ኖኅ Book Delivery


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Telegram


The first and only book delivery service in Ethiopia. Order books from around the world at fair prices with fast delivery. Free delivery
ለአስተያየትና መፅሐፎችን ለማዘዝ ከታች ባሉት አድራሻ መልዕክት ያስቀምጡልን 👇
@Noahbook7

"ማንበብ ፋሽን ነው"
Join us @noahbookdelivery

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Telegram
Статистика
Фильтр публикаций


አልፈልግም ስትለኝ እምባዬ እንዳይመጣ ታግዬ ፈገግ አልኩኝ ። ለእምባዬ ፊት መስጠት አልፈለኩም ። የሄደን ሰው እምባ አይመልሰውም ብዬ ነው መሰለኝ !

ግን ከፋኝ ፦

ተደግፌባት ነበር ። አደጋገፌ በጥርጣሬ አልነበረም ። ከኔ እሷን አምናት ነበር ፣  እንዳልጎዳት ስጣጣር ነበር ። እንዳላሳዝናት ሁኔታዬን ሁሌ አየው ነበር !

አልፈልግህም ስትለኝ ....

ጭር አለብኝ  በግርግር ውስጥ ጭርታ ስሜት እንዴት ይወለዳል ? ጭርታው አስፈራኝ ጭርታው ድብርት ወለደ ። ስታብራራ  መልስ መስጠት አልፈለኩም ። እንዲ ስለው እንዲ ይላል ብላ ምላሽ ተሸክማ እንደመጣች ገብቶኛል ።

ምላሽ ካጠና ሰው ጋር ውይይት ትርፍ የለውም ። ማን ለማን ብሎ ከማን ጋ ይሆናል ?  ይሄ መስቀል ሳላጉረመርም የምሸከመው ነው !!

ግን ይሄን ሁሉ ሲሰማኝ ፈገግ ብዬ ነበር ።

እሷም አልፈልግህም ስለው ፈገግ ብሎ ነበር ትል ይሆናል ።
©Adhanom Mitiku
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery




















ዛሬ ደግሞ በዓለማችን እጅግ ተወዳጅነት ካገኙ self help መጽሐፎች በሀገራችን ከተተረጎሙት ውስጥ 10 ይዘን መተናል።

1. ስሜትህን በብልኃት መምራት - Emotional Intelligent

ዋጋ 450 ብር

2. 48ቱ የኃያልነት ሕጎች - The 48 law of power

ዋጋ 499 ብር

3. ሰውና ተፈጥሮ - The law of human nature

ዋጋ 450 ብር

4. የሕይወት ቀመሮች - 12 rules for life

ዋጋ 350 ብር

5. ለምን ብለህ ጀምር - Start wtih why

ዋጋ 350 ብር

6. የልማድ ኃይል - Atomic habit

ዋጋ 450 ብር

7. በትልቁ የማሰብ ኃይል - The magic of thinking big

ዋጋ 300 ብር

8. የምታስበውን ትሆናለህ - The power of positive thinking

ዋጋ 499 ብር

9. ሰባቱ የስኬት ምስጢራት - The 7 habit of highly effective people

ዋጋ 550 ብር

10. አስበህ ሀብታም ሁን - Think and grow rich

ዋጋ 399 ብር

ማሳሰቢያ ፦ እነዚህ የትርጉም መጽሐፎ ከ2 መጽሐፍ ጀምሮ ማዘዝ ትችላላቹሁ።
✅✅✅
መጽሐፎቹን በምታዙበት ወቅት እነዚህን በማድረግ ይተባበሩን
📚ማዘዝ የፈለጉትን መጽሐፎች
📞ስልክ ቁጥር እና
📍አድራሻ ይላኩልን።

ይህንን ካደረጉ በ24 ሰአት ውስጥ ያዘዙት መጽሐፍ እጅዎ ገብቶ እያነበቡት ያገኙታል።😊😍📚
⛵️
Free Delivery
ለማዘዝ 👇🏾

  @Noahbook7  0939115238
 
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


"ምከረኝ" አለችኝ "ከመምከር  ጋር ጥሩ ታሪክ የለኝም" አልኳት ።

አላመነችኝም ... ለማሳመን አልጣርኩም።
"ምራኝ እሺ " አለችኝ "ሲከተሉኝ እፈራለሁ ቀድሞ ግራ ይሂድ ቀኝ ይሂድ ሳሰላስል እደናበራለሁ" አልኳት ።
ትህትና መሰላት ።

"መንገድ የጠፋበት ሰው ቢመራ የት ያደርሳል?" አልኳት
"አለማወቅ ምቾት አለው" አለችኝ።
"አለማወቅን ካላወቅን ነው ምቾት ያለው"  አልኳት።

"እንደምትወደኝ ንገረኝ" አለችኝ።

"እወድሻለሁ" 
"እሺ ምከረኝ" አለችኝ ።
ድንገት ጭንቅላቴ ላይ ከመምከር ጋር ያለኝ ታሪክ መጣብኝ...

ጓደኛዬ ነበረች ፤ ሃዘን ገጠማት  የምትወደው ሰው፣ አንድ ያላት ሰው ሞተባት። መሰበሯ ሲጠነክር መከርኳት።
"ሃኪም ነኝ፤ የሞተ ሰው በየቀኑ አያለሁ ፣ ሲሰቃዩ የነበሩ ሰዎች፣ መኖር ሰፈልጉ የነበሩ ሰዎች፣ መዳን ብቻ የሚፈልጉ ሰዎች ሲሞቱ አያለው።

ሲሞቱ ትክ ብዬ አያቸዋለሁ፣ ህመማቸው ነው የሚቋጨው ፣ ትግላቸው ነው የሚቀርላቸው ፣ መሞት ለሟቹ እረፍት ነው የሚመስለኝ" ብዬ ገጠመኜን እያጣቀስኩ ነገርኳት .....
በሳምንቱ ሞተች እራሷን ገድላ።

ለማኖር ነበር የመከርኳት ፤ አይኗን በልቅጣ ቀልቧን ሰጥታኝ ስትሰማኝ ሞት እረፍት ነው ብላ እንድትጠነክር ነበር ። ግን መኖርን ነበር የቀማኋት  መሰለኝ.......

የቱ አፋፍ ላይ ቆማ ሰምታኝ ይሆን ?
'ለምንናገረው  ይሁን እንዴት ሰምተውን ለሚተረጉሙት ትርጓሜ ኋላፊነት መውሰድ ይቻለናል ?'  አያልኩ መብከንከን ፀፀትም ተከተለኝ።

በሃሳብ ጭልጥ ስል አይታ "አትመክረኝም?" አለች ።
ፈገግ አልኩ ...

ይልቅ እንጠጣ እስኪ።
©Adhanom Mitiku
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


How poets are born? 😂

ፍቅረኛህ ከተቀጣጠራችሁበት ሰአት ዘግይታ ስልክ ስትደውል አላነሳም ስትል የሚላክ ቴክስት:-

ኖርማል ሰዎች:-ማርፈድሽ ሳያንስ ደግሞ ስልክ አታነሽም በይ ሲመችሽ ደውይ ከእነ ከቤጋ ምሳ ልበላ ሄጃለሁ ቻው።

ገጣሚዎች:-
እመጣለሁ ብለሽ ጠብቄሽ ነበረ
ዳሩ ግን ችላ አልሽኝ ስልክ ማንሳት ቀረ?
እመጣለሁ ያልሽኝ መምጣት እንዴት ነበር
በመጠበቅ ብዛት አንገቴ ሲሰበር
ሲያዝንልኝ ነበረ የተቀመጥኩበት የሲባጎው ወንበር ።

እጠብቅሻለሁ እጠብቅሻለሁ የመጣው ቢመጣ
ሰማይ ቢያስገመግም መትረየስ ቢንጣጣ

እጠብቅሻለሁ እንደ ወፏ ጫጩት እንዳለች ከጎጆ
እስኪመጣ ድረስ ድጋሚ አባ ሳንጆ

በመቅረትሽ ምክንያት አይቀንስም ፍቅሬ
ግድም አይሰጠኝም የመንደሩ ወሬ
እጠብቅሻለሁ
እጠብቅሻለሁ

ሁለት ቀን ስልኳ ከተዘጋ ደግሞ አንድ የግጥም መድብል መፅሐፍ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጀባ😂😂

Koan ad
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


ማይክ ታይሰን ለእኔ ቦክሰኛ አይደለም!
በ Alex Abreham

ከህይወት ቡጢ ለማምለጥ ሲሮጥ ያቀረቡለት የቦክስ ጓንት ውስጥ የወደቀ ሚስኪን ወፍ ነው። እንደብዙ ጥቁር አሜሪካዊያን ገና በልጅነቱ ብዙ መከራ ተቀብሏል። አባቱን በእርግኝነት አያውቅም ነበር። አንድ ጀማይካዊ የታክሲ ሹፌር ነው ይባላል።ይሁንና እሱ አባቴ ብሎ የሚያስበው /የተነገረው/  ሴቶችን ለሴተኛ አዳሪነት የሚያቀርብ ሰካራምና ዱርየ ሰው ነበር። የሆነ ሁኖ የአባት ፍቅርም ይሁን ከለላ ሳይኖረው እናቱ ጋር መጠጥ አደንዛዥ እፅ ፣ወሲብና ወንጀል  በተሞላ በዘግናኝ ሰፈር ውስጥ ለመኖር የተገደደ ሚስኪን ህፃን ነበር። የባሰው አሳዛኝ ነገር እናቱ በሴተኛ አዳሪነት ስራ የተሰማራች ሴት መሆኗ። የምታሳድጋቸው በዚሁ ስራ ነበር።

በቤተሰቤ እንደተሳቀኩ ነው የኖርኩት ይላል በሀዘን።ብዙዎቹ  የተገፉ ህፃናት ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው፣ ከሰው ያጡትን ፍቅር ከአሻንጉሊት፣ ከቤት እንስሳት ወይም በሃሳባቸው ከሚፈጥሩት ታሪክ  ለማግኘት ይጥራሉ. . .ማይክ ታይሰን ርግብ ነበረችው የሚወዳት ! አንድ የሰፈር ጉልበተኛ እርግቡን ገደለበት  . . .የማይክ ታይሰን የታፈነ ብሶት ለመጀመሪያ ጊዜ ቡጢ ሁኖ የተገለጠው እዚህ እድለቢስ ወጣት ላይ ነበር ይላሉ ታሪኩን የፃፉ! ከዛማ ምኑ ቅጡ ማይክ ከአንደበቱ ቡጢው የሚፈጥን የለየለት ተደባዳቢ የጎዳና ልጅ ሆነ። እስርቤትና ፖሊስ፣ ክስና መታሰር. . .!

በመሰረቱ ይሄ ባህሪው በዛ መንደር መሞቻው ነበር! ግን አንድ ጣሊያናዊ የቡጢ አሰልጣኝ ዓይን አረፈበት! የማይክን የጎዳና ቡጢ ከሞት ወደህይዎት፣ ከእስር ቤት ወደቦክስ ሪንግ አመጣው! እነዛን ቁጡና በብሶት የተሞረዱ የማይክን ሰንጢ ጥፍሮች በጓንት ሸፍኖ ስፖርት አደረጋቸው። ደም ሳይሆን ዝናና ገንዘብ አፈሰሱ። የምታዩት ማይክ ታይሰን ተፈጠረ። ስሙ በዓለም ናኘ። ግን ምን ዋጋ አለው ገና በ20 ዓመቱ የአለምን የከባድ ሚዛን የቦክስ ሻንፒየን የተቆጣጠረው ማይክ የገንዘብ ጎርፍ አጥለቀለቀው፣ የልጅነቱን ስነልቦናዊ ህመም ፣ብቸኝነትና የውስጡን ረብሻ  የማያክም ገንዘብ። በ16 አመቱ በካንሰር ለሞተች እናቱ ያልደረሰ ገንዘብ ። እንደጉድ ብሩን ረጨው፣ ባለፈ ባገደመበት ሴት ነው፣ መጠጥ ነው፣ ድራግ ነው። ውድ መኪና ቅንጡ ቤት ... ከተራ ሰው እስከፖሊስ በውሃ ቀጠነ እየደበደበ ቅጣት ነው። ባዶውን ቀረ።

ይታያችሁ ፎርብስ አንድ ጊዜ የማይክን ሃብት 685 ሚሊየን ዶላር ገምቶት ነበር።  ዛሬስ? ከየኪሱ የቀሩትን ሳንቲሞች ጭምር ቆጣጥሮ የቀረው ሀብት 10 ሚሊየን ብር ቢሆን ነው።  ተራ በሚባሉ ፊልሞች ሳይቀር ተራ ገፀ ባህሪ ወክሎ  አሰሩኝ እያለ እስከመለመን ደርሶ ነበር። ማይክ ታይሰን ብዙዎች እንደሚያስቡት የሚንጎማለል አንበሳ ፣ ከአለት የጠነከረ የቡጢ ንጉስ አይደለም። ቤተሰብ እና ማህበረሰብ እንዲሁም ዘረኝነት የፈጠረው ጠባሳ ለዚህ ያበቃው የቦክስ ጓንት ውስጥ ጎጆውን የሰራ ሚስኪን ወፍ ነው። የልጅነት አዕምሮ ላይ የቆመ ጠባሳ በተጠቂው ቡጢ አይጣልም። ልጆች ላይ የሚሰነዘርን የህይወትን ቡጢ፣ የስነልቦና ፍላፃ  ይከላከል ዘንድ የተፈጠረ ጋሻ  ወላጅ ይባላል። ወላጅ ናችሁ? እንግዲያውስ ለልጆቻችሁ ህያው አጥር ሁኑ!
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


HOBBIT & LORD OF THE RINGS BY J. R. R. TOLKIEN

1. Hobbit

2. The Fellowship of the king

3. The Two Tower

4. The Return of the King

Total Price 5200 Birr + Free Delivery

ማሳሰቢያ ፦ መጽሐፎቹ ለየብቻ አይሸጡም 🙏
✅✅✅
መጽሐፎቹን በምታዙበት ወቅት እነዚህን በማድረግ ይተባበሩን
📚ማዘዝ የፈለጉትን መጽሐፎች
📞ስልክ ቁጥር እና
📍አድራሻ ይላኩልን።

ይህንን ካደረጉ በ24 ሰአት ውስጥ ያዘዙት መጽሐፍ እጅዎ ገብቶ እያነበቡት ያገኙታል።😊😍📚
⛵️
Free Delivery
ለማዘዝ 👇🏾

  @Noahbook7  0939115238
 
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


ዛሬ ደግሞ እንዴት አንደበተ ዕርቱ ተናጋሪ እንደምንሆን የሚውስ መጽሐፍ ይዘን መተናል።

S
su
sup
supe
super
superc
superco
supercom
supercomm
supercommu
supercommun
supercommuni
supercommunic
supercommunica
supercommunicat
supercommunicato
supercommunicator
supercommunicators


SuperCommunicators by Charles Duhigg

How to unlock the secret language of Connection

ፀሀፊው ከዚህ በፊት The power of habit የተሰኘውን መጽሐፍ አበርክቶልናል።

Price 1450 birr
✅✅✅
መጽሐፎቹን በምታዙበት ወቅት እነዚህን በማድረግ ይተባበሩን
📞ስልክ ቁጥር እና
📚ማዘዝ የፈለጉትን መጽሐፎች
📍አድራሻ ይላኩልን።

ይህንን ካደረጉ በ24 ሰአት ውስጥ ያዘዙት መጽሐፍ እጅዎ ገብቶ እያነበቡት ያገኙታል።😊😍📚
⛵️
Free Delivery
ለማዘዝ 👇🏾

  @Noahbook7  0939115238
 
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


The Folk of the air series by Holly Black

1. The Cruel Prince

2. The Wicked King

3. The Queen of Nothing

Total Price 4200 birr

ማሳሰቢያ ፦በቅርብ ጊዜ በውስጥ መስመር  ከምንጠየቀው "መላጣ የመሆኛዎች 5 መንገዶች" የሚል መጽሐፍ ሲሆን በቅርቡ ለንባብ ይበቃል ብዙዎች pre order እያደረጉ ነው   😂😂 ጊዜው የመላጦች መሆኑን ብዙ ነገር እያመለከተ ይገኛል። መላጣ ሳትሆኑ እንዳትሞቱ የሚሉ መፈክሮችም በየመሀል ከተሞች እየተሰሙ ይገኛሉ😂

የባልታዝር 400 ቪዲዮ እንዴት ሳትለቁልን የምትሉ ደንበኞች ግን እረፉ ። 😁🙏
✅✅✅
መጽሐፎቹን በምታዙበት ወቅት እነዚህን በማድረግ ይተባበሩን
📞ስልክ ቁጥር እና
📚ማዘዝ የፈለጉትን መጽሐፎች
📍አድራሻ ይላኩልን።

ይህንን ካደረጉ በ24 ሰአት ውስጥ ያዘዙት መጽሐፍ እጅዎ ገብቶ እያነበቡት ያገኙታል።😊😍📚
⛵️
Free Delivery
ለማዘዝ 👇🏾

  @Noahbook7  0939115238
 
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


ዛሬ የሰውዬው ልደት ነው እንኳን ተወለድክ ብለን እንዘክረው። 🙏🥰🙏

[ ''በሰቆቃ  ጥርሴን  አፋጫለሁ  ብለኸን ፣  ኋላ  ደግሞ  እየቀለድክ ሳቁልኝ  ትለናለህ ።  ቀልዶችህ  ጣዕመቢስ  መሆናቸውን  ስታውቅ ፣  በስነፅሁፍ  ዋጋቸው  ትመፃደቃለህ። 

መከራ  ደርሶብህ  ብታውቅም  እንኳን  ለስቃይህ  ቅንጣት  ዋጋ አትሰጠውም ።  ከምትቀባጥረው  አንዳንዱ  እውነት  ቢሆንም ፣ ይሉኝታ  ቢስነትህ  መጠን  የለውም ።  ከግብዝነት  የተነሳ ሐቅህን  አደባባይ  አውጥተህ  ታረክሰዋለህ ።  በርግጥ  ማለት የምትሻው  ነገር  አለ ፣  እቅጩን  እንዳትናገር  ግን  ፍርሃት  ጠፍሮ  ይዞሃል ፤  ለመናገር  የሚያበቃህ  ድፍረት  አጥሮሃል ። '' ]

[ notes from underground ፋሲል ይትባረክ የስርቻው መጣጥፍ ብሎ እንደተረጎመው ]

Happy Birthday Fyodor Dostoevsky.🎂
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery



Показано 19 последних публикаций.