በአማራ ክልል ጉዳት የደረባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባት ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡
ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ እስካሁን በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት በርካታ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የቢሮው ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክተር ዘመነ አበጀ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ምሥራቅ ጎጃም ዞን ብቻ ከ400 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ኃላፊው ጠቅሰዋል፡፡
በአጠቃላይ በክልሉ ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች ወደ አገልግሎት ለመመለስ
112 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ቢሮው ያስጠናውን ጥናት መሠረት በማድረግ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡ #FMC
@minster_of_education