የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Public Health, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing, Emergency & Critical Care Nursing, Surgical Nursing, Physiotherapy, Optometry እና Human Nutrition ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የመውጫ ፈተን ያለፋችሁ እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር በኩል ተመዝግባችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የጤና ባለሙያዎች በመጋቢት 2017 ዓ.ም ፈተናውን ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
ስለሆነም የዚሁ ፈተና ምዝገባ ከየካቲት 24 - መጋቢት 7/2017 ዓ.ም የሚከናወን ስለሆነ ፈተናውን የምትወስዱ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ print አድርጋችሁ በመያዝ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እያሳሰብን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115186275/0115186276 መደወል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፦
- እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት ተመዛኞች ምዝገባውን ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን እናሳስባለን።
- ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
- በጥር 30/2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ተፈትናቹ ያለፍችሁና በዚህ የብቃት ምዘና ፈተና ለመቀመጥ የተዘጋጃችሁ ነገር ግን ቴምፖረሪ ዲግሪ ከተቋማችሁ ያልደረሰላችሁ ተመዛኞች ከትምርት ሚኒስቴር ይህ ጉዳይ ቀጥታ ከሚመለከተው የስራ ክፍል የትብብር ደብዳቤ ማያያዝ የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እንሳውቃለን።
#MoH
📄
@officialexit