላለዉ ሰዉኮ ነዉ፡፡...." ብሎ ወሬዉን ቀጠለ፡፡ ሀቢብን ብዙ ጠየቀዉ፤ መከረዉ፣ ገሰጸዉ ነገር ግን ሀቢብ ሊዋጥለት አልቻለም፡፡ እንደገና የፎዚያን ክብረ ንጽህና ሊያመጣለት ስለማይችል ሊቀበለዉ አልቻለም፡፡
.
..."ተዉ እንጂ ሀምዛ ...(አለዉ ቆጣ ብሎ)... እኔንና እሷን በምን ስሌት ነዉ የምታወዳድረን? እ?... እሷኮ ሴት ናት፡፡" አለዉ፡፡ ሀምዛ ክብረ ንፅህና የሚባለዉ ነገር ወንድም እንዲኖረዉ፤ ከትዳር በፊት ከማንም ሴት ጋር ግንኙነት ይኑረዉ የሚል እምነት የለዉም፡፡
..."ወንድ ይንዘላዘል ያለዉ ማን ነዉ ሀቢብ? ወንድ ሲበላሽ አብሮ የሚያበላሸዉ ሴትን አይደል?... ወንድም ጥሩ ፤ ሴትም ጥሩ መሆን አለባቸዉ፡፡ መልካም የሆነ ሰዉ መልካምን እንጂ አያገኘም፡፡ ደግሞ ሀቢብ ሁለታችንም የምንስማማበት ነገር አንተ ከትዳር በፊት የነበረህ ህይወት ጥሩ እንዳልሆነ ነዉ፡፡ እርግጠኛ ሁኜ የምነግርህ ግን ፎዚያ ችግሯን ስላልተረዳሃት፤ እንደ ባል ጠጋ ብለህ ስላልጠየቅካት እንጂ ንፁህና ሙሉ ናት የሚል ግምት አለኝ፡፡" ብሎ ፎዚንም በተጠራጠረ አንደበት ነገረዉ፡፡
.
......ዉይይታቸዉ ወደ ክርክር እየተለወጠ ነዉ፡፡ ሁለቱም ሞቅ ብሏቸዋል፡፡ በዚህ መካከል መኪያ .. ሀምዛ ወዳለበት ክፍል ገባች፡፡ የሀምዛን አልጋ ላይ መተኛት ያየች ጊዜ በድንጋጤ እየጮኸች ተጠመጠመችበት፡፡
......" ሀምዛ...." እያለች፡፡
╔═══❖•🌺🌺•❖═══╗
ይቀጥላል
╚═══❖•🌺🌺•❖═══╝
❥............🍃💐💐🍃..............❥
4ur any comments @muke_ye
@maraki_lyrics