✨ማብራሪያ:- ውድ የራይድ ቤተሰብ- እንደሚያውቁት ላለፉት 3 ወራት ስለራይድ አሽከርካሪ KPI ወይም የአገልግሎት አሰጣጥ መለኪያ ስናሳውቅ ቆይተናል:: አሁን ደግሞ ይህንን ለማስፈፀም ለ12 ቀናት ስለ Driver Level በበቂ ሁኔታ በSMS, በቴሌግራም, በPush Notification እንዲሁም በRIDE Inapp Message ስናስረዳ ቆይተናል:: በቅድሚያ ስለዚህ ፊቸር ጥቅም ከመጥቀሳችን በፊት ስለምንነቱ ጥቂት እንበላችሁ:: Driver Level የአሽከርካሪዎችን አገልግሎት ጥራት መለኪያ ፊቸር ሲሆን- የስራ ስርጭታችንን ጥራት ለማሻሻል አይነተኛ አሰራር ነው:: ታዲያ ይህ መለኪያ ላይ ተፅዕኖ ከሚያመጡ ተግባራት ውስጥ የተወሰኑትን ለመጥቀስ -1. የአሽከርካሪ ኮኮብ መለኪያ -2. የሚሰሩት የስራ መጠን -3. ኦንላይን የቆዩባቸው ቀናት እንዲሁም 4.cancelation ቁጥር ናቸው:: እነዚህ መለኪያዎች የተተገበሩት ድርጅታችን የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ ሲሆን በተጨማሪም ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እንዲያገኝ ይረዳዋል:: እርስዎም ከድርጅታችን ጋር ሲሰሩ ዝቅተኛው ከሚጠበቅብዎ ስነምግባር በጥቂቱ:: 1. የራይድ አፕ Online እንዳለ በአየር ላይ የሚለቀቁ ስራዎችን አለማባከን እና የደንበኞቻችንን እንግልት አለመጨመር:: 2. ስልክን በአግባቡ ለራይድ ስራ ብቻ በመጠቀም ሲስተማችን ላይ ከፍተኛ ጫና አለመፍጠር እና አገልግሎት ስርጭታችንን አለማዛባት:: 3. ከድርጅታችን ውጭ የሌላን ተመሳሳይ አገልግሎት ስቲከር ለራይድ ደንበኞች አለማስተዋወቅ እና ድርጅታችን ማግኘት የነበረበትን ጥቅም አለማሳጣት ናቸው:: ስለዚህ- ድርጅታችን በሚገባ ተደራሽነቱን እንዲያሰፋ አሰራራችንን ተቀብለው አብረውን እንዲዘልቁ በአክብሮት እንጠይቃለን:: መልካም ምሽት