ጥቅምት 24/2017 #ፃድቁ_ቅዱስ_ተክለሃይማኖት
"የፃድቃን መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.111፥6"
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ፃድቁ አባታችንን በምልጃ ፀሎታቸዉ እንዲራዱን ለምንማፀንበት #ለአቡነ_ተክለሃይማኖት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉የስማቸው ትርጉም የሃይማኖት መሰረት ፍሬ የሆነው አባታችን ከእናታቸው እግዚሐርያ ከ አባታቸው ፀጋዘአብ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታህሳስ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ
👉አባታችን #የሃይማኖት_ተክል ናቸው ጻድቁ አባታችን ገና እንደተወለዱ በሶስተኛው ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ በመውረድ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ እያሉ በመስገድ የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል
👉እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ #አዲስ_ሐዋርያ አድርጎ መርጧቸዋል ጻድቁ አባታችን ክብረ በዓላቸው እንደሚከተለው ነው
✝️ህዳር 24 ቀን ሃያ አምስተኛ ካህናተ ሰማይ ሆነው በሰማይ የስላሴን መንበር ያጠኑበት እለት ነው
✝️ታህሳስ 24 ቀን የአባታችን ልደት ነው
✝️ጥር 24 ቀን የአባታችን ሰባረ አፅሙ ነው
✝️መጋቢት 24 ቀን የአባታችን ፅንሰታቸው ነው
✝️ግንቦት 12 ቀን የአባታችን ፍልሰተ አፅሙ ነው
✝️ ነሐሴ 24 ቀን የአባታችን እረፍታቸው ነው
👉የፃድቁ አባታችን #የቅዱስ_ተክለሃይማኖት ቡራኬ ይድረሰን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን የተባረከ ይሁንልን "አሜን"
በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት በእነዚህ አብያተክርስትያናት በዓለ ንግሱ ይከበራል።
፩) ኮልፌ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት እና ቅዱስ ገብርኤል
ልዩ ስም፦ ኮ/ቀ/ክ/ከ ፊሊዶሮ
፪) ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት
ልዩ ስም፦ ልደታ /ክ/ከ መርካቶ
፫) ሲኤምሲ መካነ ጻድቃን አቡነ ተክለሃይማኖትና ቅድስት ልደታ
ልዩ ስም፦ የካ ክ/ከ መሪ ሎቄ ለገጅጃ
፬) ደብረ ቢታንያ አቡነ ተክለሃይማኖት እና ቅድስት ልደታ ለማርያም
ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ቆሬ 5 ቁጥርና 2 ቁጥር ማዞርያ
፭) ቤላ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ የካ ክ/ከ ቤላ ፈረንሳይ ፓርክ
፮) መሪ ምስራቀ ፀሐይ መካነ ቅድስት ሥላሴ ቅዱስ ዑራኤልና አቡነ አረጋዊ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦
ለሚኩራ ክፍለ ከተማ
ልዩ ቦታው መሪ/አያት
በዓለ ንግሱ ይከበራል።
[ልዑል እግዚአብሔር ]
በፍቅር፣ በሠላም፣ በጤና ያገናኘን።
🙏 አቡነ ተክለሃይማኖት ይጠብቁን 🙏
₃..አሜን | Amen..₃