መንፈሳዊ ትረካ ብቻ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነምህረት ስላለኝ ነው ምክንያት..........
መልቀቅ የምትፈልጉት ነገር ካለ @Ermiyas3 ላይ ወይም ደግሞ @Enate_mariyam3 ላይ አናግሩኝ #Ermiyas

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


Letemeket maserat yemetefelegu +251982820179/0714691444








ይሄ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል ለኦርቶዶክሳውያን የግድ ያስፈልጋል እባክዎ ከታች በመረጡት ይቀላቀሉ


selam endet ameshachu wed yemenefesawi tereka abalatoch bemulu chanalachen endeketel fekadegna nachu demetsachu awon kehone be @Ermiyas3 lay yes belachu lakulen enamesegenalen


#ሚስት_አጣሁ!  🤔

꧁ ❝ ውድ አንባቢያን 2 ደቂቃ እንዋሶትና  ይህንን አስተማሪ ታሪክ ላካፍላችሁ ።

አንድ ወጣት ሚስት ማግባት ፈለገ። በዙሪያውም ብዙ ቆነጃጂት ሞልተዋል።ወጣቱ ግን ለአይኑ እምትሞላ ፣ ለትዳሩ የምትበጅ ፣ ሙሉ የሆነች ቆንጆ ና ውብ ሴት የሚላት የትኛዋ እንደሆነች መምረጥ ተቸገረ። ሴት በሞላበት ሀገር ሚስት ፍለጋ ቢናውዝም ይችን ላግባ ብሎ መምረጥ እና መወሰን ተሳነው። ብቻ ቢፈልግም ቢያስፈልግም ሚስት አጣ።
...
ከዕለታት አንድ ቀን ምን ይሻላል ብሎ ሰው ሲያማክር እራቅ ወዳለ ሀገር አንድ ጠቢብ ሰው ስላሉ እሳቸው ጋር ቢሄድ አንዳች መፍትሄ እንደሚያገኝ ነገሩትና እርሱም ወደዛ አሉ ወደተባሉ ጠቢብ ሽማግሌ ዘንድ ይሄዳል። ጠቢቡ ዘንድም ደርሶ የበቆሎ ማሳ ቁጭ ብለው ሲጠብቁ አገኛቸው።
...
ሚስት ያጣው ወጣትም ከማሳው ዳር ካለው የእርሻው ዲብ ላይ ጺማቸውን አንጀርግገው በግርማ ሞገስ ቁጭ ብለው የበቆሎ ማሳ ወደሚጠብቁት ጥበበኛ ሽማግሌ ጠጋ አለና እንደምን ዋሉ አባቴ አላቸው።እርሳቸውም እግዚያብሔር ይመስገን እንደምን ዋልክ ልጀ አሉት።
...
ጥበበኛ ነወት ተብየ መምጣቴ ነው አላቸው። እርሳቸውም በእርጋታ ትኩር ብለው እያዩት " ምን እንድረዳህ ፈልገህ ነው የመጣኸው? " ብለው ጠየቁት። እርሱም "ሚስት አጣሁ !..."ብሎ የመጣበትን ጉዳይ አንድ በአንድ አስረዳቸው።
...
እርሳቸውም " አይይ ልጄ !! በል ና ተከተለኝ " ብለው ከበቆሎው ማሳ ዳር ቆሙና " የመጣህበትን እንድነግርህ ከዚህ ከምታየው የበቆሎ ማሳ ከዚህ ከቆምንበት ጀምርና እስከ ዳር ድረስ ውስጥ ለውስጥ ገብተህ ከዚህ ሁሉ የበቆሎ እሸት በመጠኑ ከፍ ያለ እና አሪፍ እምትለውን አንድ ብቻ የበቆሎ እሸት ዘንጥለህ አምጣልኝ ። ነገር ግን ማሳሰቢ ልስጥህ ።
...
1ኛ ከዚህ ከቆምክበ ከፊትህ ካለው እሸት ወደ ውስጥ ብገባም ከዚህ የበለጠ እሸት አላገኝም ብለህ ካመንክ እዚሁ ዘንጥለህ ልትሰጠኝ ትችላለህ።

2ኛው ማሳሰቢያ ከዚህ ጀምረህ እስከ ማሳው ዳር ድረስ ወደፊት እየተራመድክ መምረጥ ትችላለህ ነገር ግን ልብ በል አንዴ ያለፍከውን እሸት እንደገና ወደ ቡሀላ ተመልሰህ መቁረጥ አትችልም ወደፊት ብቻ።

3ኛው ማሳሰቢያ አጥቻለሁ ብለህ ባዶ እጅህን መምጣት አትችልም።

4ኛው እና የመጨረሻው ደግሞ ከዚህ ሰፊ የበቆሎ ማሳ አንድ የበቆሎ እሸት ብቻ ነው ቆርጠህ እምታመጣልኝ።
መጀመር ትችላለህ " አሉትና ተመልሰው ቁጭ አሉ ወጣቱም ወደ በቆሎው ገባና የተሻለ የሚለውን በቆሎ መፈለግ ጀመረ።
...
ሁሉም እሸት አማረው አይን አዋጅ ሆነበት ትንሽ ገባ እንዳለ በጣም የሚያማልል እሸት አየና ሊቆርጥ አሰበና " ወደፊት ከዚህ ከሚታየኝ የበለጠ ትልልቅ እና እሚያማምር ቢኖርስ ? ብሄድ ይሻላል"። ብሎ ፍለጋውን ቀጠለ። ነገር ግን ወደ ፊት በሄደ ቁጥር እንደ ቅድሙ የሚያምር ሳይሆን ጥራቱ እየቀነሰ ሄደ።
....
አሁንም ወደ ፊት ጥሩ እሸት አገኛለሁ እያለ መዳከር ያዘ። ነገር ግን ጭራሽ ከቅድሙ የባሰ በመጠኑ ያነሰ፣ ገና ለጋ የሆነ እና ትል የበላው እየሆነ መጣ። ወጣቱም ወደ ኋላ መመለስ አትችልም ስለተባለ ምናለ ቅድም ዳር ላይ ቆርጨ በነበር እያለ እየተፀፀተ አሁንም ተስፋ ሳይቆርጥ ወደፊት ልክ ቅድም ስገባ እንዳየሁት እሚያማምር እሸት አገኝ ይሆናል እያለ በተስፋ ወደ ፊት ፍለጋውን ቀጠለ። እሚያሳዝነው የተባለውን እሸት ሳይቆርጥ በገባበት ተቃራኒ የእርሻው ዳርቻ ሊወጣ ሲዳረስ እንዳለ ግማሹን ወፍ የጠረጠረው እየሆነ መጣ።"
...
እስኪ እንደ ቅድሙ ዳር ላይ ጥሩ በቀሎ ባገኝ ብሎ የእርሻው ጫፍ ላይ ብቅ አለ ነገር ግን እሚገርመው ጭራሹንም ወፍ እልም አድርጎ የጨረሰውና ቆረቆንዳ ብቻ ሁኖ አገኘው።ወደ ቡሃላ እንዳይመለስ ወደ ኋላ መመለስ አትችልም ተብሏል። ባዶ እጁን እንዳይመለስ ምንም ቢሆን ባዶ እጅህን እንዳትመለስ ተብሏል።
...
ስለዚህ አማራጭ ስላጣ ወፍ የበላውን የበቆሎ ቆረቆንዳ አንዱን ዘንጥሎ ወደ ጠቢቡ ተመለሰ እና ከፊታቸው ቆመ።

✍ እርሳቸም "እስኪ ያመጣኸውን አሳየኝ "አሉት። እርሱም አንድም በላዩ ላይ ጥሬ የሌለውን ቆረቆንዳ ሰጣቸውና በሀፍረት ፀጥ ብሎ ቆመ።"ይህንን ነው የተሻለ ያገኘኸው?" ብለው ቢጠይቁት እርሱም በሀፍረት አባቴ ያው የተሻለ አገኛለሁ ብየ ስፈልግ ሳላስበው ወፍ ከበላው ደረስኩ " አለ እየተንተፋተፈ።
...
ቁጭ በል እስኪ አሉና "አየህ የኔ ልጅ ሚስት እያማረጡ አንዷን ከአንዷ እያመረጡ መኖርም ልክ እንደዚህ ነው።
👉 አብዝቶ መምረጥ መጨረሻ ከምራጭ ይጥላልና ሚስት ከእግዚያብሔር ስለሆነች በአንተ ምርጫ አይሆንም። ከፊትህ ያለችውን ሚስት አድርግ "አሉት❞

ምንጭ "ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች"

ምን ተማራችሁ?

@menefesawitereka

https://t.me//menefesawitereka

Показано 7 последних публикаций.