⭕️መልዕክት አለኝ⭕️
ተፈላጊነት
ዶ/ር ኢዮብ
አንድ ሁለት ልጆች የነበሩት ገበሬ ነበረ፡፡ ሁለቱ ልጆቹ በእርሻ ስራው አይለዩትም ነበር፡፡ አባት ለታናሹ ልጁ የበለጠ ሃላፊነት ስለሚሰጠውና ስለሚያምነው ሁል ጊዜ ታላቅየው ጥያቄ ይፈጥርበት ነበር፡፡ አንድ ቀን አባት አምስት መቶ ብር በእጁ ላይ እንዳለውና፣ አምስት በጎችን እጁ ላይ ባለው የገንዘብ መጠን ቢያገኝ የመግዛት እቅድ እንዳለው ለታላቅ ልጁ እየነገረው ሳለ፣ ታላቅ ልጅ ይንን አጋጣሚ በመጠቀም ለምን ከእርሱ ይልቅ ለታናሹ የበለጠ ሃላፊነትን እንደሚሰጠው ጠየቀው፡፡ ይህንን ሲወያዩ ታናሽ ልጅ በዚያ አልነበረም፡፡ አባትም ቀጥተኛ መልስ ቢሰጠው ይገነዘበዋል ብሎ ስላላሰበ በብልሃት ሊያስተምረው ፈለገ፡፡
አባት ለታላቅ ልጁ፣ “እሰቲ እነዚያ ከብት የሚያረቡት ሰዎች ቤት ሂድና በግ ይሸጡ እንደሆነ አጣርተህ ተመለስ፣ ከዚያም ጥያቄህን እመልስልሃለሁ” አለው፡፡ ታላቅ ልጅ ሄዶ ተመለሰና፣ “አዎን የሚሸጡ በጎች አሏቸው” አለ፡፡ አባትም፣ “ሂድና ዋጋቸው ስንት እንደሆነ ጠይቅ” አለው፡፡ ልጅም ሄዶ መጣና፣ “ባለ 100 ብር በጎች አላቸው” አለው፡፡ አባት እንደገና፣ “ሂድና ነገውኑ በጎቹን ብንገዛቸው እኛ ድረስ ሊያመጡልን እንደሚችሉ ጠይቅ” አለው፡፡ ልጅም ሄዶ መጣና፣ “አዎን ይችላሉ” አለው፡፡ አባትም ታናሽ ወንድምህን ጥራው እስቲ አለው፡፡
ታናሽ ልጅ ሲመጣ አባት፣ “እስቲ እነዚያ ከብት የሚያረቡት ሰዎች ቤት ሂድና በግ ይሸጡ እንደሆነ አጣርተህ ተመለስ” አለው፡፡ ታናሽየው ሄዶ ተመለሰና፣ “ባለ 100 ብር፣ ጎችና እና ባለ 150 ብር በጎች አሏቸው፡፡ ነገውኑ ብንፈልግ ሊያመጡልን እንደሚችሉ ጠይቄ ተስማምተዋል” ብሎ ለአባቱ ነገረው፡፡ በመጨመርም፣ “ስለዚህ፣ የተለየ ሃሳብ ኖሮን ካልነገርኳቸው በስተቀር አምስት በጎችን በ100 ብር ሂሳብ ነገውኑ እንዲያመጡልን ተስማምቼአለሁ” አለው፡፡ አባት ወደታላቅ ልጁ ዘወር ብሎ ሲመለከት፣ ታላቅ ልጁ የራሱንና የታናሽ ወንድሙን መልስ በማሰነጻጸር ላይ እንዳለ ያስታውቅ ነበር፡፡
“አየህ ልጄ፣ አንተንና ታናሽ ወንድምህን የጠየኳችሁ አንድ አይነት ጥያቄ ነው፡፡ ያመጣችሁልኝ መረጃ ግን በጣም ይለያያል፡፡ አንተ ያችኑው የተጠየከውን ጥያቄ ነው ይዘህ የመጣኸው፡፡ ሌላ መረጃ ስፈልግ እንደገና ደጋግሜ መላክ ነበረብኝ፡፡ እርሱ ግን እኔ የፈለኩትን ፍላጎቴን በሚገባ በመረዳት የቻለውን ያህል መረጃ ይዞልኝ ነው የመጣው፣ ከተጠየቀውም በላይ ስራ ሰርቶ ነው የመጣው፡፡ ሁል ጊዜ ከአንተ ይልቅ ለእርሱ ሃላፊነትን የምሰጠው ለዚህ ነው፡፡” በማለት ቀድሞ ለጠየቀው ጥያቄ መልስን ሰጠው፡፡ ለነገሩ፣ ታላቅ ልጅ ገና መልሱ ሳይብራራ ገብቶት ነበር፡፡
የተባሉትንና የሚጠበቅባቸውን ብቻ አድርገው እጆቻቸውን የሚሰበስቡ ሰዎች ተግባርን በማከናወንና የተጠበቀባቸውን ነገር በማድረግ አንጻር ትክክለኛ ነገር አድርገዋል፡፡ በእድገት ልቆ ከመገኘት አንጻር ሲታይ ግን ባሉበት የሚረግጡ አይነት ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ አይነቱ ምርጫ ሰዎች ሊያከናውኑ ከሚችሉት አቅማቸው በታች እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች በእድገትና በተቀባይነት አልፈዋቸው ሲሆዱ እያዩ “ለምን?” እያሉ ከመጠየቅ ያለፈ እድገት አይኖራቸውም፡፡ “ለምን ለሌሎች ያደላሉ? … ለምን ሰውን ይመርጣሉ? … ብዙም የሚፈልገኝ ሰው የሌለው ለምንድን ነው? … ” መልስ ያጣው ጥያቄያቸው ብዙ ነው፡፡
የተፈላጊነት እውነታዎች …
• ከተፈላጊነት ውጪ ምንም አይነት እድገት እንደማታገኝ እወቅ፡፡
• ተፈላጊነትህን ለመጨመር የግድ ውሸት፣ የሌላውን ሰው ስም ማጥፋት፣ ሸንጋይነትና የመሳሰሉትን መንገዶች መጠቀም የለብህም፡፡
• በትጋትህና በታማኝነትህ የሰዎችን ልብ ባሳረፍክ ቁጥር ተፈላጊነትህ እየጨመረ ይሄዳል፡፡
• ብዙ እውቀትና ችሎታ ኖሮት የልብን ከማያደርስ ሰው ይልቅ፣ ብቃቱ አናሳ ሆነ ትጉ ሰው የበለጠ ተፈላጊነት አለው፡፡
• ከሚከፈልህ በላይና ከሚጠበቅብህ በላይ በትጋት ስትሰራ ተፈላጊነትን ታተርፋለህ፡፡
• ክፍያን በገንዘብ ብቻ አትጠብቅ፡፡ ከሚጠበቅብህ በላይ ስትሰራ የግድ ለዚያ የሚመጥን ገንዘብ እጅ በእጅ ላይከፈልህ ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ክፍያህ በመልካም ስምና ምስክርነት፣ በተሻለ የስራ እርከን እድገትና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ሊገለጥ ይችላል፡፡
• በመጨረሻ፣ ታማኝነትህንና ትጋትህን ለእኩይ አላማቸውና አንተን ለመበዝበዝ ብቻ ለመጠቀም ከሚፈልጉ ሰዎች ተጠንቀቅ፡፡
@pilasethiopia