OLD 1990 ethiopan Music⏮⏪⏯⏭⏩🎶


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Цитаты


ያፈቀረን ማፅናናት ለኛ ኖርማል ነው አያሳስብም😉
#Join ያርጉና
ፈታ እያሉ በውብ የፍቅር ቃላቶች ይደመሙ😍
ዘፈን , ግጥም ,

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Цитаты
Статистика
Фильтр публикаций


ሰፈራችን ጠንብቷል!!በመንደራችን የሚያልፍ ሁሉ አፊንጫው ይዞ እየተጠየፈን ነው ሚያልፈው።ነገሩ እኛም ግራ ቢገባን እንጂ መግቢያ መውጫ አጥተናል።መንደሩ አንዳች ጥንባት ተጠናውቶታል።በወይራ ጢስ የማይለቅ ግማ፤በእጣን የማይጠፋ ሽታ፤ሽቶ ቢነፋ አብሮ የሚሸት የሚቀረና ነገር መግቢያ መውጫ አሳጥቶናል....

አከባቢውን ብናስስም የሞተ እንስሳ አደለም ዝንቦች እራሱ ግማቱን ሸሽተው የጠፉ ይመስል ሰፈሩ ውስጥ እንግዳ ነገር አይታይም፡፡በጠዋቱ የመንደሩ ወጣት ራቅ ብሎ ካለ የድንጋይ ቁልል ላይ ተሰብስቦ ስለነገሩ ሲፈልጥ ደርሼ ተቀላቀልኩ...

እኔ ምለው የአቶ አያልነህ ዶሮወች ይሆኑ እንዴ??(አንዱ መላ ምቱን ጣል አደረገ

አረ እሳቸው ዶሮወቻቸው አልቀዋል የእቴ አቦዘነች አንቡላ ይሆናል እንጂ...

ሁሉም መደዳውን የተደረደሩ መንደርተኞችን ቤት እያሰላሰለ ሲያነሳ ሲጥል ድንገት ኦቾ ትዝ ብሎኝ ጥያቄዬን ሰነዘርኩ

እኔምለው ኦቾ የት ሔደ??ዛሬኮ ስላሴዎች ናቸው...

አይ የሱ ነገር አንዱ ፀበል ደሞ ጠፍቶ ይሆናል ወደማታ ብቅ ማለቱ አይቀርም ዝክሩን መቼስ አያልፋት ዛሬ ደሞ የአመት አደል?(አንደኛው በግድ የለሽነት መልሶልኝ ወደሞቀው ወሬ ሲሄድ እኔ ግን ኦቾ ላይ ሙጥኝ ብዬ በሀሳብ ጠፋሁ

ስሌላሴን ከሚሸጠው ኦቾሎኒ ላይ እየዘገነ እያደለ የሚዘክረውን የዋሁ ኦቾን ካየሁት ቆይቻለሁ።እርግጥ ስለሚታመም ድንገት እየተነሳ ፀበል የመሄድ ልምድ ስላለው መጥፋቱ ብርቅ አደለም፡፡ዲያቆን ነው፡፡ድሮ እንደውም ትዝ ይለኛል...የኔታ ከዘኬ

ቤት በፔስታል ቋጥረው እንዲያደርስ የላኩትን ምግብ መንገድ ላይ ቀምተነው በልተን የኔታ ሲጠይቁት''መንገድ ላይ ርቦኝ በላሁት''ያለበትን ቀን አረሳትም።ለኛ ብሎ እኮ ነው... የኔታም ስለሚወዱት አልተቆጡትም።ከዛ ወዲህ ኦቾ ልቤ ውስጥ ቀረ እናት እና አባቱ ከሰጡት ቀበሌ ቤት ውስጥ እየኖረ ኦቾሎኒ

እየሸጠ ነው ሚኖረው....እድሜ ልኩን ከአፍንጫው የሚፈሰው ደም አላስቀድስህ ቢለው እንጂ እንደሱም ያለ ሊቅ ዲያቆን አልነበረም።ሲያዜም ልብ ሳይሆን ነብስ ቀጥ የሚያደርግ ስርቅርቅ ድምፅ አለው እንደ ድምፁ መልኩም ሸጋ ነበር።
ከስላሴ ደብር የሱን ያህል ደሞዝተኛም አልነበረም... ግን ደሞ ህመምና አገልግሎቱ አልጣጣም ቢለው ለመኖር ሲል ቅዳሴውን ትቶት ወደ ንግዱ ገባ.

ደሞኮ እማማ ድማም አጠገብ ነው ሽታው ሚብሰው..

የሌላኛው ወጣት ድምፅ ከወሬወች ሁሉ መሀል ጆሮዬ ሲገባ ከሀሳቤ ብንን ብዬ ቆምኩ ቀድሞም ውስጤ ሲሰጋ የነበረው ነገር እንዳይሆን እየፈራሁ ነበር።ምክንያቱም ከእማማ ድማም ቤት አጠገብ ያለችው የኦቾ ደሳሳ ጎጆ ናት!! ኦቾ ደሞ ምንም ቢሆን በስላሴ ቀን ያውም በአመቱ ከደብሩም ከሰፈሩም ሊጠፋ አይችልም!!ሳላስበው እጄ እየተንቀጠቀጠ እንባዬ እርግፍ እርግፍ ሲል የተሰበሰቡት ወጣቶች አፈጠጡብኝ።እነሱም ከሀሳባቸው እየታገሉ እወነቱን መቀበል ስላልፈለጉ እንጂ የከነከናቸው ነገር እንዳለ ሁሉ...

ምን ሆነካል?? ምን ተፈጠረ??ምን አስበህ ነው???(በጥያቄ አፋጠጡኝ

ኦቾን ከነጋ አላያችሁትም!!ዛሬ ስላሴ ነው እና የት ሔደ ይባላል!??ፈራ ተባ እያልኩ ሳግ እያነቀኝ ጠየኩ

ይሄኔ ሁሉም ሳይነጋገር ብድግ ሲል ጀርባዬን ሰጥቼ እግሬን በእንባ አጀብ ወደ ኦቾ ቤት አሮጥኩት። ከኋላዬ የሚሽቀዳደም ብዙ ኮቴ ይሰማኛል ለወትሮዋ ተከፍታ ምትውለው የኦቾ ቤት ገርበብ ብላ ሳያት ደሞ ጩኸቴ እየበረታ እንደ እብድ እያደረገኝ በሩን በርግጄ ገባሁ።

ኦቾ    ኦቾቾቾ  ኦቾቾቾቾቾቾ

የሮጥኩበት ገልበቴ ከድቶኝ ተንበረከኩ ለመጮኽ አቅም አነሰኝ ለማልቀስ እንባ አነቀኝ ኦቾ ትንሽዬዋ ፍራሽ ላይ እንደተዘረጋ እጁን በዲያቆናት ወግ ለመግነዝ አመሣቅሎ የስሉስ ቅዱስን ስእል አቅፎ እስከወድያኛው አሸልቧል፡፡

ዲያቆኑ፤ምስኪኑ፤ታዛዡ፤ዝምተኛው፤ታታሪው፤ብቸኛው ኦቾ ጆሮ ጭው የሚያደርግ ለቅሶ እየተለቀሰለት እስከ ነብሱ ጥግ ድረስ የታመነባቸው ስላሴወች በሚከብሩበት ቀን ዝክራቸውን በሚዘክርበት ቀን አፈር ቀመሠ።

"በኑሯችን የምንታመን በሞታችን የማንከዳ ፍፁም የስላሴ ባርያወች

ያድርገን"

✍✍ ቻቻ ✍✍
join us 🫴🏾@OLDmy
By 👉🏽 @Amenuse 👁








ሰው በሰው መተኪያ አላገኘም ......❤️‍🩹
By 👉 @Amenuse ❤️‍🩹
Join us @OLDmy 👌🙏


ድንቅ እና ማራኪ ስራ ኤፍሬም ታምሩ
#አካሌ❤️
By👉 @Amenuse 👌❤️
Join us @OLDmy




ከኔ እረቀሽ...🙊😏
@Amenuse ❤️‍🩹
Join us @OLDmy 👌


@Amenuse ❤️‍🩹
join us @OLDmy




.
እርሷ…" በጣም ብዙ ነገሮችህ ተቀይሮዋል…"
እኔ… " በጣም ብዙ ነገሮች ቀይረውኛል…"

        ✍🏽 @Amenuse
@OLDmy


.          ምንህን ልባርክልህ?

  አንድ ወጣት ፈጣሪ ምስል ፊት ቆሞ እንዲህ ሲል ይፀልያል…" ፈጣሪዬ ያለኝን ሁሉ ባርክልኝ "

   ፈጣሪም መልሶ " ምንህን ልባርክልህ?…ስራህን እንዳልባርክልህ ስራ የለህም…ትዳርህንም እንዳልባርክልህ ትዳር የለህም…መልፋትህን እና መድከምህን እንዳልባርክልህ አትለፋም አትደክምም…ስለዚህ እንዲህ አድርግ …ቤትህ ሂድና ስራ ፈለግ ያኔ ባርክልሀለው…ራስህን ለትዳር አዘጋጅ የኔ ትዳርህን እሰጥሀለው…ልፋ፣ ድከም እና ጣር ያኔ እባርክልሀለው…"

         ✍🏽 @Amenuse 🙏❤️
          🤍 join us @OLDmy 🫶


☝🏾☝🏾☝🏾☝🏾☝🏾


እንኮን ለ2017 አመተ ምህረት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን  ❤️🙏

2017 ያሰብነው የሚሳካልን በደስታ በሰላም በጤና ሁነን ለአመነው አምላክ የምንታመንበት  የምናሳልፈው አመት ይሁንልን 🙏





Показано 16 последних публикаций.