15 ቀናት ትምህርት ተዘግቶ ቆይቷል ቀጣዩ እርምጃስ?
የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ ነበር ኢትዮጵያ መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም ለ15 ቀናት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተነገረው። ይህ ቀን የፊታችን ሰኞ የሚያበቃ ሲሆን የቫይረሱ ስርጭት እና ያስከተለው ስጋት እየጨመረ በመሆኑ ውሳኔው እንደሚራዘም ይጠበቃል።
በጉዳዩ ላይትምህርት ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና ሌሎች የጤና ተቋማት መረጃ እንዲሰጡን ብንጠይቅም ሁሉም ተቋማት የኮሮና ቫይረስ ብሔራዊ ኮማንድ ፖስት ውሳኔን እየጠበቁ መሆኑን ነግረውናል። መንግስት ዛሬ ከሰዓት ወይንም ነገ የቫይረሱን ስርጭት አስመልክቶ በቀጣይ ስለሚወሰዱ አጠቃላይ እርምጃዎች መግለጫ ሊሰጥ እንደሚችል ሰምተናል።
ምንጭ፡- ኢትዮ ኤፍ ኤም
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSREAULT