Репост из: ስሜትን በግጥም
...ትሂድ ግዴለም። ሳትመጣ መሄድን ማን እንዳስተማራት እንጃ። እንደ ምክንያትነት ያቀረበችው ለኔ የሚሆን በቂ ጊዜ የለህም የሚል ነው። አጠገቤ ያለች እየመሰላት ሰማይ ምድርን የራቀቻትን ያህል እንደራቀችኝ አልተረዳችም ይሁን አልያም እውነቱን መቀበል ያልፈለገች አላውቅም። ሀቁን ለመናገር እኔም ሰማይ ምድርን ትራቃት ወይም ምድር ሰማይን ትራቃት የማውቀው ነገር የለም፤ ጉዳዬም አይደለም። ብቻ ይሄን ተረድቻለው ሳይመጡ መሄድ መቻልን ሳያገኙ ማጣት እንዳለ....ትሂድ ማጣት ለኔ ብርቄ አይደለ፤ እንኳንስ እሷን እራሴን አጥቻለው...ትሂድ ማጣት ከመኖር እኩል የተሰጠኝ ገፀ በረከቴ ነው። እየሸኙ መሳቅ እየሳቁ ማልቀስ እያነቡ እስክስታ እጣ ፈንታዬ ከሆነ እንደሰነበተ አልገባትም መሰለኝ...ወዶ ለመጠላት አምኖ ለመከዳት ደግሞ እኔን ማን ብሎኝ ።....በእርግጥ የመጣች መሰላት....ልቧ ተሰብሮ ነበር በማን እንደሆን እንጃ፤ ብቻ በሆነ ሰው....ህመሟን ያሽርላት ብዬ ከልቤ ዘግኜ ልቧን ሞላሁላት....ትንሽ ትንሽ መሳቅ ጀመረች። የኔ ነፍስ ሻማ ነች ሌላን ታበራለች ለራሷ ታልቃለች በፅልመት ትዋጣለች። ....ዛሬ መጉደሌን አይታ ሳትመጣ ልሄድ ነው ትላለች...የኔ መጉደል የሷ ሙላት እንደሆነ አልገባትማ። ትሂዳ ትሂድ እንኳን እሷ እኔም ሄጃለው የት እንደሆን ባላውቅም። ሳያገኙ ማጣት እየሳቁ ማንባት ማንባትን መሰወር ህመምንም መቅበር ደህንነት መዘከር እጣፈንታዬ ነው የህይወቴ ገፀ በረከቴ...በማግኘት መደሰትማ ከእትብቴ ጋር አብሮ ተቀብሯል።....ትሂዳ ትሂድ።
✍ ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ
✍ ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ