💐💐💐ክፍል -9💐💐💐
🌿''ጤዛዉ ፍቅሬ'🌿
✍✍(ኑዕማን ኢድሪስ)✍✍
----------------------------------------------
Like እና Share አድርጋችሁ ጀምሩ

..... 'ሀምዛ... ሀምዛዬ... የኔ ዉድ...' እያለች እጇን እያወናጨፈች ሀምዛ ወደተኛበት አልጋ ሮጠች። ሁለቱ ጓደኛሞች ከልባቸዉ የሆነ ዉይይት ይዘዉ ስለነበር የክፍሉን በር ከፍታ ስትገባ ስላላስተዋሏት 'ሀምዛ' የሚለዉን የመኪያን ጥሪ ሲሰዉ ሀምዛ በተኛበት ፤ ሀቢብ በተቀመጠበት ቦታ ሆነዉ ደንዝዘዉ ቀሩ፤ ክዉ አሉ። ከበሩ አስከ አልጋዉ ያለችዉ ክፍተት መኪያን የአስር ሺ ሜትር ተወዳዳሪ አትሌት አስመስሏታል። ከሰዉነቷ ሁሉ ቀድሞ እንደ ባንድራ የሚዉለበለበዉ እጇ ሀምዛን ለማቀፍ ፤ የሀምዛን ገላ ለመዳበስ ሽተዋል።
.... ሀቢብ ከተቀመጠበት የአልጋዉ ጠርዝ ተነስቶ "ተረጋጊ መኪያ... ምንም'ኮ አልሆነም... አይዞሽ" እያለ ያባብላት ይዟል። እሷ ግን ባሏ አልጋ ላይ ተንጋሎ ስታይ የሞት ጽዋን የሚቀዳጅ እንጂ ተሽሎት የሚነሳ አልመስላት ብሏል። ሀምዛም ..."መኪዬ ደህና ነኝኮ ለምን እንደዚህ ትሆኛለሽ?" ብሎ ሲያናግራት ቀና ብላ አየችዉና "ደህና ነህ የኔ ቆንጆ" እያለች በለስላሳ መዳፎቿ አንዴ አይኑን ከዚያም ጉንጮቹን ትደባብሰዉ ገባች። ... "የኔ ቆንጆ መጀመሪያዉኑም አንች ሶብር አጥተሽ መጣሽ እንጂ እኔኮ ደህና ነበርኩ" ብሎ ይበልጥ ደህንነቱን አረጋገጠላት። ሀቢብም ቀጠል አድርጎ "... ሶብሪ መኪ! ትንሽ ጭረት'ጂ ያጋጠመዉ በጣም ደህና ነዉ" ብሎ አከለላት። የተወሰነ ተረጋግታ ወደ ቀድሞዋ እሷነቷ ተመልሳ ስለክስተቱና ስለሁኔታዉ ጠየቀችዉ። "ቀላል ነዉ...." ብሎ ጀመረና ለፎዚያ እንደነገራት አድርጎ አስረዳት።
....... ሀቢብ እሱ ተረስቶ ባልና ሚስቶቹ ብቻዉን ሲያወሩ 'የምን መፋጠጥ ነዉ?' በሚል አይነት "በሉ እናንተ ተጫወቱ እኔንም ሚስቴ ትጠብቀኛለች!" ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ። ፎዚን ሚስቴ በማለቱ ሀምዛ ደስ አለዉ። ጓደኛዉ የተስተካከለለት ያክል መስሎ ተሰማዉ። ነገር ግን በል ቻዉ ብሎ ቶሎ ሊሰናበተዉ ስላልፈለገ "እኔምኮ ሚስት አለችኝ ማንን ለማስቀናት ፈልገህ ነዉ?" ብሎ እንደመቀለድ ሲያደርገዉ ሀቢብም አጸፋዉን ለመመለስ ያክል ወደ መኪያ እየተመለከተ ..."ሚስቱ ጓደኛዬን አደራ እሺ! በደንብ አስታሚዉ" ብሎ ሁለቱንም በፌዝ ኮርኮም አደረጋቸዉ። መኪያም የዋዛ አለነበረችም ኖሯልና "እንደዉም ቶሎ ዉጣ በሽታዉ እንዳይብስበት ክክክክ..." እያለች በአሽሙር ቢጤ ጎንተል አደረገችዉ። "አሃሃ በሽታዉ እኔ ነኝ ማለት ነዉ!? በሉ ቻዉ" ብሎ ተሰናብቶ ወጣ።
.
.
.... ፎዚያ ሆስፒታል ዉስጥ ሀምዛ የመከራት ነገር ዉስጧ ገብቷል። በሀቢብ በጣም ብዙ ጊዜ ተስፋ ልትቆርጥ ቋፍ እየደረሰች 'እስኪ ዛሬን ልየዉ' በሚል ተስፋ ዛሬን ደርሳለች። አሁን ደግሞ የሀምዛ ምክር ተስፋዋን ይበልጥ አለመለመላት ፤ ፍቅሯን የመለሰላት አስኪመስላት ድረስ መንፈሷን ጠገነላት።
መኝታ ቤቷ ዉስጥ እንደ አክሱም ሀዉልት የተገተረዉን ቁም ሳጥኗን ከፍታ የቱን ለብሼ ተዉቤ ልጠብቀዉ ፤ ጸጉሬን እንዴት አድርጌ ላስይዘዉ እያለች 'ተዉበሽ ጠብቂዉ' የሚለዉ የሀምዛ ቃል እንደ ገደል ማሚት በጭንቅላቷ ወስጥ እያቃጨለ እንደተቀጠረ ሰአት ያስታዉሳት ይዟል።
..
.... ጠጠር የመሰለችዉ ድንጋይ ስታደናቅፈዉ ከእንቅልፉ እንደተቀሰቀሰ ሰዉ ብትት አለ። ታክሲ የሚሳፈርበትንም ቦታ አልፎት ብዙ ተጉዟል። ለካ መንገዱን ሁሉ ስለ ፎዚ ነበር የሚያስበዉ። ስለ'ሷ ብቻ ነበር የሚያልመዉ... እስካሁን ለመወሰን የከበደዉም ጉዳይ አለ። 'ፎዚን ክብረ ንጽህና አላገኘባትም' ቢሆንም ግን እሱ ራሱም የሚመሰክረዉ ነገር አለ 'ፎዚን በጣም ያፈቅራታል ከልቡ ይወዳታል' እና በዚህ አይነት ሁኔታ እንዴት ፎዚን እተዋታለሁ? የሚለዉ ሙግት ሀቢብን በአንድ ሀሳብ የሚከራከሩ ሁለት አካሎች አድርገዉታል። "ቆይ ከክብርና ከፍቅር የቱ ይበልጣል?" ሁለት ወሳኝ የሆኑ ነገሮች ከፊቱ ተጋርጠዉበታል። በዉስጡ ሙግት ገጥመዉበታል።
ይሄንኑ በማሰብና በማሰላሰል ላይ እያለ ብዙ ተጎዞ ከሰፈሩ ደረሰ። ወደ ቤቱ ከመግባቱ በፊት ሰፈሩ አከባቢ የምትገኝ ትንሽዬ የኮስሞቲክስ ሱቅ ገባ። በሃሳብ የተኮፋተረ ከንፈሩን በዉሃ ሊያረጥበዉ ሻተ ፤ መንገድ ያዛለዉን ጉልበቱን አርፍ ሊልበት ፈለገ። እንዲህ ሲሆን ነዉ ፎዚን በአዲስ መንፈስ የማገኛት ብሎ በማሰብ።
"ሙቤ እስኪ ዉሃ ካለህ አጠጣኝ" ሲል ሱቅ ጠባቂዉን ሙባረክን ጠየቀዉ። ሰዉነቱ በመንገድ ከመዛሉም በላይ በሀሳብ ዝሏል ፤ ከጸሐዩ በላይ የሀሳቡ ሙቀት ረቶታል። "አ..ን..ተ ..." አለ ሙቤ። አማረኛን በግድ ተናገር ያሉት ይመስል ቃላቶቹን በጠረባ አያለ ይዘርራቸዋል። ሁለተኛ ቋንቋዉ እንደሆነ ያስታዉቅበታል። "ና በዚ ተቅመጥ" አለዉና ትንሽዬ ኩርሲ አቀበለዉ። ዉሃን ከመስጠቱ በፊት ሀቢብን ሲያገኘዉ ሊነግረዉ የሚፈልገዉ ጉዳይ እንዳለዉ አሳብቆበታል። "ዛሬ ...ያቺ..." ብሎ ስሟ ጠፋዉና እንደማሰብ አደረገ። ነገር ግን አላገኘዉም። ስሟ ተሰወረበት። "ማን ነበር ስሟ" ብሎ ሀቢብን ጠየቀዉ። ሀቢብም ነገሩ ስላልገባዉ መልሶ እርሱኑ "የቷ ሙቤ!?" በማለት ጠየቀዉ። "ያቺ ናታ ያንተ ሚስት" ሀቢብ ድንጋጤ ዉስጡን ስንጥቅ አድርጎት ከተቀመጠበት ተነስቶ "እ... ምን ሆነች!!?" ብሎ ሙቤ ላይ አፈጠጠበት። "ዛሬ መጣችና ኩልና ሊፒስቲክ ገዝታኝ....." ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ "ኦህህ...." አለና በረጅሙ ትንፋሹን ካወጣ ቡኃላ ፊቱ ላይ በሰከንዶች ችፍ ብሎ የነበረዉን ላብ እየሟዠቀ ተቀመጠ። "ቆይ እሷም ትቀባባለች እንዴ!?" ብሎ ሲጠይቀዉ። ለጥያቄዉ ሳይመልስለት የጠየቀዉንም ዉሃ ሳይጎነጭ እየበረረ ወደ ቤቱ ከነፈ።
╔═══❖•🌺🌺•❖═══╗
ይቀጥላል ከ 200❤️ በኋላ
╚═══❖•🌺🌺•❖═══╝
❥............🍃💐💐🍃..............❥
@maraki_lyrics