Репост из: Beles Media - በለስ ሚዲያ
በመንግስት ታጣቂዎች የተገደለው ሀኪም ጋር አብረውት የተማሩ እና የሰሩ ጓደኞቹ ከሰጧቸው አስተያየቶች መካከል !!
******
ቀዳሚው ሰው
ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ልፋትህን አፈር በላው እኮ። አንዱ ተቀጠፈ! አይ ርጋታ! አዬ ትህትና! 2005 ዓ/ም የወርቅ ሜዳልያ ሸልመህ፣ ህዝብህን አገልግል ብለህ የሸኘኸው ፍሬህ በአጭር ቀረ።
የጅማዋ ኪዳነ ምህረት ደጅሽን በነጋ በነጋ 6 ዓመት ሙሉ ይሳለምሽ የነበረው ልጅሽ፣ ደሙ በከንቱ ፈሰሰች!!! የሰማይ ቤቱን አደራሽን!!!
ሌላው ጓደኛ
1 ሚሊዮን ሰው ነው የሞተው ብቻውን አልሞተው። ትህትናው እውቀቱ እርጋታው ሁሉን ጥበብ የታደለ ሀኪም ነበር። እግዚአብሔር ለልጆቹ እና ለዚ ምስኪን ህዝብ ሲል ባቆየልን የነበር። ያሳዝናል በጣም በጣም። ወንድማለም እግዚአብሔር ነፍስህን ይቀበላት። ነፍስ ይማር
ሶስተኛው ሰው
በእውቀት በፀባይ በትህትና በሁሉም ነገር የባረከህ እንዲህ በአጭር ሊወስድህ ነው ???
ወይኔ እኔ አፈር ልብላልህ የኔ ትሁት !!
አራተኛው አስተያየት ሰጭ
ዶር አንዷለም ዳኜ አብሮኝ የተማረ ባቼ ነው። የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊት ሃኪም ነው። በትምህርት ጀግንነቱ በዘመናት መካከል እንደ አጋጣሚ ልታገኘው የምትችለው እንቁ ልጅ ነው። ባህርዳር ሲሰራ አምሽቶ ሲወጣ ገደሉት እያሉኝ ነው😪😪😪 እጅግ በጣም ያማል። ነፍስህ በሰላም ትረፍ ወንድማለም!!!
አምስተኛው አስተያየት ሰጭ
"አንዱ"ን አይደለም ያጣነው ሚሊዮኖችን እንጂ።
አይ ወንድሜ እንደዚህ በቅርቡ ትጠራለህ ብዬስ አስቤም አላውቅ ነበር። ላንተስ ከዚህ ከንቱ የመባላት ዓለም ነው የተገላገልህ። ወዮ ለሚሊዮኖች! ወዮ ለሀገሬ! ወዮ ለወገኔ! 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭