የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች መመረቃቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ሐዋሳ ማእከል አስታወቀ ፡፡
የካቲት ፲፭/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን ሐዋሳ ማእከል በሐዋሳ ደብረ ኢየሱስ ወቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ከ127 በላይ በልዩ ልዩ የጤና ዘርፍ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች በትናንትናው ዕለት የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቀዋል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ የግቢ ጉባኤው የአብነት መምህር በሆኑት የኔታ ነቃ ጥበብ የወንጌል ትምህርት ተሰጥቷል።
በተጨማሪም በተመራቂ ተማሪዎች መዝሙር እና ወረብ ቀርቧል፡፡
በዕለቱም የቤተ ክርስቲያኑ አባቶች ካህናት፣ምእመናን እና የተመራቂ ቤተሰቦች የተገኙ ሲሆን ለተመራቂ ተማሪዎችም የአደራ መስቀል ተበርክቶላቸዋል።