ኤርትራ‼️
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒትር ኣይተ የማነ ገ/መስቀል እና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊው ኮለኔል ተስፋልልደት፣የኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች እንዲሁም የደህንነት ሃላፊዎች ከ ጥር 11/2017 ዓ.ም እስከ ጥር 13/2017 ዓ.ም ድረስ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከጋሽ ባርካ፣ ከሰሜናዊ እና ደቡባዊ ቀይ ባህር፣ ዓንሰባ እና ደቡባዊ ዞኖች የተውጣጡ የፀጥታ አስተዳደር እና የህግደፍ (ሻዕቢያ) ጽ/ቤት አባላት በአስመራ ከተማ በሚገኘው የማስታወቂ ሚኒስቴር አዳራሽ አስቸኳይ ሰብሰባ አካሂደው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈዋል።
በስብሰባው ፍጻሜ በተሰብሳቢዎች ከተወሰኑና ሳይሸራረፉ እንዲፈጸሙ መግባባት ላይ ከተደረሰባቸው መካከል፦
➊ ኢትዮጵያ ልትወረን ነው የሚል ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እንዲከፈትና ለዚህም ተባባሪ የሆኑ በዋናነት የአረብ ሃገራት ሚዲያዎች እንዲመረጡ፣
➋ ሁሉም ዞኖች ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማእከል የሚገቡ ምልምል ሰልጣኞችን በፍጥነት እንዲያዘጋጁ፣
➌ ታጣቂዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ወኪሎቻችን የማዛባት ስምሪት ወስደው እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ በ NSO በኩል ልዩ ክትትል እንዲደረግና ተቋሙ የተግባራት ዝርዝር በአስቸኳይ እንዲያቀርብ፣
➍ በውጭ ሃገራት የሚኖሩና መንግስትን የሚቃወሙ ዜጎች ዝርዝር መረጃ በየሃገራት ባሉ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች በኩል ተጠንቶ እንዲቀርብ፤ በቀረበው መረጃ መሰረት NSO NSO በሃገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ ከገንዝብ ቅጣት እሰከ እሰራት የሚደርሱ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጥብቅ ትዕዛዝ እንዲተላለፍ፣
➎ የኤርትራ ሰራዊትን ሞራል የሚያነሳሱ የተለያዩ ስራዎች እንዲሰሩ እንዲሁም ኢትዮጵያን የሚያወግዙ ህዝባዊ ሰልፎች በከተሞች እንዲከናዎኑና ሃላፊነቱን የማስታወቂያ ሚንስቴር ከሃገር ውስጥ ደህንነት ጋር በመቀናጀት እንዲወስድ፣
➎ ወደውጭ በሚጓዙና ወደሃገር ቤት በሚገቡ ዜጎች ላይ ልዩ ትኩረት እንዲደረግ የሚሉ ይገኙባቸዋል።
ከሰሞኑ ደግሞ ያገቡና የልጆች እናት የሆኑ ሴቶችን ጨምሮ እድሜአቸው ከ60 አመት በታች የሆኑ ዜጎቹ እንዲዘመገቡና ወደ ማሰልጠኛ ካምፕ እንዲገቡ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ተረጋግጧል።
@sheger_press@sheger_press