🌹🌹ክፍል አስራ አራት🌹🌹
🌿🌿"ጤዛዉ ፍቅሬ 🌿🌿
✍✍(ኑዕማን ኢድሪስ)✍✍
.
... ከቤት እንደወጣ ከኃላዉ ከተል አለችና "ሀቢቢ..." አለችዉ። ጅምር ፍቅሯን አቋርጦባት ከቤት ሲወጣ አላስቻላትም። ግድ ስለሆነ እንጂ ከመንገዱ ብታስቀረዉ ደስ ባላት ነበር። እርምጃዉን ገታ አድረጎ ወደ ኃላ ዘወር አለና .."ወይዬ ፎዚቲ ..." አላት።
... "ልብሴን ልቀያይርና አብረን እንሂድ" አለችዉ አብራዉ ሂዳ አብራዉ መመለስ አሰኛት። ድጋሜ የማታገኘዉ ፤ እንደወጣ የሚቀር ይመስል ሆዷ ባ ባ። ፍርሃት ፍርሃት አላት። በቆመበት ፈግጎ .. "ፎዚዬ አንቺ ልብስ እስከምትቀይሪኮ እዚሁ ይመሻል። እኔ ቶሎ ደርሼ ብመለስ አይሻልም?" አላት።
... "አልቆይምኮ ሀቢቢ .. ቶሎ ቀያይሬ ልምጣ" አለችዉ እንደ መሽኮርመም እያደረጋት።
... "እረሳሸዉዴ ሁቢ? ... (እንደ መሳቅ እያደረገዉ) ... አንቺኮ ልብስ ለመቀየር ገና ሸዋር ቤት መግባት አለብሽ። ከዚያ ደግሞ ያ የፈረደበት መስታወት ፊት መገተር አለብሽ ሃሃ..."
... "ሂድ አንተ ደግሞ .." እያለች ወደ'ሱ ቀረብ አለችና ..."አደራ ሀቢቢ ራስህን ጠብቅ" አለችዉ።
... "አታስቢ የኔ ቆንጆ"
... "በመንገድህ ላይ አደራ.. የዛሬ ሾፌሮች እንደሆኑ መንጃ ፍቃዳቸዉ ካርቶን ቀደዉ የሚያድሏቸዉ ይመስል አብዛኞቹ ህጋዊ አይደሉም።..." እያለች አደጋ እንዳይገጥመዉ በመፍራት ብዙ አስጠነቀቀችዉ። እሱም ፈገግታዉ ከፊቱ ሳይለየዉ የምትነገረዉን ሁሉ በጽሞና ሰማት።
... "እወድሃለሁ የኔ ዉብ..." ብላ በቆመበት ሂዳ ጥምጥም ብላ አቀፈችዉ። እንደወጣ ይቀራል ተብላ የተነገራት ፤ ፍቅርሽ በጅምሩ ይቀራል ተብላ ሹክ የተባለች ይመስል ዉስጧን ባር ባር አላት። ሀቢብም ያቀፈችዉን ሚስቱን እሱም አቀፋት። የሷ አስተቃቀፍ ግን ይለያል!።
... "በቃ ወደ ቤት ግቢ ፎዚዬ እኔም ቶሎ ልሂድ" አላት። ሀቢብ .. በድኑ እሷ ዘንድ ይቁም እንጂ አሁን ሀሳቡ ሁሉ ሀምዛ ላይ ሆኗል። ቆየሁበት እያለ መጨነቅ ይዟል። ከእቅፉ ዉስጥ ሲያወጣት እሷ ግን የጠመጠመችበትን እጇን አላላቀቀችም። 'ይሄን ያክል ፍቅር ርቧት ነበር ማለት ነዉ' ሲል አሰበ። ፍቅር ከምንም ነገር በላይ ይርባል። ከጥም በላይም በጣም ይጠማል። ገንዘብ ያላቸዉ ሰዎች ሁሉ በገንዘባቸዉ የማያገኙት ነገር ቢኖር እዉነተኛ ደስታንና ፍጹምነት የተሞላበት ፍቅርን ነዉ። ፍቅር ከጤናም በላይ ዉድ የሆነ ነገር ነዉ። ምክንያቱም በህይወት ያለ ሰዉ ሁሉ ማፍቀር አይችልም። ምናልባት ሊያፈቅር ቢችል እንኳ አንዳንድ ሰዎች መጥፎነትን ያፈቅራሉ ፤ ጥላቻን ይቀባሉ ፤ ክፉነትን ይመርጣሉ። ነገር ግን በተቃራኒዉ ማፍቀር የሚችሉ ነገሮች ሁሉ ህይወት አላቸዉ።
በህይወት መኖርን ትርጉም የሚሰጠዉ ነገር ንጹህ ፍቅር ሲታከልበት ፤ ደስታ ሲጨመርበት ነዉ። ፎዚያ የእስከዛሬ ትርጉም የሌለዉ ህይወቷን ፤ ያለፈዉ ከደስታ የራቀዉ ኑሯዋን ዛሬ በፍቅር ስለተዋበላት ያን የፍቅር ንጉስ መቀናጆዋን በቀላሉ ልትለቀዉ አልቻለችም።
በሽንጡ በኩል ሰድዳ ጥምጥም ያደረገችበትን እጇን ቀስ ብሎ አላቀቃቸዉ። ..."ፎዚዬ ቶሎ እመለሳለሁ። ከዚያ ስትመኚዉን የነበረዉን ሁሉ እያደረግን ጣፋጭ የፍቅር ጊዜን እናሳልፋለን - እሺ!" አላት። እንደሚያባብሉት ህጻን ልጅ እሺታዋን በአንገቷና በይኗ ገለፀችለት። የግራ ጉንጯን ሳም አድርጎ ሲሄድበት ወደነበረበት አቅጣጫ ዙሮ መንገዱን ጀመረ። ፎዚያም ጀርባዉን ሰጥቷት የሚሄደዉን ባሏን ከአይኗ እስከሚጠፋ ድረስ በስስት እየተመለከተችዉ ሸኘችዉ።
.
.
.... "መኪዬ.." አላት አይኖቹን በመስኩቱ ወዲያ ማዶ የሚታየዉን ግትር ህንጻ እየተመለከተ። 'ወይ' አለችዉ በተቻኮለ አይነት።
.... "መኪዬ አሁን ሀቢብ ሲመጣ ተቻኩለሽ ዶክተሩ ምን እንዳለኝ እንዳትነግሪዉ - እሺ" ብሎ በተኛበት ቦታ እንዳለ አንገቱን መለስ አድርጎ ወደ'ሷ ተመለከተ። መኪያም እንደዚህ ያለበትን ምክንያት ለማወቅ ያክል ..."ለምን ሀምዚ?" ብላ በተቀመጠችበት ቦታ እንደመደላደል እያለች ጠየቀችዉ።
... "ሀቢብ እንዲደነግጥ አልፈልግም። እኔዉ ቀስ ብዬ አረጋግቼ እነግረዋለሁ!" ሲላት የባሏን ትዕዛዝ ጥሳ የማታዉቀዉ መኪያ 'እሺ አልነግረዉም' ብላ ሀሳቡን በይሁንታ ተቀበለች።
.
.
... ሀቢብ ስለማን እንደሚያስብ ግራ ገብቶታል። አንዴ ስለ ቤቱ ፤ ቀጠል አድርጎም ሰሞኑን ስላቋረጠዉ ስራና ስለ አመለ ቢሱ የቅርብ አለቃዉ ፤ በመሃል ደግሞ ስንቅር የሚልበት .. ሆስፒታል ዉስጥ ክፉኛ እግሩን ተጎድቶ ስለተኛዉ ጓደኛዉ - ሀምዛ ... በሀሳብ ዉጥር ብሏል። ሁሉም 'እሱን ተወዉ' 'እሱን ተወዉና ስለ'ኔ እሰብ እያሉ የሚከፋፈሉት ፤ የሚቦጫጨቁት መሰለዉ። እግሮቹን እሱ ሳይሆን የሚያዛቸዉ ሀሳብ ከኃላዉ ሆኖ እንደ ጋሪ የሚገፋዉ እስኪመስለዉ ድረስ ራሱን አያዉቅም።
.
.
... ፎዚያ ባሏን በአይኗ ከሸኘች በኃላ ወደ ቤቱ ገባች። ሀቢብ ከቤት ከወጣ ጀምሮ ሀሳብ አይሉት ሰበብ የጭንቀት ናዳ አእምሮዋ ላይ ሰፈረባት። የትጥበት ግዴታዋን ለመወጣት ወደ ሸዋር ቤት ከገባች በኃላ ዉሃዉን በሃይል ከፍታ መታጠብ ጀመረች። ... ከፀጉሯ ኩልል ብሎ የሚወርደዉ ዉሃ በግንባሯ ላይ ተንከባሎ ቅንድቧን አልፎ አይኗ ዉስጥ ሊገባ ሲል አይኖቿን ከደነቻቸዉ - ጨፈነች። በዚህ መካከል ህልም አይሉት ቅዥት በአይነ ህሊናዋ አስደንጋጭ ክስተት ተመለከተች።
ከራሷ በላይ የምትወደዉ ባሏ ሀቢብ የእጅ ስልኩን በእጁ ይዞ ስልክ እያነጋገረ አስፖልት በመሻገር ላይ ሳለ የመኪናዉን ፍጥነት መቆጣጠር ያቃተዉ አንድ ሾፌር ሀቢብ በሚሻገርበት መንገድ በፍጥነት መኪናዉን ሲያሽከረክር ተመለከተች። "ሀቢ...ብ" ብላ በቅጽበት የከደነቻቸዉን አይኖቿን ገልጣ በጎኗ በኩል የተንጠለጠለዉን ፎጣ አነሳች። ፎጣዉን በትክክል ሳታሸርጠዉ (ሳታገለድመዉ) ተቻኩላ ከሸዋር ቤት ወጣች።ሰዉነቷ እየተንቀጠቀጠ ነበር። ያየችዉ ክስተት በአይነ ህሊናዋ ሳይሆን በእዉኗ እስኪመስላት ድረስ ያጣፋችዉን ፎጣ በአንድ እጇ ጨምድዳ እንደያዘች ገላዋ ራደ - ተብረከረከች። ስልኳን አነሳችና ወደ ሀቢብ ደወለች።
╔═══❖•💕💕•❖═══╗
ይቀጥላል....
╚═══❖•💕💕•❖═══╝
❥............🍃👑👑🍃..............❥