ፈጥሮሀል ጸሎቴን ሰምቶ የልጅ ፍቅሬን ጉጉቴን አይቶ
ከእንግዲህ ላንተ እኖራለሁ ከምንም በላይ እወድሀለሁ
እንደበትህ ይጣፍጠኛል ሳወራ ውዬ ባድር ያንሰኛል
ጨዋታህ ያስደስተኛል ህመምህ ደሞ ያስጨንቀኛል
ስስቴ ይለያል የኔ እንዳይኔ ብረት እንደ ብሌኔ
ተኝተህ መች አምንሀለሁ አይንህ ሲከደን እኔ እፈራለሁ
ስለይህ ደስ አይለኝም ግድ ሆኖ እንጂ ሰውም አላምንም
ስትዘል ስትቦርቅልኝ የነገ እጣህ ነው የሚታየኝ
አስባለሁ ብዙ እኔ ገና ያለኸኝ አንተ ነህና
ይባርከው ባንተው ተስፋዬን ጨምሮ ይስጥህ እድሜህን
ክፉ አይካህ ልጄን አ አይኔን አሌኝታዬን
👇👇👇
@old_musicaሼር🙏