ጅማ- ጌራ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በምን ሁኔታ ይገኛሉ👇
እናት ፓርቲ፣ በኦሮሚያ ክልል፣ ጅማ ዞን፣ ጌራ ወረዳ ከካቲት 6 ጀምሮ በተከሰተው የጸጥታ ችግር የተፈናቀሉ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እየተደረገ መኾኑን መረዳቱን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ነዋሪዎች የተደራጁ ኃይሎች ባደረሱት ጥቃት ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ካፋ ዞን፣ ጊምቦ ወረዳ መፈናቀላቸው ተዘግቦ እንደነበር ይታወሳል። የከፋ ዞን በተለይም የጊምቦ ወረዳ አስተዳደር፣ ተፈናቃዮቹን በትምህርት ቤቶችና ድንኳኖች በማስጠለል ድጋፍ ማድረጉን ፓርቲው ጠቅሷል፡፡ አኹንም ያላስረከባችሁትን የጦር መሣሪያ አምጡ” የሚል ግፊት በነዋሪዎች ላይ እየደረሰ ነው ያለው ፓርቲው፣ በዜጎች ግድያና ቤት የማቃጠል ወንጀሎች የተሳተፉ አካላት ላይ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ ለፍርድ አለመቅረባቸው ችግሩን አባብሶታል ብሏል። ፓርቲው፣ በአካባቢው ሠፍሮ የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት የማረጋጋት ሥራ እንዲሠራና መንግሥትም ቤታቸው ተቃጥሎባቸው በድንኳኖችና ትምህርት ቤቶች የተጠለሉ ነዋሪዎች ባፋጣኝ የሚቋቋሙበትን ኹኔታ እንዲያመቻች ጠይቋል።via wazema