#ከፍቅር_ጉዞ_ወደ_ከንቱ_መመላለስ
የማለዳ የነፍስ ስንቃችን
መንፈሳዊ ሕይወት እግዚአብሔርን በመውደድ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ይህ ፍቅርም የሁሉም ነገር መነሻ ነጥብ ሊሆን ይገባል። የምንፀልየው እግዚአብሔርን ስለምንወደው ነው "ነፍሴ አንተን ተጠማች ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውሃ በሌለበት ምድረ በዳ" መዝ. 62፥1 "አቤቱ ሕግህን እንደምን እጅግ ወደድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው" መዝ. 118፥97 የሚለውን የቅዱስ ዳዊትን ቃል እያሰብን። የመንፈስ ዝለት ካለ ግን ጸሎት ከፍቅር የመነጨ መሆኑ ቀርቶ ህሊናችን እንዳይወቅሰን ስንል ብቻ የምንፈጽመው ተግባር ይሆናል። የእውነተኛ ጸሎት መለኪያ የሆኑትን ከፍተኛ ስሜትና መመሰጥን ያጣል። ትሕትና አክብሮት ወይም ፍቅር የሌለው ይሆናል ሌሎችም መንፈሳዊ ተግባራት ሁሉ እንዲሁ ከመንፈሳዊነት ያፈነግጣሉ።
ምናልባት መንፈሳዊ ሕይወትን ስጀምር ለእግዚአብሔር ፍቅር ኖሮን ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አልገፋንበትም።
ለምን?፦
✞ ይህ ድካም የመታጣው ምን አልባት በጸሎት ጊዜ ከተመስሥጦ ይልቅ በብዛት ላይ ማተኮራችንና በቀመር በሚመራ ሕይወት ለመመራት በማሰባችን ይሆናል።
✞ ፀሎት ስናደርግ እኛን የሚያሳስበን ምን ያሕል ምዕራፍ እንደደገምን እንጂ እነዚህን በምን ዓይነት መልኩ እንደጨረስን አይደለም።
✞ በትዕዛዝ የተደነገገው የምዕራፎች ቁጥር ላይ ከደረስን በቂዬ ነው ብለን እግዚአብሔር በጸሎታችን በአምልኮታችን ተደስቷል ወይ? የሚለውን ዐብይ ጥያቄ ግን አናስተውለውም። እዚህ ነጥብ ላይ ስንደርስ ቅዱስ ማር ይሳሐቅ እንዲህ በማለት ያስጠነቅቃል። "በእግዚአብሔር ፊት የቆምሁት ቃላት ለመቁጠር አይደለም።" ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም እልፍ ቃላት በልሳን ከመናገር ይልቅ አምስት ቃላት በማስተዋል መናገርን መርጧል።(1ቆሮ 14፥19)
ብዙዎቻችን ግን ቁጥሩና ብዛቱ ለይ ስለምናተኩር ጸሎታችን በችኮላ ስለሚደረግ ማስተዋል የለበትምና ምንም እርባና አይኖረውም።
ስለዚህ ጸሎት መጸለይ ስላለበት ብቻ የሚፈጸም ግዲታ ወደ መሆን ሲለወጥ ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር በመነጋገርራችን ደስተኛ ሳንሆን ህጉን መተግበር ብቻ አላማችን ይሆናል ችኮላና ማነብነብ ማስተዋልን ይቀንሳል። ይህ አይነት የመንፈስ ዝለት ባጠቃን ጊዜ ለራሳችን " እንደ ቀራጩ ጥቂትነገርም ሆነ በቀኝ እንደተሰቀለው ወንበዴ አንድ ዓርፍተ ነገር ብናገር ጸሎቴ ከእግዚአብሔር ጋር ከልብ እገናኝ ዘንድ ነው። ልንል ይገባል።
በብዛትና ያለፍቅር ሕግን ለመፈጸም ብቻ ከሚል ሕይወት ለመላቀቅ እንሞክር። በማስተዋልና በጥልቀት ስሜት ሆነን በመንፈስ ለመጸለይ እንትጋ። ይህንንም በሌሎችም መንፈሳዊ ተግባራት ላይ እንተርጎመው።
አዘጋጅ :- በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አላቲኖስ
'#የመንፈስ_ዝለት ከሚለው #የአቡነ_ሽኖዳ መጽሐፍ የተወሰደ'
╔✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_ቀን❀
╚✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ
የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏
በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot
በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇... ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
❖ t.me/mezgebehaymanot ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳
beletekebede03@gmail.com
ወስብሐት ለእግዚአብሔር