Репост из: Bahiru Teka
🔷 የእህታች መዲና ሞት አሳዛኝ የሚያደርገው ምንድነው ?
ክፍል አንድ
እህታችን መዲና ደምሴ ለሞቷ ሰበብ የሆነው የጡት ካንሰር እንደነበር እናውቃለን ። አላህ በሰው ልጆች ላይ የፃፈው ሞት ቅሮት የለውም ። ሳአቱን ጠብቆ ይመጣል ሰበብን ከሰበቡ ባለቤት ጋር እንዲገናኝ ያደረገው አላህ ለማንኛውም ሰው ሞት ሰበብ አድርጎለታል ። የእህታችንም ከዚህ የተለየ አልነበረም ።
ይሁን እንጂ ከሞት ሰበቦች ውስጥ አንዱ ህመም ነው ። የህመሙ አይነት በጣም ቢለያይም ሰዎች በተለያየ መልኩ ህመምተኛውን ከህመሙ እንዲድን ሰበብ ያደርሳሉ ። በሰበቡ እንዲድን አላህ የፈቀደው ይድናል ። አላህ በሰበቡ እንዲድን ያልፈቀደለትና ያ ህመም ለመሞቱ ሰበብ የሚሆነው በዛው ወደ አኼራ ይሄዳል ። ነገር ግን ሰበብ በማድረሱ ቤተሰብና ዘመድ ሰበብ አድርሰናል የአላህ ውሳኔ ነውና ምንም ማድረግ አንችልም ብሎ ይፅናናል ።
በጣም በሚገርም መልኩ ብዙ ቤተሰቦች ከቤተሰባቸው ሞት ይልቅ ሰበብ ባለማድረሳቸው ሁሌም ፀፀት ሆኖባቸው ይኖራሉ ።
ወደ እህታችን መዲና ስንመለስ በሽታዋ ካንሰር መሆኑ ከታወቀ በኋላ የሚቻለው ሁሉ ሰበብ ለማድረስ ሁሉም ተረባርቧል ። ቅስም የሚሰብረውና ውስጥን የሚያደማው ግን እህታችን የጡቷ ህመም ሲጀምራት ለመታየት ሐኪም ቤት ለመሄድ አቅም ማጣቷ ነው ።
እራሳቸውም ከህይወት ጋር ትግል ውስጥ ካሉት ወንድሞቿ አንዱን ጡቴን እያመመኝ ነው ሐኪም ቤት ለመታየት ትንሽ ሳንቲም ፈልግልኝ ብትለውም ወንድሟ ሊያገኝላት ባለመቻሉ ሳትታይ ትቀራለች ። የጡቷ ህመም ግን ስር እየሰደደ አቅሙን እያዳበረ ነበር ። አደጋው እያወቀችውና እየፈራችውም ግን ለማን ትንገር እህቶቿን ማስቸገር አልፈለገችም ከህመሟ ጋር ግብግብ ቀጥላ ቀናቶች ለሳምንታት ሳምንታት ለወራቶች ቦታ እየለቀቁ ህመሟ ከአቅሟ በላይ ሲሆን ለአንድ እህቷ ትናገራለች ። እህት ደንግጣና ፈርታ ወደ ሀኪም ቤት ይዛት ትሄዳለች ስትመረመር የፈራችው አልቀረም በጣም ዘገያችሁ ወደ ካንሰርነት ተቀይራል ተባሉ ። የዚህን ጊዜ ነበር ጉዳዩ ወደኛ የደረሰው እንደምታውቁት ብዙ እህትና ወንድሞች ርብርብ አድርገው የሚቻለው ሁሉ ህክምና ተደርጎላት ነበር ። መጀመሪያ ሐኪም ቤት ለመሄድ 500 ብር ያጣችው እህታችንን ህይወት ለመታደግ እስከ 800, 000 ወጥቷል ።
እህታችን መዲና አላህ በጀነት የምታርፍ ያድርጋት እንጂ ህይወቷ በፈተና የተሞላ ነበር ። ባለትዳርና የሶስት ልጆች እናት የነበረችው መዲና የትዳር አጓርዋ የሳንቲም ድህነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነገር ነበር ማለት ይቻላል ። ብዙ ወንድሞች የተለያየ ከሸክም እስከ ሊስትሮ ከዘበኝነት እስከ ፅዳት ሰራተኝነት አነስተኛ ስራ እየሰሩ ቤተሰባቸውን ያስተዳድራሉ ። ይህ የሀላፊነት መሰማት ውጤት ነው ሀላፊነት የማይሰማው የሆነ አካል ችግር ሲመጣ ጥሎ ይጠፋል ። የመዲናም ባለቤት ከእነዚህ አንዱ ነበር ። በካንሰር ተይዛ ከካንሰሩ በላይ የልጆቿ ረሃብ በሽታ ሆኖ የሚያሰቃያትን ባለቤቱን ለመርዳት ከመጣር ይልቅ ጥሎ መሸሽ ነበር የመረጠው ። እናቱ ኬሞ ስትጀምር የሰውነቷ ፀጉር ሲረግፍ ያየው የመጀመሪያ ልጇ የ9 ጠኛ ክፍል ትምህርቱን ትቶ የእናቱን ሸክም ለመቀነስና ለማሳከም ሲል ሰው ቤት ተቀጠረ ። ‼
ይሁን እንጂ ይህ ውሳኔ በእናቱ ላይ ሌላ ሸክምና ህመም የሚጨምር ነበር ። ልጇ ከእድሜው በላይ ጫና ውስጥ ገብቶ ትምህርቱን ማቋረጡ ሌላ ህመም ሆነባት ። ህመሟ በወንድሞችና እህቶች እርዳታ ህክምና ጀምራ በተለይ ከውጭ ሀገር ይምጣ የተባለው መርፌ ከጀመረች በኋላ ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ላይ የነበረ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ሁኔታው አስከፊ መሆን ጀመረ ። ሁለቱ ልጆቿ እድሜያቸው ገና ሲሆን ሶስተኛው አምስት አመቱ አካባቢ ነው ። እነርሱን እያየች ስታለቅሰ አጠገቧ እየተቀመጠ ጡትሽ ስለተቆረጠ ነው ወይ የምታለቅሺው አይዞሽ ይበቅላል ይላታል ። የእነዚህ ልጆቿ ሁኔታ ፊት ለፊቷ እያዘገመ እየመጣ ካለው ሞት የበለጠ እንደውጋት ቀስፎ እየያዛት በአካልና የውስጥ ህመም ውስጥ ሆነች ። ከቀናት በፊት ባለቤቴ ልትጠይቃት ሄዳ ሳለች በእንባዋ ትራሷ ርሶ አየች ምን ብላ ልታፅናናት እንደምትችል ግራ ገብቷት እያለ ትንሹ ልጇ እናቴ አትሙችብኝ ብሎ ያቅፋታል ። ከብዙ መረባበሽ በኋላ አላህዬ ያንተን ውሰኔ እቀበላለሁ ግን ለእነዚህ ልጄቼ ብኖር ደስ ይለኝ ነበር ብላ የበለጠ ተረብሻ ባለቤቴም የሚያፅናናት ሲያስፈልጋት ትታ ወጣች ።
https://t.me/bahruteka