አድዋ፡ የመጨረሻው ውጊያ
« ከዚህ ቀጥሎ አጼ ምኒልክ ጦራቸውን ወደ አድዋ በመምራት የአድዋ ሸለቆ ከሚታይበት ከፍታ ላይ ሰፈሩ። ራስ መኮንን፣ ራስ መንገሻ እና ራስ ሚካኤልን ከመሃል ወራሪ፤ እራሳቸውን እና እቴጌን ከመካከል፣ ንጉሥ ተክለሃይማኖትን በስተቀኛቸው፣ ራስ አሉላን በስተግራ አደረጓቸው።
ጀነራል ባራቴሪ ከቅርብ ርቀት ላይ ቢሆንም የስንቅ እና ቁሳቁሶች እጥረት እየገጠመው ነበር። ስለዚህ በጥር ወር የምኒልክም ጦር ስንቅ እስኪያልቅ ጣልያኖች እንዲጠብቁ አዞ ነበር። ነገር ግን የጣልያን መንግሥት እርምጃ ውሰድ ዝምብለህ ከምትጠብቅ የሚል ትእዛዝ ስለላከ ሊተገብረው አልቻለም።
በየካቲት 23 ጥዋት ላይ ሊያጠቃ የነበረው ባራቴሪ ሦስት ሻለቃ ጦሮችን አሰለፈ። ጀነራል አልበርቶን በስተግራ፣ ጀነራል ዳቦርሚዳ በስተቀኝ እና ጀነራል አሪሞንዲ ከመካከል አድርጎ ደጀን ላይ ደግሞ ጀነራል ኢሌናን አስቀመጠ። አልበርቶን ራሱን ኪዳነምሕረት በምትባል ከፍታ ላይ አስቀምጦ የኢትዮጵያውያኑን እንቅስቃሴ ለመከታተል አስቦ ነበር።
ነገር ግን እሱ እንዳቀደው ሳይሆን ጀነራል አልበርቶን ዘው ብሎ ራስ አሉላ በሠፈሩበት አካባቢ ገባ። ሯጮች አጼ ምኒልክ ጋር ገስግሰው ጣልያን በጠዋት እንዳጠቃ ነገሯቸው። ዘበኞች ውጊያ ጀምረው ነበር። 25 ሺህ ሰዎችን ሲልኩላቸው አሪሞንዲን ከነበረበት ነቅለው እንዲሸሽ አደረጉት። 12 ሰዓት ላይ አልበርቶንን እና አስካሪዎቹን ወደ አሪሞንዲ ጦር ገፍተው አልበርቶንን ምርኮኛ ያዙት። የዳቦሪሚዳ ጦር እንኳን አልበርቶንን ሊያድን እራሱ ሳያስበው በራስ ሚካኤል ሰፈር ውስጥ ገብቶ ስለተከበበ ተደመሰሰ። የቀሩት የባራቴሪ ጦረኞች በንጉሥ ተክለሃይማኖት ተቆርጠው ተገደሉ። ቀን 6 ሰዓት ሲሆን በምኒልክ ሥር የዘመቱት የጦር መሪዎች በጦር ሜዳው ተሳትፈው ራሳቸውን አስመስክረዋል። የተረፉት ጣልያኖች ወደ ኤርትራ እግሬ አውጪኝ ሸሹ። እነሱም በኢትዮጵያ ገበሬዎች እየተጠቁ ኤርትራ የገቡት በጣም ጥቂቶቹ ናቸው።
የአድዋ ጦርነት እንዲህ ተፈጸመ። ከ4 እስከ 5 ሺህ ኢትዮጵያውያን ሞተው ወደ 8 ሺህ ያህል ቆስለዋል። ጀነራል አልበርቶን እና 3ሺህ ጣልያናውያን ምርኮኛ ተወሰዱ። ከእነዚህ 200 የሚሆኑት በቁስሎቻቸው ምክንያት ሲሞቱ ወደ 800 አስካሪዎች ግራ እግራቸውን እና ቀኝ እጃቸውን ተቆረጡ። ከጠላት ጋር አብራችኋል በማለት። ጣልያኖች ወደ 7ሺህ ሰዎች ሲሞቱባቸው፣ 1500 ያህል ቆስሏል። 11 ሺህ ጠመንጃዎቻቸውም ተማርከዋል። »
ከፀሐይ ብርሃነሥላሴ፡ ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት Ethiopian Warriorhood
ገጽ 234
ከጦቢያን በታሪክ ገጽ የተገኘ