📓🌓 ቅምሻ 🌗📓
🇪🇹 ክፍል ስምንት 🇪🇹
የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦
ፍቅር ከጥላቻ በላይ ዘልቆ መሄድን ይጠይቃል፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እና ማንዴላ በሰዎች እና በህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ፍቅር ያለውን የማይበገር የአሸናፊነት ኃይል፣ እንዲሁም ፍቅር በዘር፣ በጎሳ እና በኃይማኖት የተዘራን የጥላቻ ካንሰር የመፈወስ ችሎታ እንዳለው በግልጽ አስተምረውናል፡፡ ማንዴላ ለመጥላት እና በቀልን ለመፈጸም ምክንያት አላቸው፡፡ ለ27 ዓመታት የማንዴላ ስም የእስረኛ ቁጥር 46664 ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በፌብሯሪ 1990 ጧት ከእስር ቤት ተለቅቀው ከእስር ቤቱ በር ሲወጡ ከሚሊዮን ዶላር ዋጋ በላይ የሚያወጣውን ፈገግታቸውን አሳይተዋል፡፡ ለ27 ዓመታት ከቤተሰቦቻቸው ነጥለው በእስር ቤት ውስጥ ባማቀቋቸው የአፓርታይድ ጌቶች ላይ ምንም ዓይነት የጥላቻ ስሜት አላሳዩም፡፡ ማንዴላ ታላቅ ትምህርት አስተምረውን አልፈዋል፣ እንዲህ በማለት፣ “እየተራመድኩ ወደ በሩ በምቃረብበት ጊዜ ይህ ሁኔታ ወደ ነጻነት እየመራኝ እንደሆነ አስብ ነበር፡፡ የበቀልተኝነት ስሜቴን እና ጥላቻዬን እዚያው እስር ቤት ጥዬው ካልወጣሁ እዚያው እስር ቤት እንዳለሁ እቆጥረዋለሁ፡፡“ በማለት የጥላቻን መጥፎነት በግልጽ ተናግረዋል፡፡ ማንዴላ ፍጹም የጥላቻ እስረኛ አልነበሩም፡፡ እስረኛው የአፓርታይድ ጥላቻ ነበር፣ እናም አስረኞቹ የአፓርታይድ አለቆች እና ጌቶች ነበሩ፡፡ ማንዴላ ከእስር ቤት በመውጣት በጥላቻ ሰንሰለት ከአፓርታይድ ግንብ ጋር የታሰሩትን እውነተኞቹን የአፓርታይድ እስረኞች ከጥላቻ፣ ከፍርሀት፣ እና ከበቀልተኝነት ነጻ ለማውጣት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያሉት ገዥዎች በጥላቻቸው የሚቀጥሉ ከሆነ በደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ የደረሰው ዕጣ ፈንታ የሚደርስባቸው መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
በአፓርታይድ የአገዛዝ ዘመን ጊዜ “ነጻዎቹ” ነጮች እውነተኛው የማይቀረው የብዙሀን አገዛዝ በሚመጣበት ጊዜ ለብዙ ጊዜ በጭቆና ቀንበር አስረው ሲያማቅቋቸው የነበሩት ጥቁር አፍሪካውያኖች ምን ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ ሌት እና ቀን ያሰላስሉ ነበር፡፡ በጥቁር አፍሪካውያን ላይ የነበራቸው ጥላቻ እንቅልፍየለሽ ሌሊቶችን ብቻ እንዲያሳልፉ አላደረጓቸውም፣ ሆኖም ግን ልቦቻቸው፣ አዕምሯቸው እና ነብሳቸው እንዲሁም ስብዕናዎቻቸውም ጭምር እንዲሰበሩ አደረጋቸው እንጅ፡፡
ሙት መንፈሶች አደረጓቸው፣ ነጻ ሆነው ባሏቸው ኃብቶቻቸው ለመደሰት ባለመቻል የቁም ሙት አደረጓቸው፣ እንዲሁም በኤሌክትሪክ እና በእስር ቤት የሽቦ አጥር ታጥረው የእራሳቸው ጎረቤቶች የእስር ቤት በሮች ሆኑባቸው፡፡ በእርግጥ በጦር ካምፕ የሚኖሩ ህዝቦች ሆኑ፡፡
ምንጊዜም የተሻለ መንገድ አለ፡፡ የጥላቻ ትችት ከማቅረባችን በፊት እውነተኛውን ነገር ለማወቅ የበለጠ ጽናት ሊኖረን ይገባል፡፡ ስለዳግማዊ አጼ ምኒልክ፣ ስለ አጼ ኃይለስላሴ፣ ስለ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እውነኛውን ነገር ማቅረብ ይኖርብናል፡፡ እነርሱን መጥላት ሳይሆን ከስህተቶቻቸው እንማር፣ እኛ በህይወት ያለነው የእነርሱን ስህተት መድገም የለብንም፡፡ ጥላሸት በመቀባት ላይ ላለመሰማራት ከእነርሱ ስህተት እንማር፣ ነገር ግን የእርቅን መንገድ በመፈለግ የእነርሱን ስህተቶች እናርም፡፡ ከኢትዮጵያ ወጣቱ ትውልድ ጋር ህብረት በመፍጠር ማንም ወንድ ወይም ሴት በማንነቱ/ቷ፣ በዘሩ/ሯ ሳይሆን ሰው በመሆኑ/ኗ፣ አፍሪካዊ/ት እና ኢትዮጵያዊ/ት በመሆናቸው ብቻ በመመልከት አዲሲቷን ፍቅር የነገሰባት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ፡፡ ማንም ወንድ ወይም ሴት ባለው/ላት ስልጣን በመመካት ባልታጠቁ ዜጎች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጦር እልቂት ሊያዝዝ/ልታዝዝ የማይችሉበት እና ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብም ሊወገድ የሚችልበት ነጻ ህሊናን በመፍጠር አዲሲቷን ፍቅር የነገሰባት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ፡፡ በእያንዳንዱ/ዷ ግለሰብ የጎሳ፣ የእምነት ወይም የቋንቋ ልዩነት ሳንፈጥር በአንድነት በመሆን የእያንዳንዱ/ዷ ዜጋ መብት እና ክብር የሚጠበቅበትን ህብረተሰብ ለመፍጠር እንነሳ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው የወደፊቱን ብሩህ ዘመን ለመፍጠር የምንችለው፡፡ ለብዙ ጊዜ በመቆየት በጊዜ ደመና ተሸፍኖ የደበዘዘውን ነገር ቆፍሮ በማውጣት እና ጥላሸት በመቀባት አይደለም ፍቅር የነገሰበትን የወደፊቱን ትውልድ መገንባት የምንችለው፡፡
በጥላቻ ንግግር አንዘን ወይም ደግሞ አንቆጣ፡፡ ምንም ዓይነት እርባና የለውም፡፡ ይልቁንም ጥላሸት የመቀባት ዘመቻውን በሰከነ መልክ እናጋልጥ፡፡ መላዕክ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ስህተት እና ውሸት መሆኑን እና የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት ለመቀበት እና ለመበረዝ የሚደረገውን መዋተት እናጋልጥ፡፡ ከጥላቻ አራማጆች ጋር በማበር እራሳችንን ወደ ጭቃ እና የሚያጣብቅ ቆሻሻ ውስጥ አንጣል፡፡ እንዲህ የሚሉትን የጆርጅ በርናርድ ሻውን ምክሮችን በፍጹም መርሳት የለብንም፣ “ከብዙ ጊዜ በፊት ከአሳማ ጋር ማጥ ዉስጥ ላለመታገል ትምህርት አግኝቻለሁ፣ ለመታገል ከሞከርክ ቆሻሻ ትሆናለህ፣ አሳማው ግን ማጡን የነብሱን ያህል ይወደዋል፡፡“ ጥላቻን ሙያ አርገው ከሚኖሩ ሰዎች ጋር የጥላቻ ቃላትን መለዋወጥ ከአሳማ ጋር በጭቃ ማጥ ውስጥ የነጻ ትግል ውድድርን እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
ጥላቻን ወደ ፍቅር መለወጥ......
~ ይቀጥላል ~
ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም
❣ እናመሠግናለን ❣