╔═══════════════╗
ጄኔራል አናቶሊ አንደርቡክ
╚═══════════════╝
ኢስላምና ሙስሊሞችን በእጅጉ ይጠላ ነበርና ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ያለውን አቅም ሁሉ አሟጦ በእጅጉ ተፋልሟል። ሙስሊሞችን ሲያይ በንዴት በግኖ ዓይኑ ይቀላል። ሙጃሂዶችን እያሳደደና ዋሻቸው ድረስ እየዘለቀ ብዙ ኳትኗል። ኃይማኖት የሌለው ከንቱና የባከነ ሰው ነበር። ሙስሊሞችን በመግደል እና በማጥፋት ይፀድቅ ይመስል አምርሮ ተዋግቷል። ያደገው ጫካ ነው። የሰብአዊ እሴቶችን ትርጉም አያውቃቸውም።
የተወለደው በአዘርባጃን ከተማ በባኮ አውራጃ ነው። ቤተሰቦቹ በማርክስ እና በሌኒን አምላክ የለሽ ሀሳቦች ያምኑ ነበር። ይህም በአስተሳሰቡ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖን በማሳደር እስልምናን እና ሙስሊሞችን እንዲጠላ አደረገው።
የሶቪዬት ህብረትን ጦር ተቀላቅሎ የጄኔራልነት ማዕረግን ተቆናጠጠ። ጊዜው የሶቪዬት ኮሚኒስት ኃይሎች የሙስሊሞችን ሀገር አፍጋኒስታንን የወረሩበት ወቅት ነበር። የጦርነት ነጋሪቱ ከተጎሰመበት ዕለት ጀምሮ ከ1979 እስከ 1989 መጨረሻ ድረስ እየተዋጋና እያዋጋ እየገደለና እያሳሰረ አስር አመታትን አሳልፏል።
ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የሆነ እጅግ ዘግናኝ በሆነ መንገድ ሙስሊሞችን በመግደል እና በማሰቃየት የበዙ ሙጃሂዶች በእጁ ሸሂድ ሆነዋል።
የሩሲያ ጦር በጥንካሬው እና በጦር መሣሪያ የበላይነትን ቢቀዳጅም ጥቂት ቁጥር ያላቸው ሙስሊም ሙጃሂዶች በቀላልና ባረጁ መሣሪያዎች ፊት ለፊት መጋጠማቸው የአናቶሊን ትኩረት ሳበ።
እነዚህ ሰዎች ቁጥራቸው አናሳ፣ መሳርያቸው ያረጀ ሆኖ ሳለ ይህን ያህል ብዛት ባለውና በዘመናዊ መሳርያ የደረጀ ኃይል ፊት እንዴት ይፀናሉ?! በጥንካሬ፣ በድፍረት እና በጀግንነት እንዴት ይዋጋሉ?! በማለት ራሱን ይጠይቅ ጀመር። በቆራጥነት ለመፋለም የሚያነሳሳቸው የተደበቀ ኃይል እንዳለም በአዕምሮው አሰላሰለ። እስልምና በልብ ውስጥ ተዘርቶ በእምነት ፅናት አብቦ በስነምግባር ላይ የሚፈካ ውስጣዊ ኃይል ነው።
ታዲያ ከቀናቶች በአንደኛው የአላህ ቀን ከጠንካራው የጦርነት መስክ ውሎ በኋላ ጄኔራል አናቶሊ እየተዟዟረ የሩስያውያንን አስከሬን ተመለከተ። አካላቸው ተነፋፍቶ ሰውነታቸው አፍንጫን የሚሰነፍጥና የሚሸት ሆነው አገኛቸው። በተቃራኒው ወደ ሙስሊሞች ጀናዛ አይኑን አዞረ ሳይበላሽ እና ጥርሳቸው የተፈለቀቀ ጥጥ መስሎ ፈገግታን ከፊታቸው እየረጩ ተመለከተ።
ይህ ቅጽበት በሕይወቱ ውስጥ ትልቅ የለውጥ ጉዞን እንዲጀምር አደረገው። ያየውን ምስጢር ይመረምር ጀመር። ስለ ሃይማኖቶች ማንበብ ጀመረ። በተለይም ስለእስልምና በጥልቅ ለማወቅ ጓጓ።
ታሪኩን በአንደበቱ እንዲህ ያወጋናል:-
"ግቤ የሙስሊም ኃይሎችን ማቃጠልና ማጥፋት ነበር ... እስረኞቻቸውን ጭካኔ በተሞላበት መልኩ አሰቃያቸዋለሁ ... የቻልኩትንም እገላለሁ። ዘመናዊ መሳሪያን ታጥቀን ተዋጋናቸው። አዳዲስ መሳርያዎችን ሳይቀር ሞከርንባቸው። ከአየርም ከመሬትም አጠቃናቸው። እጅግ ይገርማሉ እውነትም ከፈጣሪ የሚታገዙ የአላህ ወታደሮች ነበሩ። ሚዳቆን እንኳ ማደን የማይችል ጠመንጃዎችን ብቻ ነበር የታጠቁት። ግና ወታደሮቼ ከፊታቸው እየሸሹ ሲፈረጥጡ በዓይኔ ተመልክቻለሁ። ለዚህ አለም ያላቸው ንቄትና ከጌታቸው ጋር የነበራቸው ጠንካራ ግንኙነት እምነቴ ላይ ጥርጣሬን ፈጠረ። ሩሲያኛ የሚናገሩ እስረኛ ሙጃሂዶችን እንዲያመጡልኝ ወታደሮቼን አዘዝኳቸው። እኔ ዘንድም አመጧቸው። በሩሲያኛ አናገርኳቸው። እነሱም እስልምናን እቀበል ዘንድ ጋበዙኝ። ስለ እስልምና ያለኝ አመለካከት ቀስ በቀስ ተለወጠ። በጥልቅ ማንበብ ጀመርኩ። ጓደኞቼ የተቃወሙኝን ውሳኔ እስክወስን ድረስ ስለ ሁሉም ሃይማኖቶች ማንበቤን ቀጠልኩ። በመጨረሻም እስልምናን በይፋ ተቀበልኩ። በሐቅ መንገድ ላይ ለመጓዝም ወሰንኩ። አመራሮቼ ውሳኔዬን እንድቀይር ለማሳመን ያደረጉትን ሙከራ ተቋቁሜ ባለቤቴና ልጆቼን አሰለምኩ። አላህ ያለፈውን ወንጀሌን ይምረኝም ዘንድ ሰዎችን ወደ አላህ መንገድ ለመጣራት ጉዞ ጀመርኩ። በህይወት እስካለሁም በአንድ መስጂድ ሙአዚን ሆኜ ለመኖር ወሰንኩ"
ለእስልምና መስህብ ራሱን በመስጠት ከግትር ተዋጊነት ወደ ሙአዚንነት መለወጡ ሂዳያ በአላህ እጅ መሆኑን እናስታውስ ላመኑት ይጠቅማልና ማስታወስ። አላህ ተውበቱን ይቀበለው
═════════════════
ይህ የዩቱዩብ ፔጄ ነው ሰብስክራይብ አድርገው የጀግኖችን ታሪክ ይከታተሉ
👇👇
https://youtube.com/channel/UCPgxFIQ_qZ2XHM1di_y_xoA
ይህ ደግሞ የቴሌግራም አካውንቴ ነው
👇👇👇
http://t.me/sehkaliderashid
═════════════════
ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ
╔═══════════════╗
Like ☑ Comment ☑ Share ☑
ኢኽላስ - ታማኝነት - ትጋት - ስኬት