የህንድ የቀድሞው ኘሬዚዳንት ዶ/ር አብዱል ካለም እንደተናገሩት ፦
ልጅ ሳለሁ እናታችን ጥሩ ምግብ አብሳይ እንደ ነበረች አስታውሳለሁ። ከዕለታት አንድ ቀን በከባድ ስራዎች ተዳክማ በዋለችበት ዕለት የሰራችውን እራት ለመመገብ ታድመን ነበር። ለሁላችንም ምግብ ከታደለ በኃላ የቀረበውን ምግብ ሳይ ያረረ ቂጣ ነበር። ማዕዱ ላይ የተሰናዱ ሰዎች ስለቂጣው የሚናገሩትን ሽሙጥ እየተጠባባኩ ሳለ..... አባቴ ምንም እንዳልተፈጠረ የቀረበለትን ምግብ አጠጥሞ በልተቶ .... ስለትምህርት ቤት ውሎዬ ይጠይቀኝ ጀመር።
በዚያ ምሽት ለአባቴ ምን ምለሽ እንደሰጠሁት ባላስታውስም እናቴ አባቴን ያረረ ቂጣ ስለመመገቧ ይቅርታ ስትጠይቅ መስማቴን ግን መቼም ቢሆን አልረሳውም። አባቴም በምላሹ እንዲህ ነበር ያላት "ማሬ እወዳለሁ እኮ።"
በዚያ ምሽት ከመተኛቴ በፊት አባቴን ስሜ መሰናበት ስለለብኝ እንደወትሮዬ ክፍሉ ሄድኩኝ። እግረ መንገዴም "አባዬ የእውነት የተቃጠለ ቂጣ ትወዳለህ ወይ?" ብዬ ጠየኩት። እሱም በእጁ ጉንጩን ቆንጠር አረገና .....ልጄ "እናትህ ዛሬ በጣም ደክሟት ነበር..... ደግሞም አቃጣይ ንግግሮች (ቃላት) እንጂ የተቃጠሉ ምግቦች ብዙም አይጎዱም" አለኝ። ምላሳችንን እንጠብቅ
ሁሌም መካሪ ከተገኘ ህይወት ቀላል ነው፡፡
@Tesh5050