✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯
የጌታችን ልደት በአበው
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “የቅድስና ኹሉ ሰጭ ወደዚህ ዓለም የገባው በንጹሑ ልደት በኩል ነው። የቀደመው አዳም ከድንግል መሬት ተገኘ፤ ከእርሱም ያለ ሴት ዕርዳታ ሴት ተገኘች። ልክ አዳም ያለ ሴት ሴትን እንዳስገኘ፤ ድንግልም ያለ ወንድ በዚህ ዕለት ወንድን አስገኘች። ስለዚህ ሴቶች ለወንዶች ዕዳቸውን ከፈሉ፤ አዳም ብቻውን ሔዋንን እንዳስገኘ ድንግልም ያለ ወንድ ወንድን አስገኝታለችና። አዳም ያለ ሴት ሴትን ስላስገኘ ሊኩራራ አይገባም፤ ድንግልም ያለ ወንድ ወንድን አስገኝታለችና። በምሥጢሩ ተመሳሳይነት የተፈጥሮው ተመሳሳይነት ተረጋገጠ። ከአዳም ጎን አንዲት አጥንት ወሰደ ነገር ግን አዳም ጉድለት አልተገኘበትም÷ በተመሳሳይ ከድንግል ወንድ ልጅ ተወለደ ድንግልናዋ ግን አልተለወጠም” እያለ በሚያስደንቅ መንገድ የቅድስት ድንግል ማርያም ድንግልናን በአዳም ኅቱመ ጎን በኩል ያሳየናል”።
ይህ የልደት ቀን የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብር ከማሳየቱም አልፎ ሴቶችን እንዴት እንደካሰቻቸው ፍንትው አድርጎ ያመለክተናል። የጌታችን የልደት ዕለት ማለት የሴቶች ክብር የተገለጠበትና ወንድና ሴት እኩል መኾናቸው የተረጋገጠበት ዕለት ነው። “ሴቶች ሆይ የሴትነትን ክብር ያስመለሰችላችሁን ቅድስት ድንግል ማርያምን ትረሷት ይኾንን?”። ድንግል በድንግልና ወለደች ሲባል ሰምተን እንዳንደናገጥና ወደ ጥርጣሬ ባሕር ውስጥ እንዳንገባ አስቀድሞ አዳም ብቻውን ሔዋንን ሲያስገኝ ያለውን ነገር በመጽሐፍ አጻፈልን። አዳም ሔዋንን ብቻውን ከጎኑ እንዳስገኘ አምኖ የተቀበለ ሰው እንዴት ድንግል ማርያም በድንግልና ወለደች ሲባል ለማመን ይከብደው ይኾን? በጣም የሚያስገርመው ሔዋን ከአዳም ጎን ብትወጣም ለአዳም ውድቀትም ምክንያት ኾና ነበር፤ ድንግል የወለደችው ግን ዓለምን በሙሉ የሚያድን አምላክ ነው።