የበአል ትዝታ!
°°°°°°°°°°°°°
የሰፈራችን አባቶች የገዙት በሬ አንድ አይን አልነበረውም!
የት ዘምቶ እንደሆነ እንጃ!
እንደ ጭቃ ሹም ታጅቦ መጣ።
አረማመዱ መቼም የጤና አልነበረም። ልክ የሰፈራችን የቆሻሻ ገንዳ አጠገብ ሲደርስ ደነበረ!
ተፈነጣጠረ!
አባቶቻችን እንደ ዝምብ መንጋ ዝዝዝዝ..ብለው ተበተኑ!
" ያዘው! ያዘው! "
ከወኔ ውጪ ሰውነት የሌላቸው ጋሽ ብሩ ቁልቁል የሚንደረደረውን በሬ በሩጫ ተከተሉት
...ግን ተሳሳቱ--- ፈጠኑ....በጣም!
በሬው ቀጥ ብሎ ሲቆም ጋሽ ብሩ ፍሬናቸውን በጥሰው እግሩ ስር እንደ ሊስትሮ.....
በሬው በቀኟ ዐይኑ እንደ መሽኮርመም አለና!
በቀንዱ ዘገናቸው! ( የምሬን ነው )
እንደ ጀላቲ ቀንዱ ጫፍ ላይ ሰክቷቸው ሲታይ የፈረንጅ አጋዘን ይመስል ነበር።
ዘቅዘቅ ሲሉ፡ ነጯ ኮፍያ ጠብ አለች!
" በህግ አምላክ! "....አሉ አየር ላይ ( ማንን ይሆን? )
በሬው ጋሽ ብሩን አንጠልጥሎ ወደገንዳው ተመለሰና ገንዳው ውስጥ ጨመራቸው!( አስቀመጣቸው ልበል? )
ተረኛ የሚዘገን ሲፈልግ፡ ሰዉ ተተራመሰ!
ዞሮ ዘሎ ሲመጣ ጋሽ ብሩ ከገንዳው ብቅ አሉ!
አልጋ ስር የተረሳ ጫማ መስለው..😂
" ኮፍያዬን አላያችሁም? "
" አላየንም "
" ያችኋትናኮ አቀብሉኝማ "
" ሌላ ቀን ይውሰዷት "....በዚያ ላይ
" ቢወጋንስ? "
" እኔ አባታችሁ እንዴት ልውጣ ታዲያ? "
እንዳይወጡ ቆሟል ፊት ለፊት
" ኧረ ጠነባሁ ጎበዝ "
መቼስ ብዙ ስቀናል ያኔ። በስንት መከራ ተሸነፈ!
ታርዶም ጣጠኛ ነበር
የታረደ ቀን ጠዋት ቅርጫው ላይ ጫጫታ ይሰማል
ጨጓራው ተሰረቀ!
ያው ከሮቤል ውጪ መቼም ማንም አይሆንም!
የነሮቢ በር በሃይል ተንኳኳ!...ሮቢ ከፈተ
" ጨጓራውን መልስ! "
" ኧረ ጋሼ! የምን ጨጓራ? "
" ዛሬ ፊኛህን ተሰናበት! ልቆምበት ነው "
" እኔ አላየሁምኮ "
" ምንድነው በመዘፍዘፊያው ያስቀመጥከው "
" የባቢ ሽንት ጨርቅ ነው "
" እያጠብክለት? "
" አዎ "
" በፈርስ ነው የምታለቀልቀው? "
Credit:- Fikre Z Bhere Ethiopia
°°°°°°°°°°°°°
የሰፈራችን አባቶች የገዙት በሬ አንድ አይን አልነበረውም!
የት ዘምቶ እንደሆነ እንጃ!
እንደ ጭቃ ሹም ታጅቦ መጣ።
አረማመዱ መቼም የጤና አልነበረም። ልክ የሰፈራችን የቆሻሻ ገንዳ አጠገብ ሲደርስ ደነበረ!
ተፈነጣጠረ!
አባቶቻችን እንደ ዝምብ መንጋ ዝዝዝዝ..ብለው ተበተኑ!
" ያዘው! ያዘው! "
ከወኔ ውጪ ሰውነት የሌላቸው ጋሽ ብሩ ቁልቁል የሚንደረደረውን በሬ በሩጫ ተከተሉት
...ግን ተሳሳቱ--- ፈጠኑ....በጣም!
በሬው ቀጥ ብሎ ሲቆም ጋሽ ብሩ ፍሬናቸውን በጥሰው እግሩ ስር እንደ ሊስትሮ.....
በሬው በቀኟ ዐይኑ እንደ መሽኮርመም አለና!
በቀንዱ ዘገናቸው! ( የምሬን ነው )
እንደ ጀላቲ ቀንዱ ጫፍ ላይ ሰክቷቸው ሲታይ የፈረንጅ አጋዘን ይመስል ነበር።
ዘቅዘቅ ሲሉ፡ ነጯ ኮፍያ ጠብ አለች!
" በህግ አምላክ! "....አሉ አየር ላይ ( ማንን ይሆን? )
በሬው ጋሽ ብሩን አንጠልጥሎ ወደገንዳው ተመለሰና ገንዳው ውስጥ ጨመራቸው!( አስቀመጣቸው ልበል? )
ተረኛ የሚዘገን ሲፈልግ፡ ሰዉ ተተራመሰ!
ዞሮ ዘሎ ሲመጣ ጋሽ ብሩ ከገንዳው ብቅ አሉ!
አልጋ ስር የተረሳ ጫማ መስለው..😂
" ኮፍያዬን አላያችሁም? "
" አላየንም "
" ያችኋትናኮ አቀብሉኝማ "
" ሌላ ቀን ይውሰዷት "....በዚያ ላይ
" ቢወጋንስ? "
" እኔ አባታችሁ እንዴት ልውጣ ታዲያ? "
እንዳይወጡ ቆሟል ፊት ለፊት
" ኧረ ጠነባሁ ጎበዝ "
መቼስ ብዙ ስቀናል ያኔ። በስንት መከራ ተሸነፈ!
ታርዶም ጣጠኛ ነበር
የታረደ ቀን ጠዋት ቅርጫው ላይ ጫጫታ ይሰማል
ጨጓራው ተሰረቀ!
ያው ከሮቤል ውጪ መቼም ማንም አይሆንም!
የነሮቢ በር በሃይል ተንኳኳ!...ሮቢ ከፈተ
" ጨጓራውን መልስ! "
" ኧረ ጋሼ! የምን ጨጓራ? "
" ዛሬ ፊኛህን ተሰናበት! ልቆምበት ነው "
" እኔ አላየሁምኮ "
" ምንድነው በመዘፍዘፊያው ያስቀመጥከው "
" የባቢ ሽንት ጨርቅ ነው "
" እያጠብክለት? "
" አዎ "
" በፈርስ ነው የምታለቀልቀው? "
Credit:- Fikre Z Bhere Ethiopia