የፓስታ ፌስቲቫል በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል
በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚካሄድ የሚጠበቀው የፓስታ ፌስቲቫል፤ የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡30 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ይከናወናል፡፡
በካልቸር ክለብ በሚዘጋጀው የጣልያን ምግብ ፌስቲቫል ላይ ከ5ሺ እስከ 7ሺ እንግዶች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡
በፌስቲቫሉ ላይ ከ23 በላይ የፓስታ ምግብ ሻጮች የተለያዩ ዓይነት የፓስታ ምግቦች፣ ሱጎዎችና ጣፋጮች እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡
የመግቢያው ዋጋ 250 ብር ሲሆን፤ትኬቶችን በቴሌብር መግዛት ወይም የእለቱ ዕለት በመግቢያው በር ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
በዚህ ፌስቲቫል ላይ ከግሩም የፓስታ ምግቦች ባሻገር፣ ሙዚቃና ከምግብ ማብሰል ጋር የተያያዙ አዝናኝ ትርኢቶች ይኖራሉ ተብሏል፡፡