"حديقة العلم" "የዒልም ፓርክ"


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


قناة تَهتَمُّ بنشر الفوائد واﻷقوال الصحيحة
من اﻵيات القرآنيـة
واﻷحاديث النبويــة
والآثار السلفيــــة
يُقدِّمُها لكم "موسى دالنور السلطي" باللغة العربية واﻷمهرية

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


🔸ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"በጁሙዓ ቀንና ለሊት በኔ ላይ ሶለዋት ማውረድን አብዙ"

አሏሁምመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዐላ ሙሐመድ ወዐላ ኣሊሂ ወሰሕቢህ።
________________
(حسنه الألباني في الصحيحية :1407)


ወንድሜ ከልብህ አንድም ጊዜ ቢሆን እንኳ አስተጝፊሩሏህ ማለትን አታስተናንስ ምናልባትም አሏህ በሷ ብቻ ወንጀሎችህን ጠራርጎ ሊያጠፋልህ ይችላልና።


በቃ! ይቅር በል ልብህ ለሌሎች ጥላቻና ተንኮል ሳይሆን ዐውፍታን ብቻ ይሸከም።
አላህ ይቅር ባዮችንኮ ይወዳቸዋል ታዲያ አላህ ሊወድህ አትወድም?!።


ኢላሂ! አንተ የወሰንከውን ነገር የምንወድ አድርገን በተቀረው ዕድሜያችን በረካ አድርግልን ከአደጋና ከክፋት ሁሉ አርቀን ያረብ።


ያረብ! ላጤዎችን ዘውጅልን ትዳር ለሀብት ሰበብ ነው ከወንጀል ያርቃል የጌታን ውዴታ ያስገኛል።


አምላካችን ሆይ! ከድካም በኋላ ረፍትን ከሐዘን በኋላ ደስታን ከትዕግስት በኋላ ተድላን ለግሰን ያረበል’ዓለሚን።


ያ አሏህ! የዛሬውን ቀን ከትላንትናው የነገውን ከዛሬው የተሻለ አድርገው እውን መሆኑን የጠበቅነውን የህልማችንን ደስታ አትከለክለን።


ከዚህ በፊት በ 131ዓ·ሂ ረጀብ ላይ ወይም በ749 ዓ·ል ወረርሽን ተከስቶ በረመዷን ውስጥ እጅግ በጣም በርትቶ ነበር እንዳውም "ኩፋ" ሀገር ውስጥ በየ ቀኑ አንድ ሺህ ጀናዛ ይቆጠር ነበር ከረመዷን በኋላም እየቀነሰ እየቀነሰ በሸዋል ውስጥ ጠፍቷል።

ይኸው እኛም ሸዋል ውስጥ ነን እና እባካችሁ በዱዓ መበርታት አለብን።
(اللهم ارفع عنا ما حل بنا من البلاء والوباء والكورونا والفتن ما ظهر منها وما بطن يا من يقول للشيء كن فيكون)
ــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
📚 المعارف لابن قتيبة الدينوري ص(٦٠٢)
📚 كنوز الذهب في تاريخ حلب لسبط ابن العجمي (١ / ١٧٠).


ሴት ልጅ ሊያጫት (ሊያገባት) የመጣው ሰውዬ ሸሪዓዊ እይታን ሊያያት በሚፈልግ ጊዜ ሜካፕ💄 ተቀብታ ሊትዋብለት አይፈቀድም ምክንያቱም ይህ ማጭበርበርና ማታለል ነውና።
________
العلامة ابن عثيمين رحمه الله
(فتاوى نور على الدرب)


🧤በጓንት ሱጁድ ማድረግ🧤
~~~~~~~~~~~~~~~~
የእጅ ጓንት አድርጎ ሱጁድ ማድረግ ብዙሃኑ የዲን ምሁራን ሱጁድን አያበላሽም ብለዋል ከፊላቸው የተጠላ (ከራሃ) ነው ብሉም።

ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ ላይ ሶሃቦች የመሬቱ ሙቀት ሱጁድ ለማድረግ ሳያስችላቸው ሲቀር ልብሳቸውን ዘርግተው ሱጁድ ያደርጉበት ነበር ተብሏልና።

እንደ ኮሮና ቫይረስ ባስፈራበት ወቅት ላይ ጓንት ለብሶ ሱጁድ ማድረግ ያለ ከራሃም ይፈቀዳል አል’ኢማሙ ኢብኑ ባዝ ለሴትም ሆነ ለወንድ ይፈቀዳል ብለው ፈትዋ ሰጥተዋል።
_______________
🎙(د.سليمان بن سليم الله الرحيلي)


🌷ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ለኡመታቸው በጣም ከፈሩላቸው ነገራቶች መካከል፦
💥—ደጃል
💥—ትንሹ ሺርክ
💥—ሴቶች
💥—ዱንያ
💥—ምላሰ አዋቂ ሙናፊቅ
💥—የሉጥ ሕዝቦች ሥራ (ግብረ_ሰዶም)
💥—ምላስ
💥—ቁርኣን ቀርቶ የተበላሸ ግለሰብ
💥—ጠማማ መሪዎች
💥—ወለድ።


ለሊት ላይ ረመዷን ሲመጣ ለይል ለመስገድ ረመዷን ሲወጣ ሽንት ለመሽናት ከሚነሳ ሰው አትሁን!!

ከእለታት አንድ ቀን የሆኑ ሰዎች ስለ ለይል መቆም ሲያወሩ አንድ ገጠሬ አጠገባቸው ላይ ነበረና "ለሊት ትነሳለህ እንዴ?" አሉት እሱም "አዎ ወላሂ" አላቸው "ከዚያስ ምን ታደርጋለህ" ሲሉት ጊዜ "ሽንቴን ሸንቼ ተመልሼ እተኛለሁ" አላቸው።
_____
(أخبار الحمقى والمغفلين لابن الجوزي:126)


ሰዎችን በመፍራት ከመልካም ሥራ መቆጠብ ምንም እንኳን እንደ ፉደይል አይነት ያሉ አንዳንድ ሰለፎች ከሺርክ ቢቆጥሩትም ስህተት ነው የሚባለው እንጂ ሺርክ ነው አይባልም!

ግን እነሱ ሺርክ ነው ሲሉ የፈለጉት ወይ ይህን ነገር ላደርግ ነበር ይሉኝታ (ሪያእ) ይሆንብኛል ብዬ ትቻለሁ እያለ ጥቆማ በማድረግ በተወው ጊዜ ሊሆን ይችላል።

ሌላ ጊዜ ሰው ኖረም አልኖረም የሚትሠራው ነገር ከሆነ ሰው ቢኖርም ሰው ስላለና እንዳያደንቁኝ ብለህ መተው የለብህም

ነገርግን አንዳንዴ ወይም ራሱ ላይ በጣም ሪያእ የሚፈራ ሥራው እንዳይበላሽበት በጣም የሚሰጋ ከሆነ ሰዎች እስከሚሄዱ ድረስ ቢጠብቅ የተሻለ ይሆናል ምክንያቱም ለብቻ የሚሠራና አንድ ላይ የሚሠራ አንድ አይደለምና።

መጥፎ ሥራን ደግሞ ሰዎች ስላሉ ብሎ መተው ከእፍረት (ከሐያእ) አንፃር ከሆነ ይህ የሚያስወቅስ ሳይሆን የሚያስወድስ ነው የሚሆነው

ነገርግን (ለተዘዩን) ለሰዎች ጥሩ ሆኖ ለመታየትና ራሱን ለማላቅ አስቦ ከሆነ ይህ ሪያእ ውስጥ ይገባል ትንሹ ሺርክ ተብሎ የተሰየመው ይሆናል።
_____________
🎙ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ


🏝የሸዋል ጾም🏝

🌷ነቢያችን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
«من صام رمضان وأتبعه بست من شوال كان كصيام الدهر»
📚(رواه مسلم وغيره)

"ረመዷንን የጾመ ሰው ከሸዋልም ስድስት ቀን አስከትሎ ከጾመ ዓመቱን በሙሉ እንደ ጾመ ይቆጠርለታል"

🌷በሌላም ዘገባ ላይ እንዲህ ብለዋል ፦
«صيام شهر رمضان بعشرة أشهر وصيام ستة أيام من شوال بشهرين وذلك صيام السنة»
📚صححه الألباني في صحيح الترغيب

«የረመዷን አንድ ወር ጾም በአስር ወር ሲባዛለት የሸዋል ስድስት ቀን ጾም ደግሞ በሁለት ወር ይባዛለታል ይህ ደግሞ የአንድ ዓመት ጾም ነው»

(ማሳሰቢያ)
①የረመዷን ቀዷእ ያለበት ሰው ቀዷኡን ሳያወጣ በፊት ሸዋልን ቢጾም ይህ አጅር ልገኝለት አይችልም ምክንያቱም የሸዋል ጾም ለረመዷን ጾም ተከታይ መሆን አለበትና።

②የሸዋልን ቀናቶች አከታትሎም ሆነ ለያይቶ መጾም ችግር የለውም ነገርግን ማከታተሉ ተመራጭ ነው
ምክንያቱም ክፍተት ማስገባቱ ለመተው ሊያበቃው ይችላልና።

________________
📚[مجموع فتاوى ورسائل ابن عثيمين : 18/20]


የዒድ ቀናችን ነውና አንዴ ፈገግ በሉልኝማ!

አንድ ልጅ "ጠለዐል’በድሩ ዐለይና" የሚለውን የዓረብኛ ግጥም እያነበበ ወደ መፀዳጃ ቤት ይገባል ከዚያም አባቱ ገብቶ ይመታዋል ልጁም ሲያለቅስ ሰምታ እናትየው መጥታ ለምን ልጁን መታህው ትለዋለች አባትየውም መፀዳጃ ቦታ ላይ ቁርኣን ይቀራል’ንዴ?! ይላታል እሷም አሁን ያነበበው እኮ የዐረብኛ ስንኝ ነው እንጂ ቁርኣን አይደለም! ሲትለው ጊዜ አባትየው አለቀሰ እሷም ለምን ታለቅሳለህ ሲትለው ጊዜ እኔ እኮ ይህ ነገር ቁርኣን መስሎኝ ሰላሳ ዓመት ድረስ ሶላት ላይ እየቀራሁት ነበር አላት ‼️
_____________
📚أخبار الحمقى و المغفلين لابن الجوزي.




📌 س/ كيف نحافظ على العبادات بعد رمضان ؟

🎙جـ/ الشيخ العلامة الإمام :
محمد بن صالح بن عثيمين
-رحمه الله تعالى- .


• - قال الحافظ ابن رجب -رحمه الله-
• - التزين في العيد يستوي فيه الخارج إلى الصلاة والجالس في بيته ، حتى النساء والأطفال.
ለዒድ በመዋብ ለዒድ ሶላት የሚሄዱትምና በቤት የተቀመጡትም _ሴቶችምና ሕፃናት ሁሉ ሳይቀሩ_ እኩል ናቸው።
📜(فتح الباري لابن رجب ٤٢٠/٨) ‏

▪‏قال ابن حجر رحمه الله:
"إظهار السرور في الأعياد من شعار الدِّين".
በዓላት ላይ ደስታን ማሳየት ከዲን መገለጫዎች አንዱ ነው።
__________________
📜(الفتح ٤٤٦/٢)
‏༄༅‏༄༅‏༄༅‏༄༅❁❁✿❁❁‌‏༄༅‏༄༅‏༄


👆👆👆👆
💡حق الله لا ينتهي بانتهاء رمضان💡
•موعظة مؤثرة•
🎙للعلامة د. صالح بن فوزان الفوزان
-حفظه الله تعالى-.


Репост из: [فتاوي مهمة لعامة الأمة]
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram

Показано 20 последних публикаций.

208

подписчиков
Статистика канала