#ምክር_ለወጣቶች_
( Day )السلام عليكم ورحمت الله وبركاته
بسم الله الرحمان الرحيم
🌟 وذكر فاءن ذكرا تنفع المؤمنين، وما خلقت الجن والاءنس الا ليعبدون
يا اختي المسلمة يا من اللتزمت كتاب الله تلاوة، وتدبرا ،وعملا ، يا من تريدين الخلود في الجنة اليك هذه الكامات التي تخرج من قلب اختك وترد لك السعادة في الدنيا والفوز في الأخيرة
አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ የአላህን መፅሀፍ በማንበብ፣ በማስተንትን፣እንዲሁም በመስራት የተቆራኘሽው እህቴ፣ በጀነት መዘውተርን የምትፈልጊዋ እህቴ ሆይ ላንቺ በዱንያም በአኼራም ደስታን እና እድለኝነትን ከምትመኝልሽ እህትሽ ልብ ውስጥ የሚወጡትን ንግግሮች እንኪ,
ይህች ፅሁፍ የምታተኩረው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ
Day ለምታከብሩ ተማሪዎች ሁሉ በተለይ ለሙስሊም እህቶች እንድታስተውሉ ለማስታወስ ነው
እሺ ቢስሚላህ
1, የተፈጠርንበት አላማ አላህን በትክክል ለመገዛት እንድሆነ እና በተሰጠን ግዜ እንደምንጠየቅ ለምን ረሳን በአላህ ?????????
2, እዛ
Day የሚከበርበት ቦታ የሚሰሩትን ሀራም ስራዎች ለምሳሌ ሰላትን ማዘግየት፣ ኢኽቲላጥ ፣ ዘፈኖች ....... ሌሎችም የእስልምና ትዕዛዝን የሚቃረኑ ስራዎች እንደሚሰሩ እያወቅን የምንሄድበትስ ምክንያት ምንድን ነው???
3, ይህንን አያህ ማስተንተን ለምን አቃተን?
"ياءيها الذين آمنو اتقو الله حق تقاته ولاتموتن الا وانتم مسلمون"
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ትክክለኛ የሆነ መፍራትን ፍሩት ሙስሊም ሆናችሁ ቢሆን እንጂ እንዳትሞቱ"
እህቶች በ ደንብ እናስተውል ሴት ልጅ ያለ ሀያእ ምንም አይደለችም። የሰሀቢያቶችንም ታሪክ ብናይ በሀያእ ፣ ትልቅ በሆነ ኢልም ነው የምናቃቸው ፉጢማ(ረ.ዐ)እኮ በሀያቷ 3ግዜ ነው ከቤቷ የወጣችው ይህም በኒካህ፣ ለሀጅ እና ስትሞት ነበር። አጂብ እኛ ግን ....... ሌላው ቀርቶ Day ለማክበር የሚሄድ ራሱ በጣም በዝቷል መልሺ እስኪ እህቴ ይሄ ስራ አላህን ከመፍራት ነውን ???
አንተስ ብትሆን ወንድሜ ቁርአንን ሀፍዘህ ፣በህግጋቱ ሰርተህ ፣ሙስሊም ኡማውን መጥቀምን ፣ትልቁ ግብህን ለምን ረሳህ ???
ሁላችንም በጊዜያችን እንጠየቃለን ። "ስንሰራው በነበረው ስራ እንሞታለን፣ በሞትንበት ነገርም እንቀሰቀሳለን ። "ሒሳብም ምርመራም አለብን እኮ አህባቢ
ለግራውንድ ማይነሷ ቤታችን ለቀብራችን ብርሃን ካሁኑ መያዝ እንጀምር።
ከመቼውም ግዜ በላይ በዒልም እንጠንክር ምክንያቱም 👇
انما يخش الله من عباده العلماء
ስለተባልን፣
አላህን ለመፍራት ትዕዛዝን እና ክልከላን ለማወቅ ዒልም ግዴታ ነውና በኢልም እንጠንክር አደራ
ከአላህ ራህመት ተስፋ አድርገን ወደሱም ተዋድቀን እንለምነው እሱ ምህረተ ሰፊ ነውና ተውባችንን ይቀበለናል ኢንሻአላህ ሱብሀን ወጣትነት አያታለን ወላሂ ወጣትነትም ያልፋል ወጣትነታችን ሳያልፍ እንጠቀምበት። ሁሌም ሞት እንደማይረሳን እናስታውስ ወደ ተውባም እንቻኮል አላህ ያግዘን ያረብ ንግግርን ሰምተው ከሚሰሩበት ኢላሂ ያድርገን እውነትን ካረጋገጥኩ ከአላህ ነው ከተሳሳትኩም ከነፍሲያዬ እና ከሸይጧን ነው አላህ ኸይሩን ይግጠመን
والله اعلم
✍ የአንሷር ልጅ