✍🏾 Daniel Kifle 😊😊
ገና በወጣትነት ዕድሜዬ፣ “ኹሉ ከንቱ ነው” ለማለት የምደርስ አይመስለኝም ነበር።
1.
በሕይወቴ የቀረቡልኝን አማራጮች ብዛት ተመልክቼ፣ ተራ በተራ ለማጣጣም መሯሯጥ የጀመርኩት ከትንሽነቴ ነው። ሯጭ፣ ኳስ ተጫዋች፣ አስተማሪ፣ ዶክተር፣ ኢንጂነር፣ ፊልሞች ላይ እንዳየኋቸው አክተሮች የመኾን ፍላጎት ነበረኝ።
ኹሉን መኾን ስለማልችል፣ አንዱን ብቻ ኾንኩኝ።
2.
ከማንበብ ዕውቀት ስለሚገኝ፥ ሃይማኖት፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ቤተሰብ እና ሌሎች ጉዳዮች የተዳሰሱባቸውን ሕትመቶች ለማገላበጥ ሞከርኩ።
እያንዳንዱ ርእስ ላይ ሊቅ እንደማይኮ፞ን ሳስተውል፣ የሚያስፈልገኝን ጥቂት ነገር ወስጄ ቀሪውን ለሌሎች ተውኩኝ። ስፐርጅን ”ብዙ መጻሕፍትን ጎብኙ፤ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ኑሩ” እንዳለው ነው።
3.
ዓለምን ዞሬ የመጎብኘት ፍላጎት ነበረኝ።
የምድርን ገጽ ባካልል እንኳ እንደማልረካ ሲገባኝ፣ አምሮቴ በጥቂት ሐገራት ጉብኝት ወጣልኝ። “ዐይን ከማየት አይጠግብም” እንደተባለው ነው። በዙሪያዬ ያሉ፞ ሰዎች ዓለሜ ስለኾኑ እነርሱን እዞራለኹ።
4.
በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች የሚመገቡትን የመብላት እና የሚጠጡትን የመጎ፞ንጨት መሻት ነበረኝ።
በምድር ከሚርመሰመሱ፣ በሰማይ ከሚበሩ፞ት እና ባሕር ውስጥ ከሚኖሩት ጥቂቶቹን ስቀምስ አዲስ ነገር እንደሌለ ተገንዝቤአለሁ።
5.
እግዚአብሔርን የሚፈሩ ብዙ ሴቶች ቢኖሩም፣ አንዷን ብቻ እንደማገባ ሳውቅ ደስ አለኝ። አስተዋይ ሴት ባገኘኹ ቁጥር፣ “ሚስቴ በኾነች” ብዬ አልመኝም። “ድስት ግጣሙን ያገኛል” እንደሚባለው ነው።
6.
ሰዎችን የምፈልገው አብረን ቁም ነገር እንድንሠራ ነበር።
ከሰዎች የማገኘው ትርፍ፣ ሰዎች መኾናቸውን ሳስተውል ግን ከነርሱ ጋራ ማሳለፍ ቁም ነገሬ ኾነ። ያዳር ጸሎት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወዳጆቼ የዘውትር ናፍቆቴ ናቸው።
7.
የምታወስበትን ነገር መትከል እፈልግ ነበር።
ከሞትኩ በኋላ የምረ፞ሳ፞በትን ፍጥነት ሳስብ ግን ለስሜ የሚኾን መታሰቢያ የማቆም ምኞቴን ጣልኹት። ለታናናሾቼ መንገድ ማሳየት የምኖርለት ግብ ኾኖኛል።
የቀረቡልኝን ብዙ አማራጮች ለማግበስበስ ከመሯሯጥ አርፌ፣ እንደ ሰባኪው “ኹሉ ከንቱ ነው” ለማለት በቅቻለሁ።
ትኩረቴ ለሙታን ትንሣኤ የማደርገው ዝግጅት ላይ ነው።
Disclaimer:
(በሕይወት ተስፋ የቆረጠ ሰው የጻፈው፣ የስንብት ደብዳቤ አይደለም፤ ለመኖር የሚጓጓ፣ ነገን ለማየት የሚናፍቅ ተስፈኛ የከተበው ነው።)
የውስጥ የሰላም ምንጭ ኢየሱስ😍
@revealjesus