አሁን ከቅርብ ሰዓታት በፊት ሱቅ የምፈልገውን እቃ ሳጣ ባለኝ መንገድ ትይዩ ወደላይ ፍለጋ ወጣሁኝ። ነገር ግን በመንገዴ ላይ ቆሜ ያየውት የምር! የምሬን ነው ጥልቅ ሀዘን የጣለብኝ። የሆኑ ሽማግሌ ናቸው ጥግ ከአረቄ ቤት አጠገብ አንድ መዳበሪያ አንጥፈው በላዩ ሽንኩርት አስቀምጠው እየሸጡ ሳለ አራት ደንቦች መጥተው ማዋከብ ያዙ። ሁለቱ ደንቦች ቆመዋል ሁለቱ ደግሞ ሽማግሌውን ያጨናንቋቸኋል። "ምንድነው ማነው የፈቀደልህ" እያለ አንደኛው ደንብ በዱላው ሽንኩርቱን ይንዳል። ሰውዬው ደንግጠዋል እጅግ በጣም ፈርተኋል። እየንተባተቡ ቃል እያማጡ ሳግ እያነቃቸው "እሷ ነች ፈቅዳልኝ እኮ ነው" ብለው የአረቄ ቤት ሴቷን ያመላክታሉ!። "ዝም ብለ መጥተህ መንገድ ላይ ትዘረጋለህ!" ብሎ ሌላኛው መዳበሪያውን ሲጎትተው ሽንኩርቱ መንገድ ላይ ተበተነ። እኚህ ሰውዬ በመደብ አድርገው ያስቀመጡት ሽንኩርት ቢሸጥ ከሦስት መቶ ብር ቢያንስ እንጂ አያልፍም። ልክ ትልቅ ንግድ በማንቀሳቀስ ወንጀል እየሰሩ እስከሚመስል ድረስ አበሻቅጠውና አሯቅተው ላኳቸው። የተበተነ ሽንኩርታቸውን እያዩ ሊሄዱ አሉና ደግሞ እንደመመለስ ግራ ገብቷቸው ቆመው አየዋቸው።
ደንቦችሁ ሽንኩሩቱን በትነው እዛው የተውት ቢወስዱት እንደማያዋጣቸው ስለተረዱ ነው። ብዙ ደንብ ተብዬዎች አይቻለሁ ቲማቲም፣ ሙዝ፣ ብርቱካን የሚሸጡ ላብ አደሮችን እስከነ እቃዎቻቸው በመውረስ እርስ በእርስ ተጠራርተው ከመሰሎቻቸው ጋር ይበሉታል የተረፈውን ይጡሉታል አብዛኛውን ጊዜ ግን ህጋዊ ሻጭ ለሚሉት በእጅ አዙር ይሸጡታል። ግብር የሚከፍለው ነጋዴም ያመጡትን ምርት ሳያንገራግር የመቀበል ግዴታ ውስጥ ይገባል። ብዙ የንግድ ቦታዎች "በህጋዊ አይደለም" ስም እስከነ እቃቸው ታሽገኋል። ይህ ዘረፋ ቁጥራቸው የበዛ ደንብና ፖሊሶች አበልጽጓቸዋል: ኑሮአቸውን አሸወይና አደርጎላቸዋል። የሚያሽጉት ቤቱን አይደለም ሊሸጥ የተዘጋጀው የታሸጉ materialsን ጭምሮ ነው። ስልክ ቤት ከሆነ በተን ስልካቸውን ለውጠው ሌላ ይይዛሉ ቀሪውን እንደለመደባቸው ይፖሹታል። ሌሎች የንግድ ማዕከላት ደግሞ ከማሸጋቸው በፊት የቤት እቃቸዎቻቸውን ለመለወጥ ይጠቀሙበታል።
ኤሌክትኖሪስ መሸጫ፣ ሱቃቸው፣ ቡቲካቸው ወዘተ የተዘጋባቸው ሰዎችን በቃን ብለው እንዲሁ አይተዋቸውም። ለልማት በማለት የሚኖሩበት ድረስ ይመጣሉ፤ ቤታቸውን ያፈርሳሉ ከሞቀ ኑሯቸው አፈናቅለው ጎዳና አዳሪ ያደርጓቸዋል። ለተራበ እጅ ደራሽ የሆኑ፤ ጠንካራ ሰራተኛና ክብር ያላቸው ባለፀጋ የነበሩ ስንት አባወራዎች መንገድ ወድቀው ፍርፋሪ ሲለምኑ በሰፈሬ በዘመኔም ተመልክቻለሁ!።
ሰዎች ለዓመታት ለፍተው ያካበቱን ሀብት በአንድ ቀን አመድ ማድረግ ጀብደይነት አይጠይቅም፤ አዕምሮን አለመጠቀም ብቻ በቂ ነው!!። ሙስሊሞች የሚሉት አንድ አባባል ሁሌም ቀልቤን ይወስደዋል "የሰው ሀቅ መመኘትም ሆነ መውሰድ በአላህ ዘንድ ያስጠይቃል እንደሱ ያለህም ፀያፍ የለም!" የራስ ያልሆነን ነገር ከሰው በመንጠቅ ተዘርፎ ተበልቶ ተፈስቶ እና ታርቶ ዝም ያለህ ሰላማዊ ኑሮ መኖር አይቻልም። ህሊናን በመጠጥና አሺሽ ጸጥ ማስባል ቢቻልም ግፍ ዞሮ ይመጣል። ፈርኦን የራሔል ልጆች ገድሎ ተስፋ የሌለው ሀዘን እንዳከናነባት፤ እርሷም እንባዋን በእጇ ጠርጋ ወደሰማይ እንዳፈናጠረቻቸው፤ ፈራጅ የሆነው ፈጣሪዋም ለበዳዮቿ የእግር እሳት እንደሆነው እንዲሀ ጠቢቡ እንዳለሁ ይዘግይ እንጂ `` ለሁሉም ጊዜ አለው! ``
© ሞገስ ዘአምድ GURU
JOIN US
@philosophyethContact us
@FREDOBASNJOIN OUR BOOK CHANNEL
@bookshelfeth1