ኦርቶዶክሳዊ ንድፍ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Дизайн


በኦርቶዶክሳዊ ንድፍ ውስጥ
--> ለአመታዊ በዓላት ፕሮፋይል
--> እለታዊ ጥቅስ
--> ጥያቄ ማግኘት ይችላሉ

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Дизайн
Статистика
Фильтр публикаций


🔴 ሰበር ዜና ዛሬ ትምህርት ሚኒሰትር ያወጣው አዲስ ያልተጠበቀ መግለጫ   ‼️

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ ከስር open ሚለውን ይጫኑ 👇👇




 ፫. ዕለተ ረቡዕ 
ሀ. ምክረ አይሁድ፡- ይህቺ ዕለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ፈሪሳውያን ጌታ ኢየሱስን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ምክር የመከሩበት ምክራቸውንም ያጸኑበትና ሰቅለው ይገድሉት ዘንድ የወሰኑበት ቀን በመሆኗ የአይሁድ የምክር ቀን ተብላ ትጠራለች፡፡ ይሁን እንጂ በዚሁ ምክራቸው ወቅት ጌታ ኢየሱስን እንዴት አድርገው እንደሚይዙት በጣም ይጨነቁ ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ወቅት በመሆኑ በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ብዙ ሕዝብ ትምህርቱን ያደንቁ ስለነበር ሁከት እንዳይፈጠር ከመፍራታቸው የተነሣ ነው፡፡ በዚህ ጭንቀትም ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው ተገኝቶ ጌታ ኢየሱስን እርሱ በመሳም አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ለዚህ ተግባሩም ሠላሳ ብር ወረታውን እንዲከፍሉት ከእነርሱ ጋር በመስማማቱና የምክራቸው ተባባሪ በመሆኑ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማር.፳፮፥፩-፭፣፳፮፥፲፬-፲፮፣ማር.፲፬፥፩-፲፩፣ሉቃ.፳፪፥፩)
ለ. የመልካም መዓዛ ቀን፡- ዕለተ ረቡዕ ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ተቀምጦ ሳለ በመላ ዘመንዋ ራስዋን በዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ ዕፍረት ኃጢአትን ይቅር የሚል መልካም መዓዛ ያለው አምላክ መጣ ስትል ውድ የሆነ ዋጋ ያለው ወይም የሦስት መቶ ዲናር ሽቱን ገዝታ ወደ እርሱ በመምጣትና በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው የመልካም መዓዛ ቀንም ትባላለች፡፡ በዚህም ምክንያት ከኃጢአትዋ የተነሣ መልካም መዓዛ ያልነበራት ማርያም እንተ እፍረት በዚህ በጎ ተግባርዋ መልካም መዓዛ ያለት ሆና ወደቤትዋ ተመልሳለች፡፡ (ማቴ.፳፮፥፮፣ዮሐ.፲፪፥፩-፰)
ሐ. የዕንባ ቀን፡- ይህቺው ማርያም እንተ ዕፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን እያጠበች በፀጉሯም እግሩን እያበሰች ስለ ኃጢአቷ ሥርየት ተማጽናዋለችና የዕንባ ቀን ትባላለች፡፡ (ማቴ.፳፮፥፮-፲፫፣ ማር.፲፬፥፫-፱፣ዮሐ.፲፪፥፩-፰)

💖💖

@orthodox_graphics_tube_et 🌟


 ፪. ዕለተ ሠሉስ
ሀ. የጥያቄ ቀን፡- ዕለተ ሠሉስ የጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል፤ ምክንያቱም ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰኞ ዕለት ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ  በዚች ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋል፡፡ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ያቀረቡለት ጥያቄም ‹‹ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለ ትምህርት በማስተማር ተአምራት ማድረግ ገበያ መፍታትን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?›› የሚል ነበር፡፡ እርሱም መልሶ ‹‹እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ፣ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው?›› ብሎ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል ከሰው ነው ብንልም ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ያከብሩታል እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን›› ተባባሉና ‹‹ከወዴት እንደሆነ አናውቅም›› ብለው መለሱለት፤ እርሱም ‹‹እኔም በማን ሥልጣን እንደዚሁ እንደማደርግ አልነግራችሁም›› አላቸው፡፡ ልቡናቸው በክፋት ሥራና በጥርጥር  ስለተሞላ ነው እንጂይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንደሚያደርግ ሳያውቅ ቀርቶ አልነበረም፡፡ (ማቴ.፳፩፥፳፫-፳፮፣ማር.፲፩፥፳፯-፴፫፣ሉቃ. ፳፥፩-፰)
ለ. የትምህርት ቀን፡- ይህቺ ዕለት ዕለተ ትምህርት ወይም የትምህርት ቀን በመባልም ትጠራለች፡፡ ጌታችን በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት በማስተማር የተሰጠው ስያሜ ሲሆን ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ መክሮ መመለስ እንደሚገባን ሲገልጽልን ነው፡፡ (ማቴ.፳፩፥፳፰፣፳፭፥፵፮፣ማር.፲፪፥፪፣፲፫፥፴፯፣ ሉቃ.፳፥፱፣፳፩፥፴፰)   💖💖

@orthodox_graphics_tube_et 🌟


⭐️⭐️ የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ስያሜዎች

፩. ዕለተ ሰኑይ ☀️

➡️ ሀ. አንጽሖተ ቤተ መቅደስ፡- በዚች ዕለት መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፡፡ በዚያም በደረሰ ጊዜ ቤተ መቅደሱ የጸሎት የመሥዋዕት ቤት መሆኑ ቀርቶ የንግድ ቤት ሆኖ ቢያገኘው ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት›› ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው ገርፎም አስወጣቸው፡፡ ይኸውም የእርሱ ቤተ መቅደስ የሆነውን ሰውነታችንን ኃጢአት ሰፍኖበት ቢያገኘው ራሱ ተገርፎ ተገፍፎ መከራ መስቀልንም ሁሉ ተቀብሎ ከሰውነታችን ኃጢአትን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ (ሉቃ.፲፱፥፵፮)
 
➡️ ለ. መርገመ በለስ፡- ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግስቱ ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ፤ በመንገድም ሲያልፍ ቅጠል ያላት በለስን ከሩቁ ተመለከተ፡፡ ወደ በለሲቱም በቀረበ ጊዜ ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ያንጊዜም ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ከአንቺ ፍሬ የሚበላ አይኑር›› ሲል በለሲቱን ረገማት፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ይህንን ሰሙት፡፡ በዚህም ምክንያት ይህች ዕለት በለሲቱ የተረገመችባት ቀን ናትና መርገመ በለስ ተብላ ትጠራለች፡፡ (ማር.፲፩፥፲፩-፲፬)


በዚህ አገላለጽ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ስትሆን ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባር ነው፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስ ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈልጎ አላገኘባቸውም፡፡ እስራኤል፦ ሕዝበ እግዚአብሔር፣ የአብርሃም ዘር መባልን እንጂ የአብርሃምን ሥራ በመሥራት በምግባር በሃይማኖት ጸንተው መኖር አይፈልጉምና ደግ ሰው አልተገኘባቸውም፡፡


በሌላ በኩል ደግሞ በለስ የተባለች ኦሪት ናት፡፡ ኦሪት በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛትም አማናዊ ድኅነትን የምታሰጥ ሆና አላገኛትም፡፡ ይሁን እንጂ በእርሷ ድኅነት ባይገኝባትም ‹‹ኦሪትና ነቢያትን ከመፈጸም በቀር ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ›› በማለት ሕገ ኦሪትን ፈጽሟታል፡፡ ከዚህም ባሻገር በለስ የተባለች ኃጢአት ናት፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አግኝቷታል፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሠሩት ለጊዜው ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም በአንቺ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ሲል ነው፡፡ በለሲቱ ስትረገም ፈጥና መድረቋም በአዳም ምክንያት ያገኘን በደል በእርሱ እንደጠፋልን ለመግለጽ ነው፡፡ 💖💖

@orthodox_graphics_tube_et 🌟


አረ ሪያክሽን ይጎለናል


ሰሙነ ሕማማት ተብሎ የሚጠራው ወቅት ከዐቢይ ጾም መጨረሻ ከሆሣዕና ዋዜማ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ባሉት ቀናት ውስጥ ያለው ሳምንት ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ይህንን ወቅት አስመልክቶ  በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ‹‹ውእቱ ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ፤ እርሱ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤›› በማለት የነገረ ሕማማቱን ምሥጢር አስቀድሞ ተናግሮአል፡፡ በዚህም መሠረት በኋለኛው ዘመን እግዚአብሔር ወልድ ስለኛ ስለ ሰው ልጆች ድኅነት ሲል ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋም ነፍስ ነሥቶ በፈቃዱ ሰው ሆኖ በፈቃዱ መከራ መስቀልን ተቀበለ፡፡ በመስቀሉም ላይ ሳለ በፈቃዱ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጠ፡፡ በዚህም መሠረት እኛም በእርሱ በአምላካችን የሆነበትን መከራ መስቀሉን ሁሉ የምናስብበት ሳምንት በመሆኑ ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ (ኢሳ.፶፫፥፬፣ማቴ. ፰፡፲፯፣ዮሐ.፩፥፳፱)


ከ፻፹፰-፪፻፴ ዓ.ም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ የነበረው ቅዱስ ድሜጥሮስ እግዚአብሔር አምላክ በገለጠለት የጊዜ ቀመር (ባሕረ ሐሳብ) መሠረት ሰሙነ ሕማማት ከዐቢይ ጾም ቀጥሎ እንዲሆን ተወስኗል፡፡ ቤተ ክርስቲያንም በቀመረ ድሜጥሮስ ዓመታትን በንኡስ በማእከላዊና በዐቢይ ቀመር እየቀመረች አጽዋማት የሚገቡበትን በዓላት የሚውሉበትን ጊዜ ለምእመናን ታሳውቃለች፡፡ ይህን ሳምንት ላቲናውያንና ግሪካውያን ታላቁ ሳምንት ሲሉት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደግሞ ሰሙነ ሕማማት በማለት ትጠራዋለች፡፡


በዚህ ሳምንት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ በሙሉ ያደረገውን ትድግና ቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም ግብረ ሕማማት የተባለው የቤተ ክርስቲያናችን መጽሐፍ ነገረ ሕማማቱን መከራ መስቀሉን በሰፊው ይናገርለታል፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም መድኃኒታችን ክርስቶስ አንዳች በደል ሳይኖርበት በሰውነቱ የደረሰበትን ሕማሙንና መከራውን ሞቱንም እያሰብን ይህንን የዐቢይ ጾምን መጨረሻ ወቅት ወይም ስምንተኛውን ሳምንት በካህናቱ መሪነት ሁላችን ምእመናን በተረጋጋ ኅሊና  አብዝተን በመጾም፣ በመጸለይና በመስገድ እንድናከብር ሥርዓትን ሠርታልናለች፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ሁሉ ይህንን የጌታን የሕማማት ሰሙን ከተድላ ከደስታ በመራቅ ነገረ መስቀሉን እያሰቡ በኀዘንና በልቅሶ ሆነው የሚያሳልፉት፡፡


@orthodox_graphics_tube_et 🌟


#ሆሳዕና


“እንደ ህጉ ደም ሳይፈስ ስርየት የለምና ነገር ሁሉ በደም ይነጻልና እርሱ ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር በግ ሆኖ የመጣ ነውና ስለእኛ ደሙን ሊያፈስ ሞተ። ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ እንደተናገረው እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።”

ዕብ 9:22


ደና አደራቹ ❤️


እስኪ ደስ ሚላቹን የንስሀ(የህማማት) መዝሙር ላኩልም ቪድዮ እንስራበት


ለስቅለት ቀን scheduled አድርገነዋል ❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥

ሪያክሽን ብዙ ካደረጋቹ እንለቀዋለን


አረ ሪያክሽን ይጎለናል


ቪድዮውን ሰርተን ጨርሰናል ❤️‍🔥❤️‍🔥


ኒቆዲሞስ ❤️


#መድኃኒዓለም


አዲስ ቪድዮ በYoutube ቻናላችን በቅርብ ቀን❤️❤️❤️

📱 በዩትዩብ ቻናላችን በቅርብ ቀን

ዩትዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ለማድረግ ይህንን ይጫኑ


✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✝️@orthodox_graphics✝️
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨


6. #ገብርኄር
  ገብርኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አገልጋዮችና አገልግሎታቸው በምሳሌ ያስተማረው ትምህርት የሚነገርበት ሳምንት ነው፡፡ ይኽውም አንድ ባለጸጋ ሰው ወደ ሌላ ሀገር ከመሔዱ አስቀድሞ ለሦስት አገልጋዮቹ እንደየአቅማቸው አንድ፣ ሁለት እና አምስት መክሊት እንደሰጣቸውና ከሔደበትም በተመለሰ ጊዜ ሁሉንም ጠርቶ ከነትርፉ መክሊቱን እንዲመልሱለት እንደጠየቃቸው ያስተማረበት ነው፡፡ ሁለቱ አገልጋዮች በእጥፍ አትርፈው ባለአምስቱ ዐሥር አድርጎ፣ ባለሁለቱም አራት አድረጎ መልሰውለታል፡፡ ባለአንዱ መክሊት ደግሞ መክሊቱን መሬት ቆፍሮ ቀብሮት ነበርና ሳያተርፍበት ያንኑ መልሶለታል፡፡ የቀበረበትንም ምክንያት ሲናገር ‹‹ጌታ ሆይ አንተ እኮ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ስለዚህ ፈራሁ ሔጄም መክሊትህን በምድር ቀበርኩት›› ብሏል፡፡ ባለጸጋውም አትርፈው የመለሱለትን ‹‹እናንተ ታማኝ አገልጋዮች በጥቂቱ ታምናችኋልና በብዙ እሾማችኋለሁ ወደ ጌታ ደስታ ግቡ›› ብሎ ሾሟቸዋል፡፡ ቀብሮ የመለሰውን ግን ‹‹አንተ ክፉና ሀኬተኛ ባሪያ…አትርፈህ ብትመልስ በተሸለምክ ነበር፤ ስለዚህ ያለውን ውሰዱበትና ዐሥር ላለውም ጨምሩለት ላለው ይጨመርለታል ከሌለው ግን ያንኑ ይወስዱበታል፤ እርሱን ግን ወደ ውጭ አውጥታችሁ ጣሉት›› ብሎ ፈረደበት፤ (ማቴ 25፥14-30)፡፡
   በምሰሌያዊ ትምህርት ባለጸጋ የተባለው የሁሉ ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ አገልጋዮች የተባሉት ምእመናን ናቸው፤ መክሊት የተባለው ደግሞ ለምእመናን የተሰጣቸው መንፈሳዊ ጸጋዎች ናቸው፡፡ አትርፈው የመጡት በተሰጣቸው ጸጋ ለራሳቸው ተጠቅመው ለሌላውም ተርፈው መልካም አርአያና ምሳሌ ሆነው የሚኖሩ አገልጋዮች ምሳሌ ሲሆኑ የተሰጠውን መክሊት ቀብሮ ሰንብቶ ያንኑ የመለሰው ደግሞ የተሰጠውን ጸጋና ዕድሜን በከንቱና በዋዛ ነገር ሲያባክን  የሚኖር ምእመን ምሳሌ ነው፡፡ አትርፈው የመጡት የተሸለሙት መንግሥተ ሰማያትን ሲሆን ቀብሮ የመጣው ደግሞ የተፈረደበት ትሉ ወደማያንቀላፋ እሳቱ ወደማይጠፋ ገሃነመ እሳት ነው፡፡ የተማረውን በልቡ ይዞ የኖረ ሰው፣ ሃይማኖት በልብ ነው፤ መናገር አያስፈልግም፤ የልቤን እግዚአብሔር ያውቀዋል፤ የእንጀራ ጉዳይ ነው ምን ላድርግ? እያሉ ራሳቸውን የሚያታልሉ ባለሥልጣናት የባለአንድ መክሊቱ አገልጋይ ምሳሌ ናቸው፡፡ ሳምንቱ ገብርኄር ተብሎ የተሰየመው በታማኞቹ አገልጋዮችና በታማኝነታቸው ነው፡፡
   በዚህ ሰንበት የሚሰበከው ምስባክ ‹‹አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው፤ በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አወራሁ እነሆ ከንፈሮቼን አልከለክልም አቤቱ አንተ ጽድቄን ታውቃለህ›› (መዝ 39፥8-9) የሚለው ነው፡፡ እኛም ሳምንቱን ስንዘክር ከእግዚአብሔር የተሰጠንን ጸጋ መጠቀም እንጂ መቅበር እንደሌለብን ራሳችንን እየጠየቅን መሆን አለበት፡፡ ቀሪ ዘመናችንንም ስላለፈው ዘመን ኃጢአት ንስሐ ለመግባት መወሰን ይገባናል፡፡


“አብሳሪ ድንግል
የራማው ልዑል
ስዕለት የምትሰማ
ቅዱስ ገብርኤል 🤍”


ለማጠብ ባልበቃ
እግርህን ልከተል ፥ በጥላህ ሥር ልረፍ፤
ላንዴም ቢሆን ልንካ ፥ የቀሚስህን ጫፍ፤
ለደምህ ቢያበቃኝ ፥ ለከበረው ሥጋ፤
ጫፉን ብቻ ስጠኝ ፥ ከምሕረትህ መዝገብ ፥ ሰው ሳያይ ልጠጋ።

ከመቅደስህ ስመጣ ውድህን እንዳገኝ
ያኔ እንደተጠጋሁ የዛኔው ና በለኝ
ስትምረኝ ውሰደኝ

✍️ከዘማሪ ዲ.ን ጸጋ ሥላሴ
“ስትምረኝ ውሰደኝ” መዝሙር የተወሰደ

Показано 20 последних публикаций.